
Natnael Mekonnen
@NatnaelMekonne7 • 387,350 subscribers
No one can Judge me only God can Judge me ! https://t.co/peGFd40VeL https://t.co/s40zMIggYn
Shorts
Videos

ታላቅ ቀን! እንደትናንት ደስ ብሎኝ አያውቅም። በህይወቴ ሰራሁ ከምላቸው ቁምነገሮች አንዱ የታላቁ ፊልድ ማርሻልን የህይወት ታሪክ የሚያትተውን መፅሀፍ እሳቸው በህይወት እያሉ ታትሞ እንዲወጣ አስታዋፅኦ በማድረጌ ነው። ይሄ መፅሀፍ ክብሩ ለፊልድ ማርሻሉ አይደለም። እሳቸው የክብር የመጨረሻው ተራራ ላይ ቆመዋል። ይሄ ክብር ለመላ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፣ ለታላቁ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ነው። የትናንትናው ቀን ኢትዮጵያ ጀግኖቿ ሲሞቱ እየጠበቀች የምታከብር አገር ብቻ ሳትሆን የዋሉላትን በቁማቸው፣ ሳያረጁ፣ ሳይታመሙ፣ ሳያልፉ፣ “አመሰግናለሁ” የምትል አገር መሆኗን ያሳየንበት ቀን ነበር። ይሄ መፅሀፍ ታሪኩ የሚያጠነጥነው በፊልድ ማርሻል ህይወት ዙሪያ ቢሆንም፣ በሳቸው ህይወት ውስጥ አሁን በህይወት ያሉም ሆኑ ያለፉ ታላላቅ የጦር መሪዎች አሉ። ሰው ሲሞት ጠብቀን ታሪኩን የመፃፍና የማወደስ፣ ሌጋሲውንና መንፈሱን ለትውልድ የማድረስ ቀንበር በዚህ መፅሀፍ የተሰበረ ይመስለኛል። ሰዎች በህይወት እያሉ፣ ሳይታመሙ፣ ሳያረጁ፣ ከስልጣን ሳይወርዱ፣ ያለፉባቸውን የህይወት እጥፋቶች ከራሳቸው ከባለታሪኩ አፍ ተጠይቆ በመፅሀፍ ማስቀረት በሌላው አለም የተለመደ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥም ከዚህ በኋላ በሰፊው ሊቀጥል የሚገባው እጅግ አስፈላጊ ስራ ነው። ለአንድ አገር የስነፅሁፍም ሆነ ወታደራዊ ታሪክም ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ፊልድ ማርሻልን እኔ ባየኋቸው አይን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያያቸው ምኞቴ ነበር። በህይወቴ እንደሳቸው ቅን፣ ትሁት፣ በአገር ፍቅር ስሜት የተሞላ፣ እጅግ አሰላሳይና አዋቂ ሰው አላየሁም። የአገሬ መከላከያ ሰራዊትና ኢትዮጵያ እንደሳቸውና እንደሳቸው ባሉ ሰዎች እጅ በመሆናቸው ኩራትም ትልቅ መተማመንም ይሰማኛል። እንደአለመታደል ሆኖ ጀግናን ማክበር ይተናነቀናል እንጂ እንደፊልድ ማርሻል ላሉ የኢትዮጵያ ጀግኖች በቁማቸው አፈር ውስጥ ሳይገቡ በስማቸው ትልልቅ ፋውንዴሽኖች ሊቋቋሙላቸው፣ ሀውልቶች ሊሰሩላቸው፣ መንገዶች ሊሰየሙላቸው፣ ታሪኮቻቸው በዚህ መልኩ በመፅሀፍት ሊፃፉ ይገባል! አንድ ኢትዮጵያዊ ከ 17 አመቱ ጀምሮ ወጣትነቱን፣ ህልሙን፣ ህይወቱን ሰጥቶ ከ42 አመት በላይ እናት አገሩን በታማኝነት ከማገልገል ሌላ ለአገሩ ምን ሊሰጥ ይችላል? ኢትዮጵያስ ከአንድ ዜጋዋ ከዚህ በላይ ምን ልትጠብቅ ትችላለች? ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለዚች ሀገር የከፈሉት ውዱ እድሚያቸውን፣ ወጣትነታቸውን፣ ጉብዝናቸውን፣ ነው። ሊያውም ከብዙ የሞት ትንቅንቅ ፣ ስቃይ፣ ረሃብ ፣ መገፋት፣ ጋር! ይሄንን የተኖረ ህይወት ሙሉ ለሙሉም ባይሆን በከፊል በዚህ ታሪካዊ መፅሀፍ እንዲሰነድ የበኩሌን አስተዋፅኦ በማበርከቴ ክብር የሚሰማኝ ለዚህ ነው። ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለኢትዮጵያችን ላደረጉት ሁሉ እናመሰግናለን!
Natnael Mekonnen18,856 views • 4 days ago

እኝህን ኢትዮጵያዊ የትግራይ እናት በአሁኑ ጊዜ ከማን ጋር ብንታረቅ ይሻላል ይላሉ ብሎ ጠያቂው ሲጠይቃቸው: የትግራይ እናት እንዲህ ብለው ይመልሳሉ። ''ከዐቢይ ብንታረቅ ይሻለናል።'' ከኢሳያስስ ብሎ ሌላ ጥያቄ ሲጨምርላቸው፦ ''ልጆቻችን ለካራና ለሞት ዳረግን እንጂ ምን ፈየደልን ከኢሳያስ ጋር መሆን።'' ብለው ይመልሳሉ።ይህ የትግራይ እናቶች ድምፅ ነው። ግን ሁመራኮ አንሰጥም ብሏል ብሎ ሲጠይቃቸው፦ ''ሁመራ አልሰጥም አላለም፤ በሰላም ነው ሚሰጠን። እኛም በሰላም መጠየቅ አለብን። ሲጀመርም እኛ እንደ ትግራይ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላምና በመተቃቀፍ ነው እንጂ ሌላ መንገድ አያስፈልገንም። ይህ ግልፅ መሆን አለበት። ከዐቢይ ጋርም በሰላም ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው። ይህ መታወቅ አለበት። ለፈጣሪም እንደ እናቶች እንደዚህ ነው የምንፀልየው። ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ብቻ ነው የሚያዋጣን። ሰላሙ ያምጣልን።''
Natnael Mekonnen26,851 views • 8 days ago

እንደዛሬ ስቄ አላውቅም! 🤣 ከልደቱ አያሌው በላይ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴው፣ ለተነሳበትና ለተቀመጠበት ነገር ሁሉ መግለጫ መስጠት የሚወድ ሰው በዚች ምድር ላይ አለ ግን? ዛሬ ደግሞ ሱፉንና ከረቫቱን ለብሶ፣ ቁምነገረኛ መስሎ መጥቶ እኛ ከ17 አመት በፊት ከፍተን ያረጀንበትን ፌስቡክ… “ብዙ አውጥቼና አውርጄ በደጋፊዎቼ ጉትጎታና ጥያቄ ፌስቡክ አካውንት ልከፍት ነው” ብሎ መግለጫ አልሰጠም መሰላችሁ 🤣 ወይ ልደቱ ....መቼ ይሆን ዘመኑን የሚቀላቀለው? ልዴ ምን ሆነህ ነው በናትህ? ፈጠን ፈጠን በል እንጂ ወደኋላ እየቀረህ ነውኮ! 😄
Natnael Mekonnen48,853 views • 21 days ago

ትናት በመቀሌ ከተማ ወጣቶችና ህፃናት ለውትድርና በግዳጅ ታፍሰው ከተጫኑበት መኪና ላይ በመዝለል ሲያመልጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ነው።
Natnael Mekonnen38,629 views • 27 days ago

ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው የሙዚቃ አልበም ሊያወጣ ነው‼ ልደቱ እንደገለፀው ሀሳብን በዜማ’ የሚል አንድ አልበም በ AI ሰርቻለሁ። እና በውስጡ 12 ዘፈኖችን የያዘ ነው። ይሄ አልበም የፖለቲካ ፍልስፍናዬን፣ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች፣ በሌሎች የሕይወት ዘርፎችም ያለኝን እይታ የምገልጽበት ነው እና ለአዲሱ ዓመት ከመስከረም 1 ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት በየእለቱ ቀን አንድ አንድ ዘፈን እለቃለሁ።” በማለት ገልጿል።ፖለቲከኛው በመጨረሻም እዚህ ላይ በመድረሱ ብዙዎች እየተነጋገሩበት ነው።
Natnael Mekonnen18,896 views • 21 days ago

የደብረጽዮንና የአብይ የአራት ሰአታት ውይይት ብዙዎቹ የህወሓት መሪዎች ጓደኞቼ ናቸው። እናም በሚዲያ ቃለምልልስ ላይ ስነሱ ስጠየቅ ክፉ ላለመናገር እጠነቀቃለሁ። ዛሬ ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ። ቅድም ጌታቸው የጠቀሰው ሰው (ዶ/ር ደብረጽዮን መሆናቸው ልብ ይሏል) እኔ ባለሁበት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለብቻቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ለአራት ሰአታት የፈጀ የእግር ጉዞ እያደረጉ ሰፊ ውይይት አድርገው ነበር ከዛ በኋላ እኔና ዶ/ር ደብረጽዮን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ውይይት አደረግን። ከዛ ምን ተፈጠረ? ዝርዝሩን ከአቶ ዘሪሁን ተሾመ አንደበት!
Natnael Mekonnen40,965 views • 2 months ago

ካንተ ጋራ Situ Jira ሲከፉኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ ከጐኔ ሲጠፉ የሚረዳኝ ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ አለሁኝ የምትል ለተጐዳ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ ከወረት ያልሆነ ታላቅ ፍቅርህ ሀዘኔን የሚያልፍ መፅናናትህ እምባዬን ያበሰከው ደጋፊዬ ስተከዝ ሆንክልኝ መፅናኛዬ አትከዳኝ አትለወጥ በሁኔታ አተወኝ ስደከም ስበረታ ፍቅርህ የፍቅሮች ሁሉ አውራ ዘለዓለም የሚቀጥል እያበራ ዘማሪ መስከረም (መስኪዬ ) Situ Jira ❤️🙏
Natnael Mekonnen21,928 views • 1 month ago

የዩቱዩብ አቋራጭ የሽቀላ ስትራቴጂ መጀመሪያ በተባራሪ ወሬ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በድንገተኛ የቤተሰብ ሁኔታ (እህታቸው ድንገተኛ ሞት) አሜሪካ እንደገቡ ትሰማለህ። ከዚያ ይህንን ዜና እንዴት ወደገንዘብ መቀየር እንዳለብህ ታሰላስልና “የምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከሐገር ፈረጠጡ” ብለህ ሰፊ ዘገባ ትሰራና ብዙ View ታገኛለህ። ከዛ ሰውየው ሲመለሱ ውሸታም መባልህ ስለማይቀር ሽቀላህን ከጨረስክ በኋላ ሳይመለሱ በፊት ዜናውን በስህተት እንደሰራህ ትናገራለህ። (ሽቀላውም አልቀረብህም ውሸታምም አልተባልክም) ሶስተኛው Step ደግሞ Damage controlling ይባላል። “ሳታጣራ ለምን አወራህ መጀመሪያ?” የሚሉህ ሲመጡ አይንህን አፍጥጠህ ትመጣና “መረጃዬኮ ሙሉ ለሙሉ ስህተት አልነበረም። መቅረታቸውን እንጂ የዋሸሁት አሜሪካ መምጣታቸው ሃቅ ነው” ብለህ ሃጢአትህን በግማሽ ትቀንሳለህ። አራተኛው ደረጃ Victim blaming ይባላል። አንተው ዋሽተህና የሰውየውን ስም አጥፍተህ ስታበቃ ሃላፊነት ከመውሰድ ይልቅ እኚህን እሚያክሉ አዛውንት "እሳቸውስ ለምን ሲሉ በዚህ ሰአት አሜሪካ መጡ" ብለህ እንደህፃን ልጅ ትቆጣጠርና ጥፋቱን ሁሉ የሳቸው አድርገህ ሹልክ ብለህ ታመልጣለህ ማለት ነው። 😆 ይሄ ሁሉ ሚደረገው እንግዲህ ለዚያች የዩቱዩብ ሽቀላ ሲባል ነው ወገን። ፕሮፌሰሩ ከመጀመሪያም አሜሪካ እንደማይቀሩ ሰውየው ያውቀዋል። ነገር ግን ፕሮፌሰሩ ዘመድ ጥየቃ ከሐገር ወጡ ቢል ዩቱዩብ ላይ ብዙ እይታ አያገኝም “ኮበለሉ” ቢል ግን ዜናው ብዙ እይታ እንደሚያገኝለት ስለገባው በስማቸው እስከ 1000 ዶላር ሸቀለና እይታው እየቀነሰ ሲመጣ ሳይጋለጥ በፊት ራሱ መጥቶ ራሱ ላይ ግለ ሂስ አወረደ 😆 ለዚህ ሰውዬ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሽቀላ ናቸው ጎበዝ! ጣቃ ነጋዴ ለመሆን ተፈጥረህ በስህተት ፖለቲካ ውስጥ ስትገባ እንዲህ ነው ምታስበው።
Natnael Mekonnen22,785 views • 1 month ago

አስረስ ማረ የአቶ አማኑኤልን ሃሳብ ደግፎ አንዳርጋቸው ፅጌን ገብቶለታል። አሁን ጥያቄው አንዳርጋቸው ህወሃቶችም “ተኩላ” ካሉት። አስረስ ማረም ቀላማጅ ካለው። ማንን ወክሎ ከማን ጋር ነው የተፃመደው? 🤣 የወሎ ሰው "አላህ ሲጣላ በትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም" ይላል። አንዳርጋቸው በሁለቱም ቡድን ተተፍቶ የኢሳያስ አፍወርቂ ጥፍር ላይ ተንጠልጥሎ ቀርቷል 🤣 አስረስ ማረ ግን የህወሃት ወዳጁ አማኑኤልን ከሞንጆሪኖ ጥፊ ለማዳን ያሳየውን ቁርጠኝነት ሳናደንቅ አናልፍም 😛
Natnael Mekonnen18,469 views • 1 month ago

🇪🇹 ታላቅ ዜና ለኢትዮጵያውያን — የሕዳሴ ግድብ ታሪክ በዓለም መድረክ! 🌍⚡CNN የኢትዮጵያ ትልቁ የልማት ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD) ዛሬ የኢትዮጵያን የኃይል ዘርፍ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን የኃይል የወደፊት ተስፋ እየቀየረ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ሆኗል። CNN Africa በቅርቡ ባቀረበው ዘገባ፣ ጋዜጠኛዋ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ወደ ሕዳሴ ግድብ በመሄድ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት እንዴት ኤሌክትሪክ እያመነጨ እና የቀጣናውን የኃይል ገጽታ እየቀየረ እንደሚገኝ ተመልክታለች። ይህ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ዜና ነው። ምክንያቱም ሕዳሴ ግድብ የውኃና የኮንክሪት ግንባታ ብቻ አይደለም፤ የኃይል፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የቀጣናዊ ትስስር ትልቅ መሠረት ነው። ⚡ በ2026 የተገለጹ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ፓወር መረጃዎችን የጠቀሱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፣ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ካመነጨችው ከ35,670 GWh በላይ ኤሌክትሪክ 51.5% ያህሉ ከሕዳሴ ግድብ የተገኘ መሆኑ ተዘግቧል። የግድቡ የተገጠመ የማመንጨት አቅም 5,150 ሜጋዋት ሲሆን፣ በአማካይ በዓመት 15,700 GWh ያህል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የታቀደ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ነው። ይህ ኃይል ለቤቶቻችን መብራት ብቻ አይደለም። ለፋብሪካዎች፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድ፣ ለከተሞች፣ ለቴክኖሎጂ እና ለአዳዲስ የሥራ ዕድሎች መሠረት ሊሆን የሚችል ሀብት ነው። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ከድንበር ባሻገር በመሸጥ የቀጣናው የኃይል አቅራቢ የመሆን ዕድሏን እያሳደገች ነው። ለምሳሌ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምትገዛውን ኤሌክትሪክ በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች መሆኗ በ2026 ተዘግቧል። ጎበዝ የCNN Africa ዘገባ ከአንድ የቴሌቪዥን ዘገባ በላይ ትርጉም አለው። ለዓመታት በዓለም ሚዲያ ሕዳሴ ግድብ ብዙውን ጊዜ ከውዝግብና ከዲፕሎማሲ አንፃር ሲዘገብ ቆይቷል። አሁን ግን ግድቡ ኤሌክትሪክ እያመነጨ፣ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ አቅም እየፈጠረ እና የቀጣናውን የኃይል ገበያ እየቀየረ ያለ ፕሮጀክት ተብሎ መታየቱ ራሱ ትልቅ ታሪክ ነው። የሕዳሴ ግድብ የአንድ ትውልድ ሕልም ከወረቀት ወደ ተጨባጭ የኃይል ምንጭ የተለወጠበት ምሳሌ ነው። አባይ አሁን ውኃ ብቻ አይፈስም — ኃይል፣ ተስፋና የልማት ዕድልም ይዞ ይፈሳል። 🇪🇹⚡ #ኢትዮጵያ #ሕዳሴግድብ #GERD #Ethiopia #GrandEthiopianRenaissanceDam #Africa #Energy #CNN
Natnael Mekonnen21,265 views • 1 month ago

ሰበር መረጃ‼️ የሕወሓት ታጣቂዎች ከኤርትራ ድጋፍ እንደተደረገላቸውና ለመከላከያ እጃቸውን መስጠታቸውን ተናገሩ በቪዲዮው ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የሕወሓት ታጣቂዎች እንቅስቃሴያቸው በኤርትራ በኩል ድጋፍና ማመቻቸት እንደተደረገለት ገልጸዋል። በኮር 32፣ አርማ 13፣ ክፍለጦር ዕርደ ትግራይ የሃይል መሪ የነበሩት አደራ ንጋሽ እንደገለጹት፤ ከአዲሚቲ ተነስተው በኤርትራ መኪናዎች ታጅበው እስከ ኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ተጓጓዘዋል።በኋላም በነበረው ውጊያ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውንና በጥሩ ሁኔታ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
Natnael Mekonnen23,300 views • 1 month ago