AmharaQuest's banner
AmharaQuest's profile picture

AmharaQuest

@AmharaQuest5,942 subscribers

Videos

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የመጨረሻውን ጥሪ አስተላለፉ ::
12:18

Sensitive content

This media may contain sensitive content.

AmharaQuest's profile picture

🚨"…በኢትዮጵያችን በኦሮሚያ አሩሲ እንደዚሁ እንደ ሱዳኑ ያለ አረመኔያዊ ግፍ ነው የተፈጸመው። "…የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሱዳን የግመል ነጋዴውን ሀሜቲ የመሀመድ ደጋሎን ፈጥኖ ደራሽ ጨፍጫፊ አሸባሪ ቡድን፣ በኢትዮጵያም የኦሮሞ ብልጽግና ወንጌል ፕሬዘዳንቱን አቢይ አሕመድን ይዛ ንፁሐንን በመጨፍጨፍ፣ በማስጨፍጨፍ፣ ለሀሜቲና ለአቢይ ድሮን ከእነ ኦፕሬተሩ፣ ከነ ቦንቡ፣ ጠመንጃ ከነ ጥይቱ፣ ዶላር በኮንቴነር እየሰጠች እሷ በምትኩ የሱዳንና የኢትዮጵያን ወርቅና መዓድነት ያለከልካይ ትዝቀዋለች፣ ታግዘዋለችም። "…በሱዳን መልካቸው ጠቆር ያሉት ሱዳናውያን እናንተ አረቦች አይደላችሁም ተብለው ለዘር ሳያስቀሩ ጨፍጭፈዋቸዋል። ክርስቲያን ሱዳኒዎችም ከጭፍጨፋው አልተረፉም። አላመለጡም። አላህ ወአክበር እያሉ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ነው የፈጇቸው። በተለይ እናቶችና ሕጻናቱ እንዴት አንጀት እንደሚበሉ አትጠይቁኝ። አንዲት ሴት እጇን አስረው አንጠልጥለው የሚፈጽሙባትም ግፍ ይዘገንናል። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም የሱዳኑን ጭፍጨፋ ሳይጠቅሱ በዓለም ላይ ክርስቲያኖች እና ክርስትና ጥቃት እየደረሰበት ነው በማለት የናይጄሪያው ቢኮ ሃራም ላይ እንደዛቱ ፎክስ ኒውስ ዘግቧል። "…በኢትዮጵያችን በኦሮሚያ አሩሲ እንደዚሁ እንደ ሱዳኑ ያለ አረመኔያዊ ግፍ ነው የተፈጸመው። ሕፃን ሽማግሌ አልቀራቸውም። ጭፍጭፍ ነው የደረጓቸው። የሱዳኑ በስልክ እየቀረጹ ቀጥታ በቲክቶክና በፌስቡክ ነው የለቀቁት። የእኛዎቹ እሱን ተከልክለው ሕዝቡ ነው አስከሬንና ዋይታውን ቀርጾ ዓለም ይመልከተን ያለው። የብልጽግና አገዛዝ እስከአሁን ትንፍሽ አላለም። የሱዳኑ ዓለም አቀፍ ጫጫታ ሲበዛበት ዋናውን ጨፍጫፊ በክብር አስረው ወደ ማረፊያ ወስደውታል። የኢትዮጵያዎቹ ማን አባቱ ነው የሚጠይቀን በማለት ጭራሽ ለቢቢሲ "ውሸት ነው" ሐሰት ነው የተጨፈጨፈ የለም በማለት ለሚዲያው ቃላቸውን ሰጥተዋል። በነገራችን ላይ ኤምሬት ለሱዳኑ ሀሚቲ ከደቡብ አሜሪካ ከኮሎምቢያ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችን ዶላር እየከፈለች ሶማሊያ ላይ በተከራየችው ወደቧ በኩል በገፍ እንደምታስገባም ዘገባዎችን እያየሁ ነበር። በዐማራ ክልልም የሚፈነዳውን ቦንብ ድሮን ኦፕሬት የሚያደርጉት ኤምሬት ቀጥራ ያመጣቻቸው ሲሆኑ አስተኳሾቹ ግን ኦፒዎቹ እዚያው ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ ያሉ ዐማራ መሳይ አሞሮች ናቸው ይባላል። "…ዘመናዊ ቀኝ ገዢ ለመሆን አፍሪካውያንን እየፈጀች ማዕድኑንም ዝቃ አፍሳ እየወሰደች ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እየገነባች፣ ለመዝናናት ደግሞ እኔው ጋር ኑ እያለች በንፁሐን ደም እየተገነባች የምተገኘውም ባቢሎን ኤምሬት ዱባይም እንደሰዶምና ገሞራ መጥፋቷ አይቀርም። ይሄ የጊዜ ጉዳይ ነው። ሱዳኖችም በአቢይ አሕመድ ምክንያት ኢትዮጵያም አብራ ነው የጨፈጨፈችን የሚል ክስ ማቅረብ ጀምረዋል። ይሄ የጠንቋይ የመተት የአስማት ባለዛር የኦሮሞ ብልፅግና መሪ ከሁሉ አጣልቶን ምን ዓይነት መዓት እየጠራብን እንደሆነ ፈጣሪ ይወቅ። ዘመዴ #StateSponsoredAmharaGenocide

AmharaQuest

10,891 Aufrufe • vor 8 Monaten