Loading video...

Video Failed to Load

Go Home

ብሄርተኝነት vs የዜጋ ፖለቲካ

16,258 views • 2 years ago •via X (Twitter)

0 Comments

No comments available

Comments from the original post will appear here

Related Videos

ዕብደት በህብረት ብሬ 😂 በኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ "ፖለቲካ ማለት" በሚል ርዕስ ከተካሄደው ውይይት ላይ የተወሰደ። "ድንቁርና ያስፈረኛል!'' ይል ነበር ታላቁ ባለቅኔ ሎሬት ፀጋየ ገብረመድህን ። የሀገራችን ውስብስብ ችግር የሚመነጨው ከትምህርት እጦት (ከድንቁርና) ነው ብንል አንሳሳትም። ዓለም የሰለጠነችው በእውቀት ሲሆን ፣ እውቀት ደግሞ የሚቀዳው ከትምህርት ነው። ኢትዮጵያ በየቀኑ እየታመሰች ያለችው በብሄር ፖለቲካ አይምሰላችሁ ። ከጀርመን የበለጠ ብሄርተኝነት አልነበረም ። ጀርመን ፅንፈኛ ብሄርተኝነቷን በትምህርት ልጓም ገራችው እና በለፀገች ። ጃፓን የብሄርተኝነት ግለቷን በትምህርት አቀዝቅዛ ከዛሬ እድገቷ ላይ ደረሰች ። ኢትዮጵያ ከህንድ በላይ ፣ ከናጀሪያ በላይ… ብዙ ብሄሮች ኖረዋት አይደለም በብሄር ፖለቲካ የምትንቀረቀበው ። የብሄር ፖለቲካዋ በብዙ ደናቁራት እየታመሰ ስለሆነ ነው። ፖለቲካ ሳይንስ መሆኑን አናስብም ። ሳይንስ በስሜት ሳይሆን በስሌት ፣ በመሰለኝ ሳይሆን በአመክንዮ ይመራል ። ሳይንስን የሚያብራራው ደሞ ጋሽ ትምህርት ይባላል። ኢትዮጵያ… ዋነኛው ማንሰላሰያዋ የትምህርት ተቋሟ ለዘመናት በመዳከሙ የተነሳ ለዘመናት በጦርነት ፣ በግጭት እና በርሃብ አለጋ ያለማቋረጥ እየተገረፈች ትገኛለች ። እውቁ ኢኮኖሚስት እንዲሁም ዝምተኛው እና አንሰላሳዩ ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሀገሩ ችግሮች ሁሉ ምንጩ የትምህርት ተቋሙ መቀጨጭ መሆኑን በደንብ ስለተረዳው ነው የኢትዮጵያን የትምህርት ሚኒስተርነት ማዕርግን ከገዥው ፓርቲ ተቀብሎ ሀገሩን በቅንነት እየገለገለ ያለው ። ፕሮፍ ፖለቲካን በእውቀት እንጂ በብሄር መነፀር አያየውም።እውቀት የጉራጌ ልጅነቱን ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ጋር አያጋጭበትም ። ገንዘብም ሆነ ስልጣን የእውቀት ሚዛኑን አላዛቡበትም። ከእውቀት ጋር ተጣልተው ከድንቁርና ጋር ተጣብተው የሚገኙ እንዳንድ ሰዎች በተለይ በማንነት ችግርና በፕሮፌሰሩ መንፈሳዊ ቅናት ምቀኝነት ያበዱ እንዳንዶች ስለ ብርሃኑ ብዙ ለማለትና ለማጠልሸት መክረዋል ፕርፌሰሩ ወይ ፍንክች አጅሬ መሆኑን ቢያቁም ተፍጨርጭረው ነበር አልተሳካም:: ፕሮፌሰሩ ከፓርቲያቸው ጋር አድርጉት ስለትባለው ቪዲዮ ላይ እውነት ለመናገር ፕ/ሮ ብርሃኑ ምን አለ? ፕሮፍ ምን አሉ? አንኳር አንኳር ሃሳባቸው: — *ታታሪው የጉራጌ ህዝብ፣ በብሄር ማንነት በተመሰረተ የጉራጌ ክልል በተባለ በረት ውስጥ መታጎር እንደሌለበት። * ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የብሄር ሳይሆን የዜጋ ፖለቲካ እንደሆነ * ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ህልማቸው በኦሮሞ ፖለቲካ ታጥረው መቅረት ሳይሆን በታላቋ ኢትዮጵያ ትልቅ አሻራ አስቀምጠው ማለፍ እንደሆነ ። * የወያኔን ፖለቲከኞች አሁንም ድረስ እንደሚጠየፏቸው እነዚህ ሃሳቦች ሀቅ ናቸው ። ነገሩን ግን ለማስጮህ የተደረገው ሙከራ ያሳዝናል::

Natnael Mekonnen

45,627 views • 2 years ago