#abiyahmed

NeaminZeleke's profile picture

ዛሬ በጠዋት ከ #አዲስአበባ ለረጅም ግዜ የማውቀው ሌላ ወዳጄ ደውሎ በአይኑ ያየውን፣ ወደ አካባቢው ሄዶ ያየውን ጆሮ ጭው የሚያደርግ፣ እንጀት የሚያኮማትር ጉዳይ ነገረኝ። #AbiyAhmed እና የኦሮሞ ብልጽግና የሚባለው የማህብረሰብ ዝቃጮች ጥርቃሞ በአዲስ አባባ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት የነውር፣ የኢ-ፍትሃዊነት፣ የአረመኔነት ጥግ ተግባራት መካከል እንዱን ብቻ የሚመለከት ነው ። ባለፉት ሁለት ቀናት በቦሌ “ፒኮክ መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የነበሩ ቤቶችን በሙሉ አፈረሱ፣ እንድ አዛውንት ራሳቸውን አጥፍተዋል፣ ሌላ ሰው ተገድሎአል፣ ፌደራል ፓሊስና የአዲስ አበባ ፓሊስ አካባቢውን በመውረር በርካታ ዜጎችን ደብድበዋል" አለኝ ። "ማነው ይህን ያስፈጸምው ብዬ ለጠየኩት ጥያቄ ፣ “ጥላሁን የሚባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር” ተብየው በማለት መለሰልኝ። “በአንድ ሳምት ውስጥ አካባቢውን ልቀቁ ተባሉ” ይህን ኢፍትሃዊ፣ ኢ-ህገ መንግስታዊ ውሳኔ "አቤት ለማለት ደርሰው ሲመለሱ ቤታቸው ፈርሶ ነው ያገኙት"። "ቦታው 200, 000 ካሬ የሚሆን እርሻ ነበር፣ እታክልትና ፍራፍሬ አምራች ቦታ፣ ሙሉ በሙሉ ጉራጌዎች ናቸው 61 ቤተሰቦች እንዳንዶቹ ከ 50 አመት በላይ በአካባቢው ሰፍረው አልምተው ፣ መተዳደሪያ ያደረጉ፣ ካርታና የስራ ፈቃድ ያላቸው ናቸው" ብሎ ነገኝ። "ዚጎችን አናፈናቅልም በማለት "ሌላም ሌላም ብሎ ድፍን የኢትዮጵያን ህዝብ የደለለው አረመኔው የበሻሻ ወሮበላ #አብይአሀድ “የኮሪዶ ልማት” ሊላው ገጽታ የሚያሳዩ መሰል ዘግናኝ አረመኔያዊ ድርጊቶች ሞልተው ፈሰዋል። በዜጎች ላይ የሚፈጨመው የማያባራ አረመኔያዊነት ስላቅና ቧልት፣ ይህ ብልጽግና የሚባል ወያኔ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው የማህበረስብ ዝቃጮች አራዊትነት እንደቀጠለ ነው። አላባራም ። በራሱ ተረት ተረትና ሃስት የሰከረው ፋሽታዊው #አብይ አህመድ ነጋ ጠባ የኮሪዶር ልማት በሚል አዲስ አበባን ለአረቦች ለመሸጥ፣ የኦሮሚያ ብልጽግና እና ክሮኒዎቹ፣ በድለላ ሀብት እንዲያካብቱ ማደበልብ ፣ በድሃ፣ አቅመ ደካማ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዞጎች የደም እምባ፣ የሚያፈሱበት፣ በርክታቶች ራሳቸውን ያጠፉበት፣ የብልጽግናው ቅጥፈት፣ እብደት፣ ክህደትና ሴራ የወለደው የአምስት ዓመታት የፊዳና የመዓት ኑሮ በኢትዮጲያ! የብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጲያን እያፈረሰ፣ ኢትዮጲያዊያንን ያጫረሰ፣ የኢትዮጲያን ስም ያስረከሰ፣ ሀገሪቱን ለኤምሬቶችና የራሱን ህልምና ቅዠት ስልጣን ለሚያራዝሙት ሆዳም ካድሬዎች የሸጠ፣ ደሃን የበደለ ፍትሕን ያጎዳለ አረመኔያዊ አገዛዝ ነው። ======================= ይህን አይን ያወጣ፣ ጥርስ ያገጠጠ አረመኔነት አንድ ጠበቃ ዛሬ ያስነበበውን እናንተም እንብቡት። Andualem Buketo Geda ይሄን ለጥፏል። ቅስም ይሰብራል! አርብ እለት ፒኮክ መናፈሻ አካባቢ አትክልት በማምረት ስራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦች እና ልጆቻቸው ቢሮዬ መጡ።'ሰፈሩ ለልማት ሊነሳ ነው እየተባለ ነው።ከወላጆቻችን ዘመን ጀምሮ በአካባቢው ለ73 አመታት ቆይተናል።ድንገት ተነሱ ብንባል ምን ይዋጠን!?' አሉኝ። 'መጀመሪያ የምትሄዱበትን ቦታ ማመቻቸት የመንግስት ግዴታ ነው።ያ ሳይሆን ለማስነሳት እንቅስቃሴ የሚደረግ ቢሆን ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርቤ እግድ እንዲሰጣችሁ አደርጋለሁ!' ብያቸው ተለያየን።ቅዳሜ ጉዳዩ የሚታይበትን አግባብ ሳዘጋጅ ዋልኩ።እሁድ ጠዋት ደወሉልኝ ።ከቤተክርስትያን ስንመለስ ቤታችን እየፈረሰ አገኘነው አሉ። ከባልደረባዬ ጋር ሄድን ።አይዟችሁ ብለን መትረፍ የሚችለውን ለማስቆም እንሞክራለን አልናቸው ።እስከ ማታ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት የህግ አቤቱታዎችን ስናዘጋጅ አመሸን።ሰኞ ጠዋት ኮሚኒቲው ህጋዊ የህብረት ስራ ማህበር ያላቸው በመሆኑ በማህበራቸው ስም ሊቀመንበሩ አቶ ዱላ ኑርጋ ውክልና እንዲሰጡን ተነጋገርን።ትላንት ከሰአት ሊቀመንበሩ የጠበቃ ውክልና ለመስጠት የማህበሩን የመመስረቻ ጽሁፍ ስላጡት ለማክሰኞ ጠዋት እንደሚሰጡን ተነጋገርን ።ዛሬ ጠዋት አቶ ዱላ ከቤታቸው ሲወጡ የማህበሩ አባላት ሰፈር ውስጥ ለማፍረሻ የመጣ ዶዘር ቆሟል።ሌሎች አባላቶች ለኛ ውክልና ለመስጠት ውልና ማስረጃ እየጠበቋቸው ነው።አብራቸው ከቤት የወጡትን ባለቤታቸውን ' መጣሁ እየሄድሽ ጠብቂኝ !' ብለዋት ወደ ቤት ተመለሱ።በአንዲት ቀጭን ሲባጎ እራሳቸውን አንጠልጥለው ተገኘ። ዛሬ ጠዋት 3:00 ላይ እኔ አቤቱታዬን ይዤ የአቶ ዱላን ስልክ ስጠብቅ ከሌሎች አባላቶች ተደወለልኝ።ከዛ ወዲህ ያለው ቢነገርም ጥቅም የለውም። ሰፈሩ መፍረሱ እና መልሶ መልማቱ ላይ ተቃውሞ የሌለውን ኮሚኒቲ በ2 እና በ3 ሰአት እያዋከቡ ማስወጣት መውደቂያውን ሳያውቅ ማሳቀቅ መጨረሻው ይሄ ነው። አቶ ዱላ ለ20 አመት በሊቀመንበርነት ያገለገሉትን ከ70 አመት በላይ በአንድ ቦታ የቆየውን ለፍቶ አዳሪ ማህበረሰብ 'ፌይል አደርጌያቸዋለሁ' ብለው እራሳቸውን አጥፍተዋል።እኔም ያንን ኮሚኒቲ ፌይል አድርጌዋለሁ።ትላንት አቤቱታውን ባስገባ ምናልባት ሊቀመንበሩ ከውሳኔው ይቆጠብ ይሆን?!ከጠዋት ጀምሮ በሰቀቀን ውስጥ ነኝ! ቀብራቸው ነገ ይፈጸማል! ነብሳቸውን ፈጣሪ ይቀበላት !!

Neamin Zeleke

43,191 views • 1 year ago

No more content to load