
Natnael Mekonnen
@NatnaelMekonne7 • 385,827 subscribers
No one can Judge me only God can Judge me ! https://t.co/peGFd40VeL https://t.co/s40zMIggYn
Shorts
Videos

🇪🇹 ታላቅ ዜና ለኢትዮጵያውያን — የሕዳሴ ግድብ ታሪክ በዓለም መድረክ! 🌍⚡CNN የኢትዮጵያ ትልቁ የልማት ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD) ዛሬ የኢትዮጵያን የኃይል ዘርፍ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን የኃይል የወደፊት ተስፋ እየቀየረ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ሆኗል። CNN Africa በቅርቡ ባቀረበው ዘገባ፣ ጋዜጠኛዋ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ወደ ሕዳሴ ግድብ በመሄድ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት እንዴት ኤሌክትሪክ እያመነጨ እና የቀጣናውን የኃይል ገጽታ እየቀየረ እንደሚገኝ ተመልክታለች። ይህ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ዜና ነው። ምክንያቱም ሕዳሴ ግድብ የውኃና የኮንክሪት ግንባታ ብቻ አይደለም፤ የኃይል፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የቀጣናዊ ትስስር ትልቅ መሠረት ነው። ⚡ በ2026 የተገለጹ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ፓወር መረጃዎችን የጠቀሱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፣ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ካመነጨችው ከ35,670 GWh በላይ ኤሌክትሪክ 51.5% ያህሉ ከሕዳሴ ግድብ የተገኘ መሆኑ ተዘግቧል። የግድቡ የተገጠመ የማመንጨት አቅም 5,150 ሜጋዋት ሲሆን፣ በአማካይ በዓመት 15,700 GWh ያህል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የታቀደ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ነው። ይህ ኃይል ለቤቶቻችን መብራት ብቻ አይደለም። ለፋብሪካዎች፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድ፣ ለከተሞች፣ ለቴክኖሎጂ እና ለአዳዲስ የሥራ ዕድሎች መሠረት ሊሆን የሚችል ሀብት ነው። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ከድንበር ባሻገር በመሸጥ የቀጣናው የኃይል አቅራቢ የመሆን ዕድሏን እያሳደገች ነው። ለምሳሌ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምትገዛውን ኤሌክትሪክ በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች መሆኗ በ2026 ተዘግቧል። ጎበዝ የCNN Africa ዘገባ ከአንድ የቴሌቪዥን ዘገባ በላይ ትርጉም አለው። ለዓመታት በዓለም ሚዲያ ሕዳሴ ግድብ ብዙውን ጊዜ ከውዝግብና ከዲፕሎማሲ አንፃር ሲዘገብ ቆይቷል። አሁን ግን ግድቡ ኤሌክትሪክ እያመነጨ፣ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ አቅም እየፈጠረ እና የቀጣናውን የኃይል ገበያ እየቀየረ ያለ ፕሮጀክት ተብሎ መታየቱ ራሱ ትልቅ ታሪክ ነው። የሕዳሴ ግድብ የአንድ ትውልድ ሕልም ከወረቀት ወደ ተጨባጭ የኃይል ምንጭ የተለወጠበት ምሳሌ ነው። አባይ አሁን ውኃ ብቻ አይፈስም — ኃይል፣ ተስፋና የልማት ዕድልም ይዞ ይፈሳል። 🇪🇹⚡ #ኢትዮጵያ #ሕዳሴግድብ #GERD #Ethiopia #GrandEthiopianRenaissanceDam #Africa #Energy #CNN
Natnael Mekonnen20,349 views • 4 days ago

ባለቀይ ቦኔት ሰራዊቱ በጠላት ሰፈር 🫡 የኤፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻ ዕዝ የሀገር መከታ ነው። ባለቀይ ቦኔት ሰራዊቱ በጠላት ሰፈር ስሙ ገናና ነው። ባለ ቀይ ቦኔት ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ቀይ መስመሮች እንዲያስጠብቅ ሆኖ ተሰርቷል። የዚህ ሰራዊት ምስረታ ሀይል አለኝና ጥቅሜን በሀይል ላስከብር የሚል አይደለም። አሊያም እንደ አንዳንዶች የባህር በሩን በደም ወስደነዋል ለሚሉ ሀገራት በደም ላስመልስ የሚልም አይደለም። ኢትዮጵያ በታሪኳ የወረረችው ሀገር ፣ በወረራ ሀይል ያስከበረችው ጥቅም የለም። ይህ ከትናነት እስከ ዛሬ የዘለቀ መርኋ ነው። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደሚሉት ዛሬ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለመስበር የሚጣደፋ ሀይሎች የጥፋት መልዕክተኞችን እብሪት መስበርና አላማቸውን ማምከን ቀዳሚ ተግባሩ መሆኑን ያሳስባሉ። በአሁኑ ወቅት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በሰው ኃይልና በትጥቅ ግንባታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ለየትኛውም አገር አፍራሽ ጥቃትና ለሰፈር ባንዳዎች ፈጣንና አስተማማኝ ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀ ነው። ኢትዮ መልህቅ የልዩ ዘመቻ ዕዝ የደረሰበትን የልህቀት ከፍታ እየቃኘ አብሯችሁ ቆይታ ያደርጋል። 👇
Natnael Mekonnen11,618 views • 4 days ago

🇪🇹 ክብር ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት! 🫡 እኛ በሰላም የምናሳልፈው ሌሊት፣ እነሱ የሀገርን ዳር ድንበር በንቃት ይጠብቃሉ። እኛ በነፃነት የምንኖርበት ቀን፣ እነሱ የሀገርን አደራ በቁርጠኝነት ይሸከማሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሉዓላዊነታችን መከታ፣ የሕዝባችን ጋሻ እና የሰላም ጠባቂ ነው። በተራራ፣ በሸለቆ፣ በበረሃም ሆነ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ የሚቆመው ለራሱ ክብር ሳይሆን፣ ሕዝቡ በሰላምና በመረጋጋት እንዲኖር ነው። በታማኝነት ያገለገሉ፣ በመስዋዕትነት የሀገርን ክብር ያስጠበቁ፣ ለባንዲራችን እና ለሕዝባችን የቆሙ ጀግኖቻችን ለዘላለም ይከበራሉ። የሀገር ሰላም በጀግኖች ትጋት ይጠበቃል፤ የሕዝብ ደህንነትም በመስዋዕታቸው ይጸናል። ስለዚህ ለእነዚህ ጀግኖች የምንሰጠው ክብርና እውቅና የሀገርን ክብር ማክበር ነው። ክብር ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት! 🇪🇹 ክብር ለሀገር ሲሉ ለቆሙ ጀግኖች! 🫡 ኢትዮጵያ በጀግኖቿ ትፀናለች፤ ሰላምዋም የሁላችን የጋራ ኃላፊነት ነው።
Natnael Mekonnen23,449 views • 21 days ago

የደብረጽዮንና የአብይ የአራት ሰአታት ውይይት ብዙዎቹ የህወሓት መሪዎች ጓደኞቼ ናቸው። እናም በሚዲያ ቃለምልልስ ላይ ስነሱ ስጠየቅ ክፉ ላለመናገር እጠነቀቃለሁ። ዛሬ ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ። ቅድም ጌታቸው የጠቀሰው ሰው (ዶ/ር ደብረጽዮን መሆናቸው ልብ ይሏል) እኔ ባለሁበት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለብቻቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ለአራት ሰአታት የፈጀ የእግር ጉዞ እያደረጉ ሰፊ ውይይት አድርገው ነበር ከዛ በኋላ እኔና ዶ/ር ደብረጽዮን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ውይይት አደረግን። ከዛ ምን ተፈጠረ? ዝርዝሩን ከአቶ ዘሪሁን ተሾመ አንደበት!
Natnael Mekonnen40,965 views • 1 month ago

የህግ ያለህ! የሚዲያ ባለስልጣን ያለህ! ከዛሬ ነገ ይሻሻላል አልን። ብዙ ነገር እንዳላየ አለፍን። ግን የዚህ አይነቱ ባለጌና የዚህ አይነቱን ባለጌ የሚያቀርቡ የዩቱዩብ ሚዲያዎች እንደተባይ እየተባዙ መጡ እንጂ ሊቀንሱ አልቻሉም። አንድ ተራ አንደበቱን እንኳን መግራት ያቃተው ሰው የሐገር መከላከያ ሰራዊትን የተከበረ መለዮ ለብሶ “እኔ ተልእኮ ላይ ነኝ” እያለ ይደነፋል። አንድ ቀን ወታደራዊ ስልጠና ሳይወስድ “ ወታደር ነኝ” ይላል። ጭራሽ ከአመራሮች ጋር የተነሳውን ፎቶ እያሳየ “ እየኝ ከጀነራል እገሌ ጋር የተነሳሁትን ፎቶ” እያለ ይጎፈላል። የመከላከያ አባል ሳይሆኑ ወታደር ነኝ ማለትም ሆነ የወታደሩን መለዮ ለብሶ መንቀሳቀስ ለአመታት የሚያስቀፈድድ ወንጀል ነው። ግን ማን ይጠይቀው? ማን ነገሬ ብሎ ይሄን ይቆጣጠር? ማን ሚዲያውን Monitor አድርጎ የዚህ አይነቱን ቀጣፊ ስርአት ያሲዝ? በየቀኑ በዱር በገደሉ ሐገር ሊያስቀጥል ደሙን የሚገብረው ወታደርስ እንዲህ አይነቱ ባለጌ አደባባይ ወጥቶ በስሙ ሲነግድና ከመከላከያው ባህሪና አላማ ውጪ ህዝብና ህዝብን የሚያናክስ የጥላቻ ስብከት ሲያስተጋባ ሲያይ ምን ይሰማዋል? የሐገር መከላከያ ሰራዊት መለዮ በማንም መንደርተኛ አረቂያም ሊለበስ አይደለም ሊነካ አይገባውም እያልን ይሄ ደግሞ መጥቶ ጭራሽ ደረቱን ነፍቶ ለተልእኮ ነው የለበስኩት ይለናል። ህግ! ስነስርአት! አይከበርም ወይ? ለምንድነው ምታሸማቅቁን? የዚህ አይነቱን ባለጌ አይዞህ የምትሉትስ ምን ነክቷችሁ ነው? ለምንድነው እኛንስ ተናጋሪዎች ምታደርጉን? ኢትዮጵያ ውስጥ እነዚህን ትኩረት ፈላጊ የዩቱዩብ ሚዲያዎችንስ የሚቆጣጠራቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤት የለም ወይ? ለሐገር ኢሜጅ አይጨነቁ! ለመከላከያ ክብር አይጨነቁ! ለህፃናት አእምሮ አይጨነቁ! ማነው ሃይ የሚልልን? ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ደቃቃ ስቱዲዮ ሰርቶ ፖድካስትና ሚዲያ እያለ ያለሙያውና ስራው በየቅያሱ የማይገመገም የዩቱዩብ ሚዲያ እያቋቋመ ቤተሰብ ሲያፈርስ አይተናል። ያለሙያው ዳኛ ሆኖ የቤተሰብን ገበና አደባባይ ሲያወጣ አይተናል፣ የፍርድቤትን ስራ ቀምተው የ DNA ውጤት እስከመናገር ደርሰዋል፣ ቤተሰብ የህብረተሰብ መሰረት ሆኖ ሳለ ለህፃናት ልጆች ሳይጠነቀቁ የባለትዳሮችን ገመና ፣ የወንድምና እህት፣ የእናትና ልጅን ለመስማት የሚያስፀይፉ ጉዶችን በየቀኑ ይግቱናል። ለቅሶ እየሸጡ በሚሊየን የሚቆጠር ብር ያፍሳሉ። ግን አንድም የሚቆጣጠራቸው አካል የለም። ግብር አይከፍሉ። ኮንተንታቸው አይመረመር። የሚያስተላልፉት ጉድ በብሮድካስቲንግ ባለስልጣን አይገመገም። መንግስት ሃይ አይላቸው። ምን ጉድ ነው? ማነው የሚመለከተው አካል? ማነው እነዚህን አረመኔ የሚዲያ ባለቤቶች የሚገራልን? ማነው የሰው ጓዳና ገመናን እየቀረፁ ወደህዝቡ የሚደፉትን እነዚህ የሰይጣን ቁራጮች አንድ የሚልልን? ይኸው ጭራሽ አሁን የማንንም ዱርዬ የተከበረውን የመከላከያን ልብስ አልብሰው ያንቧርቁብናል። ሚዲያዎቹን መቆጣጠር ካልቻላችሁ ለሚችል ሰው አሳልፋችሁ ስጡ። ህግ ይከበር። በየማህበራዊ ሚዲያው የሚተላለፉት ነገሮች ጆሮን ጭው ያደርጋሉ። መቼ ነው ይሄ የሚያበቃው? እንዲህ አይነት በሐገር መከላከያ ስም የሚነግዱ ባለጌዎችንስ መቼ ይሆን ህግ የሚቀጣልን?
Natnael Mekonnen29,640 views • 1 month ago

Moggaasni maqaa mootolii Bahiranagaash (Baahir Nigus) kan kenname Afaan Gi'iziitiin yemmuu ta'u, mootolii naannoo dachii Laga Marabii hanga Galaana Diimaatti jiru kan amma Eritiraa jedhamee waamamu bulchaa turaniif mootolii Impaayira Abisiiniyaatiin moggaafame ture. Itti waamamni isaaniis Abisiiniyaadhaaf ture. Bahiranagaashota keessaa Bahiranagaash Doorii kan akka lakkoofsa Awurooppaatti xumura bara 1400 hanga jalqaba 1500tti kan Naannicha bulchedha. Bahiranagaash Doorii, sabaan Oromoo ture. Looreetni Nagaa Addunyaa kab. MM Dr. Abiy Ahmed Ali Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ijaarsa Itoophiyaa keessatti gahee Oromoo ibsuuf akka fakkeenyaatti af-gaaffii OBN Afaan Oromoo wajjin godhan irratti kaasan keessaa kan kutamee gadhiifamedha. Haasaan kun boombii cimaadha, guutuusaa dhaggeeffannee walitti deebina.
Natnael Mekonnen13,058 views • 18 days ago

ይህ በመቐለ ከተማ አዲሽምድሑን የሚባል ሰፈር ውስጥ በአንድ አዳራሽ የህወሓት ታጣቂዎች ለጦርነት ያፈሷቸውን ወጣቶች ሌሊቱን በአዳራሹ አሳድረዋቸው ቀን በምታዩት መልኩ በባስ እየጫኑ ወደ ወታደራዊ ስልጠና ካምፕ እየተወሰዱ ነው። ወላጆቻቸው፣ በተለይም እናቶቻቸው፣ በሀዘንና በጭንቀት ዓይናቸው እንባ እያፈሰሱ ይመለከቷቸዋል። እናቶች በታጣቂዎች ከቦታው እንዲርቁ በኃይል ቢነገራቸውም የእናት ሆድ አልችል ብሎ እንደተመለሱ ያገኘውት መረጃ ያመለክታል። ሌላው የህወሓት ግፍ እነዚህ በግዳጅ ታፍሰው የተወሰዱት ወጣቶች መካከል አብዛኞቹ ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመልሰው የነበሩ ወጣቶች ናቸው:: የትግራይ ወጣቶች በህወሓት መራሹ ቡድን የሚያጋጥማቸው መከራ መጨረሻ የለውም። በቅርቡም ወጣቶች ከትግራይ እንዳይወጡ የሚከለክል እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
Natnael Mekonnen29,902 views • 1 month ago

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የምትገኝ አንዲት ወጣት በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጨችው አዲስ የቪዲዮ መልዕክት፣ በክልሉ ውስጥ አስደንጋጭ የሆነ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን አጋለጠች። ወጣቷ በቪዲዮው ላይ እንዳብራራችው፣ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ከቤተክርስቲያን፣ ከመንገድ እና ከሆቴሎች እየታፈሱ ወደ ጦርነት ማሰልጠኛዎች እየተወሰዱ ነው። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የምትገልጸው ይህቺ ወጣት፣ ምልመላው ማንንም የማይመርጥ መሆኑን ታስረዳለች። ከገጠር አካባቢዎች ለሃይማኖት ትምህርት የመጡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተማሪዎች እና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ሳይቀሩ የግዳጅ ምልመላው ሰለባ ሆነዋል። ምልመላውን የሚያካሂዱት አካላት ከቤት ወደ ቤት እየዞሩ "ለጦርነት የሚደርስ ልጅ አላችሁ ወይ?" በማለት ቤተሰብን ጭምር እያስገደዱ እንደሚገኙም አክላለች። ከጦርነቱ ስጋት በተጨማሪ፣ በክልሉ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ እና የምግብ እጥረት ህዝቡን ክፉኛ እየፈተነው እንደሚገኝ በዘገባው ተጠቅሷል። የጥሬ ገንዘብ እጥረት በመኖሩ የዕለት ተዕለት ግብይት በሞባይል ባንኪንግ (Mobile Banking) ብቻ እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሰችው ወጣቷ፣ "በማንኛውም ሰዓት ኢንተርኔት ቢቋረጥ በረሃብ እናልቃለን፤ ቀጣዩ ጉርሻችን ከየት እንደሚመጣ አናውቅም" ስትል የሁኔታውን አሳሳቢነት አስረድታለች። ወጣቷ አሁን እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ አጥብቃ በመኮነን፣ ጦርነቱ ለማንም የማይጠቅም እና አሸናፊ የሌለው መሆኑን ገልጻለች። በፌደራል መንግስቱም ሆነ አሁን ትግራይን እያስተዳደሩ ባሉ አካላት ላይ ጠንካራ ትችት ያቀረበች ሲሆን፣ የባለስልጣናት ልጆች በአሜሪካ እና በአውሮፓ በሰላም እየኖሩ፣ የድሃው ልጅ ግን ለማንም በማይጠቅም ጦርነት እንዲማገድ እየተደረገ ነው ብላለች። "ወደ ጦርነት መሄድ አንፈልግም፤ ማንም ጦርነት እንዲሄድ አንፈልግም። መሞት ካለብኝም እዚሁ ግደሉኝ" በማለት ምሬቷን አሰምታለች። ባለፈው ጦርነት በርካቶች ቢሞቱም ምንም የመጣ ለውጥ አለመኖሩንም አስታውሳለች። በመጨረሻም፣ ይህንን ቪዲዮ ያዘጋጀችው በክልሉ ያለውን እውነተኛ ገጽታ እና የህዝቡን ስቃይ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ መሆኑን ገልጻለች። የትግራይ ወጣቶች በራሳቸው ፍላጎት ወደ ጦርነት እየገቡ እንዳልሆነ እና በግዴታ እየታፈሱ መሆኑን ዓለም እንዲያውቅላት በማስገንዘብ መልዕክቷን አጠናቅቃለች። ይህ አዲስ ክስተት በክልሉ ዳግም የጦርነት እና አለመረጋጋት ስጋት እያንዣበበ መሆኑን የሚያሳይ ማሳያ ሆኗል።
Natnael Mekonnen29,739 views • 1 month ago