Natnael Mekonnen's banner
Natnael Mekonnen's profile picture

Natnael Mekonnen

@NatnaelMekonne7 • 387,350 subscribers

No one can Judge me only God can Judge me ! https://t.co/peGFd40VeL https://t.co/s40zMIggYn

Shorts

መሪዎቹ ወደ ስብሰባው በአንድ መኪና! የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 በህንድ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ በአንድ መኪና ሲጓዙ ታይተዋል። መኪናው የፕሬዝዳንት ፑቲን ሲሆን፣ ፑቲን ወደ ውጭ ሀገራት በሚያደርጉት ጉዞ የራሳቸውን የፕሬዝዳንት መኪና ይዘው መጓዛቸው የተለመደ ነው። በተለምዶም የፑቲን መኪና እጅግ ጥብቅ የደህንነት ፕሮቶኮል ያለው በመሆኑ፣ ሌላ መሪ አብሯቸው ሲጓዝ ማየት ብዙ ጊዜ የሚታይ ነገር አይደለም። በዚህ ጊዜ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፑቲን ጋር በአንድ መኪና ወደ ስብሰባው ሲጓዙ መታየታቸው ትኩረት የሚስብ ነው። ይህን እንደ ተራ የትራንስፖርት ሁኔታ ብቻ ማየት አይገባም፤ በዲፕሎማሲ ዓለም እንዲህ ያሉ ምስሎች ብዙ ጊዜ የመሪዎችን ቅርበት፣ የግንኙነት ደረጃ እና የጋራ ፖለቲካዊ መልዕክት የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይችላሉ። ፑቲን የሚጠቀሙት የፕሬዝዳንት መኪና Aurus Senat የተባለ በሩሲያ የተሰራ የቅንጦትና ከፍተኛ ጥበቃ ያለው ሊሙዚን ነው። የፕሬዝዳንቱ ልዩ ስሪት የታጠቀ (armored) ሲሆን፣ የሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ ኮንቮይ ዋና አካል ነው። ፑቲንም በአንዳንድ የውጭ ሀገር ጉዞዎቻቸው ይህንን መኪና ይጠቀማሉ። በዚህ ጊዜ ግን ዐቢይ አህመድ ከፑቲን ጋር በዚሁ መኪና ውስጥ አብረው ሲጓዙ መታየታቸው ትኩረት ስቧል። በተለይ የፕሬዝዳንታዊ መኪናውን ጥብቅ የደህንነት አሠራር ስንመለከት፣ ሁለቱ መሪዎች በአንድ መኪና መጓዛቸው በራሱ የሚያስተውል ነው።

51,337 次观看

NewsAlret‼️ ወጣቶች በትግራይ ክልል በህወሓት መራሹ ታጣቂዎች የሚፈጸምባቸውን የግዳጅ ጦርነት አፈሳ አምልጠው ሲሮጡ:: ይህ ሺዲዮ ዛሬ ጠዋት በመቀሌ 17 ቀበሌ የተከሰተ ነው። ሰዎች ከዕድሜ በታች የሆነን ልጅ ለመውሰድ ወደ ቤቱ ሲሄዱ፣ ልጁ ‘አባቴን ጥሩልኝ!’ እያለ ይጮኽ ነበር። ህወሓቶች (ሞንጆሪኖ) ግን በሚዲያ ላይ ወጥተው ‘ግዳጅ ወይም አስገዳጅ ምልመላ የለም!’ እያሉ በወጣቶች ሕይወት ይቀልዳሉ። ህወሓት ለረጅም ዘመን የትግራይ እናቶችን በእንባና በሀዘን ውስጥ ማኖርን እንደ ፖለቲካ መንገድ ሲጠቀም ቆይቷል። ከህወሓት በላይ ግን የሚያስገርሙኝ፣ ይህን ሁሉ የእናቶች ለቅሶና የወጣቶች መከራ እያዩ ዝምታን የመረጡ ሰዎች ናቸው። ራሳቸውን የትግራይ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አንዳንድ ዲያስፖራዎች፣ እንዲሁም እውነታውን ችላ ብለው የፖለቲካ ከበሮ የሚደልቁ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ይበልጥ ያስደንቁኛል። ትግራይ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች በፋሽን በሞዴሊንግ አንዳንዱ ደግሞ በየክለቡ ከበሮ ደላቂና አስደላቂ የሆኑ ትግራዋይ ነን በማለት ጆኖሳይድ ትግራይ ትስዐር እያሉ በየ ሶሻል ሚዲያቸው ሲያደነቁሩን ለነበሩ የአዞ እምባ አልቃሶች ትግራይና የትግርይ ህዝብ ሳይሆን ህወሓት ናፋቂዎች ለሆኑት ነው ጥያቄዬ ህወሓትን እንደናፈቃችሁት ይቀራል እኔም ስለእናተ መሰሪነት አስመሳይነት የነበረው የአዞ እምባችሁ ለትግራይ ወጣትና ህዝብ እናቶች ሳይሆን ለህወሓት እንደነበር መናገርና መፃፌን እቀጥላለሁ

38,843 次观看

እንኳን ሰው ወፍ እናለምዳለን፡፡

እንኳን ሰው ወፍ እናለምዳለን፡፡

13,503 次观看

Ethiopia welcomes Turkish President Erdogan with elegance and high regard. Welcome to the #LandOfOrigins Mr President. Ethiopia knows how to welcome and host. 🇪🇹🇹🇷 #Turkey #Ethiopia

Ethiopia welcomes Turkish President Erdogan with elegance and high regard. Welcome to the #LandOfOrigins Mr President. Ethiopia knows how to welcome and host. 🇪🇹🇹🇷 #Turkey #Ethiopia

15,063 次观看

ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ (The Man) እነ አንቶኔ ይውሩ አንተ ስራህን ስራ ትውልድ ቅረጽ 🙌

ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ (The Man) እነ አንቶኔ ይውሩ አንተ ስራህን ስራ ትውልድ ቅረጽ 🙌

30,440 次观看

አሰብን እንጋራለን ስንል ፕሬዘዳንት ኢሳያስም አጨብጭቧል። ትናንት ከእንቅልፋቸው ነቅተው ማዳመጥ የለመዱ ሰዎች የባህር በር ጥያቄን ትናንት የጀመርነው ይመስላቸዋል። በዚህ ቪዲዮ እንደሚታየው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤርትራውን ፕሬዘዳንት ፊትለፊታቸው አስቀምጠው "ከኤርትራ ጋር አሰብን እንጋራለን" ሲሉ ይደመጣል። ፕሬዘዳንት ኢሳያስም በአድናቆትና በመስማማት ሲያጨበጭቡ ይታያል። አንዳንድ ማስለቀስን ሙያ ያደረጉ ሰዎች እንደሚሉት የባህር በር ጥያቄን ለፖለቲካ ብሽሽቅ አልጀመርነውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጣ ቀን አንስቶ በግልፅ ሲያነሳው የነበረና እስከሚሳካልን ድረስ ስናነሳው የምንኖረው ፍትሃዊ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ አላማችን ነው። እኛ ያለውሀ ልንዘጋ አንችልም። ትልቅ ነን። መተንፈሻ ያስፈልገናል። በምስራቅ አፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ ገንብተናል። ትልቁ የሀዝብ ቁጥር የኛ ነው። ትልቅ የቆዳ ስፋት አለን። ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ ተደምረው በህዝብ ቁጥር እንበልጣቸዋለን። ለግዜው ከባህር የምንርቀው ጥቂት ኪሎሜትር ብቻ ነው። አለም አቀፍ ህግ ይፈቅድልናል። ታሪክ ይደግፈናል። የኛ የባህር በር ጥያቄ ለጎረቤት ሐገራት ስጋት ሳይሆን በረከት ነው። ስለዚህ ጥያቄውን ዛሬ አልጀመርነውም ዛሬም አናቆመውም። ጥያቄያችንን ምናቆመው ጥያቄያችን ሲመለስ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ የባህር በር ታገኛለች። ባንዳዎችም ይህንን ታሪክ እያለቀሱ ያዩታል!

16,924 次观看

Videos

NatnaelMekonne7's profile picture

ታላቅ ቀን! እንደትናንት ደስ ብሎኝ አያውቅም። በህይወቴ ሰራሁ ከምላቸው ቁምነገሮች አንዱ የታላቁ ፊልድ ማርሻልን የህይወት ታሪክ የሚያትተውን መፅሀፍ እሳቸው በህይወት እያሉ ታትሞ እንዲወጣ አስታዋፅኦ በማድረጌ ነው። ይሄ መፅሀፍ ክብሩ ለፊልድ ማርሻሉ አይደለም። እሳቸው የክብር የመጨረሻው ተራራ ላይ ቆመዋል። ይሄ ክብር ለመላ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፣ ለታላቁ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ነው። የትናንትናው ቀን ኢትዮጵያ ጀግኖቿ ሲሞቱ እየጠበቀች የምታከብር አገር ብቻ ሳትሆን የዋሉላትን በቁማቸው፣ ሳያረጁ፣ ሳይታመሙ፣ ሳያልፉ፣ “አመሰግናለሁ” የምትል አገር መሆኗን ያሳየንበት ቀን ነበር። ይሄ መፅሀፍ ታሪኩ የሚያጠነጥነው በፊልድ ማርሻል ህይወት ዙሪያ ቢሆንም፣ በሳቸው ህይወት ውስጥ አሁን በህይወት ያሉም ሆኑ ያለፉ ታላላቅ የጦር መሪዎች አሉ። ሰው ሲሞት ጠብቀን ታሪኩን የመፃፍና የማወደስ፣ ሌጋሲውንና መንፈሱን ለትውልድ የማድረስ ቀንበር በዚህ መፅሀፍ የተሰበረ ይመስለኛል። ሰዎች በህይወት እያሉ፣ ሳይታመሙ፣ ሳያረጁ፣ ከስልጣን ሳይወርዱ፣ ያለፉባቸውን የህይወት እጥፋቶች ከራሳቸው ከባለታሪኩ አፍ ተጠይቆ በመፅሀፍ ማስቀረት በሌላው አለም የተለመደ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥም ከዚህ በኋላ በሰፊው ሊቀጥል የሚገባው እጅግ አስፈላጊ ስራ ነው። ለአንድ አገር የስነፅሁፍም ሆነ ወታደራዊ ታሪክም ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ፊልድ ማርሻልን እኔ ባየኋቸው አይን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያያቸው ምኞቴ ነበር። በህይወቴ እንደሳቸው ቅን፣ ትሁት፣ በአገር ፍቅር ስሜት የተሞላ፣ እጅግ አሰላሳይና አዋቂ ሰው አላየሁም። የአገሬ መከላከያ ሰራዊትና ኢትዮጵያ እንደሳቸውና እንደሳቸው ባሉ ሰዎች እጅ በመሆናቸው ኩራትም ትልቅ መተማመንም ይሰማኛል። እንደአለመታደል ሆኖ ጀግናን ማክበር ይተናነቀናል እንጂ እንደፊልድ ማርሻል ላሉ የኢትዮጵያ ጀግኖች በቁማቸው አፈር ውስጥ ሳይገቡ በስማቸው ትልልቅ ፋውንዴሽኖች ሊቋቋሙላቸው፣ ሀውልቶች ሊሰሩላቸው፣ መንገዶች ሊሰየሙላቸው፣ ታሪኮቻቸው በዚህ መልኩ በመፅሀፍት ሊፃፉ ይገባል! አንድ ኢትዮጵያዊ ከ 17 አመቱ ጀምሮ ወጣትነቱን፣ ህልሙን፣ ህይወቱን ሰጥቶ ከ42 አመት በላይ እናት አገሩን በታማኝነት ከማገልገል ሌላ ለአገሩ ምን ሊሰጥ ይችላል? ኢትዮጵያስ ከአንድ ዜጋዋ ከዚህ በላይ ምን ልትጠብቅ ትችላለች? ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለዚች ሀገር የከፈሉት ውዱ እድሚያቸውን፣ ወጣትነታቸውን፣ ጉብዝናቸውን፣ ነው። ሊያውም ከብዙ የሞት ትንቅንቅ ፣ ስቃይ፣ ረሃብ ፣ መገፋት፣ ጋር! ይሄንን የተኖረ ህይወት ሙሉ ለሙሉም ባይሆን በከፊል በዚህ ታሪካዊ መፅሀፍ እንዲሰነድ የበኩሌን አስተዋፅኦ በማበርከቴ ክብር የሚሰማኝ ለዚህ ነው። ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለኢትዮጵያችን ላደረጉት ሁሉ እናመሰግናለን!

Natnael Mekonnen

18,856 次观看 • 4 天前

NatnaelMekonne7's profile picture

የዩቱዩብ አቋራጭ የሽቀላ ስትራቴጂ መጀመሪያ በተባራሪ ወሬ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በድንገተኛ የቤተሰብ ሁኔታ (እህታቸው ድንገተኛ ሞት) አሜሪካ እንደገቡ ትሰማለህ። ከዚያ ይህንን ዜና እንዴት ወደገንዘብ መቀየር እንዳለብህ ታሰላስልና “የምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከሐገር ፈረጠጡ” ብለህ ሰፊ ዘገባ ትሰራና ብዙ View ታገኛለህ። ከዛ ሰውየው ሲመለሱ ውሸታም መባልህ ስለማይቀር ሽቀላህን ከጨረስክ በኋላ ሳይመለሱ በፊት ዜናውን በስህተት እንደሰራህ ትናገራለህ። (ሽቀላውም አልቀረብህም ውሸታምም አልተባልክም) ሶስተኛው Step ደግሞ Damage controlling ይባላል። “ሳታጣራ ለምን አወራህ መጀመሪያ?” የሚሉህ ሲመጡ አይንህን አፍጥጠህ ትመጣና “መረጃዬኮ ሙሉ ለሙሉ ስህተት አልነበረም። መቅረታቸውን እንጂ የዋሸሁት አሜሪካ መምጣታቸው ሃቅ ነው” ብለህ ሃጢአትህን በግማሽ ትቀንሳለህ። አራተኛው ደረጃ Victim blaming ይባላል። አንተው ዋሽተህና የሰውየውን ስም አጥፍተህ ስታበቃ ሃላፊነት ከመውሰድ ይልቅ እኚህን እሚያክሉ አዛውንት "እሳቸውስ ለምን ሲሉ በዚህ ሰአት አሜሪካ መጡ" ብለህ እንደህፃን ልጅ ትቆጣጠርና ጥፋቱን ሁሉ የሳቸው አድርገህ ሹልክ ብለህ ታመልጣለህ ማለት ነው። 😆 ይሄ ሁሉ ሚደረገው እንግዲህ ለዚያች የዩቱዩብ ሽቀላ ሲባል ነው ወገን። ፕሮፌሰሩ ከመጀመሪያም አሜሪካ እንደማይቀሩ ሰውየው ያውቀዋል። ነገር ግን ፕሮፌሰሩ ዘመድ ጥየቃ ከሐገር ወጡ ቢል ዩቱዩብ ላይ ብዙ እይታ አያገኝም “ኮበለሉ” ቢል ግን ዜናው ብዙ እይታ እንደሚያገኝለት ስለገባው በስማቸው እስከ 1000 ዶላር ሸቀለና እይታው እየቀነሰ ሲመጣ ሳይጋለጥ በፊት ራሱ መጥቶ ራሱ ላይ ግለ ሂስ አወረደ 😆 ለዚህ ሰውዬ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሽቀላ ናቸው ጎበዝ! ጣቃ ነጋዴ ለመሆን ተፈጥረህ በስህተት ፖለቲካ ውስጥ ስትገባ እንዲህ ነው ምታስበው።

Natnael Mekonnen

22,785 次观看 • 1 个月前

NatnaelMekonne7's profile picture

🇪🇹 ታላቅ ዜና ለኢትዮጵያውያን — የሕዳሴ ግድብ ታሪክ በዓለም መድረክ! 🌍⚡CNN የኢትዮጵያ ትልቁ የልማት ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD) ዛሬ የኢትዮጵያን የኃይል ዘርፍ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን የኃይል የወደፊት ተስፋ እየቀየረ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ሆኗል። CNN Africa በቅርቡ ባቀረበው ዘገባ፣ ጋዜጠኛዋ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ወደ ሕዳሴ ግድብ በመሄድ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት እንዴት ኤሌክትሪክ እያመነጨ እና የቀጣናውን የኃይል ገጽታ እየቀየረ እንደሚገኝ ተመልክታለች። ይህ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ዜና ነው። ምክንያቱም ሕዳሴ ግድብ የውኃና የኮንክሪት ግንባታ ብቻ አይደለም፤ የኃይል፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንዱስትሪ ልማትና የቀጣናዊ ትስስር ትልቅ መሠረት ነው። ⚡ በ2026 የተገለጹ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ፓወር መረጃዎችን የጠቀሱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፣ በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ካመነጨችው ከ35,670 GWh በላይ ኤሌክትሪክ 51.5% ያህሉ ከሕዳሴ ግድብ የተገኘ መሆኑ ተዘግቧል። የግድቡ የተገጠመ የማመንጨት አቅም 5,150 ሜጋዋት ሲሆን፣ በአማካይ በዓመት 15,700 GWh ያህል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የታቀደ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ነው። ይህ ኃይል ለቤቶቻችን መብራት ብቻ አይደለም። ለፋብሪካዎች፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድ፣ ለከተሞች፣ ለቴክኖሎጂ እና ለአዳዲስ የሥራ ዕድሎች መሠረት ሊሆን የሚችል ሀብት ነው። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን ከድንበር ባሻገር በመሸጥ የቀጣናው የኃይል አቅራቢ የመሆን ዕድሏን እያሳደገች ነው። ለምሳሌ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምትገዛውን ኤሌክትሪክ በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች መሆኗ በ2026 ተዘግቧል። ጎበዝ የCNN Africa ዘገባ ከአንድ የቴሌቪዥን ዘገባ በላይ ትርጉም አለው። ለዓመታት በዓለም ሚዲያ ሕዳሴ ግድብ ብዙውን ጊዜ ከውዝግብና ከዲፕሎማሲ አንፃር ሲዘገብ ቆይቷል። አሁን ግን ግድቡ ኤሌክትሪክ እያመነጨ፣ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ አቅም እየፈጠረ እና የቀጣናውን የኃይል ገበያ እየቀየረ ያለ ፕሮጀክት ተብሎ መታየቱ ራሱ ትልቅ ታሪክ ነው። የሕዳሴ ግድብ የአንድ ትውልድ ሕልም ከወረቀት ወደ ተጨባጭ የኃይል ምንጭ የተለወጠበት ምሳሌ ነው። አባይ አሁን ውኃ ብቻ አይፈስም — ኃይል፣ ተስፋና የልማት ዕድልም ይዞ ይፈሳል። 🇪🇹⚡ #ኢትዮጵያ #ሕዳሴግድብ #GERD #Ethiopia #GrandEthiopianRenaissanceDam #Africa #Energy #CNN

Natnael Mekonnen

21,265 次观看 • 1 个月前