Video yükleniyor...

Video Yüklenemedi

Ana Sayfaya Dön

ኃላ ቀርነትን በስራ እንቀይራለን

27,535 görüntüleme • 3 ay önce •via X (Twitter)

0 Yorum

Yorum bulunmuyor

Orijinal gönderinin yorumları burada görünecek

Benzer Videolar

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ከ20 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ዘመናዊ ተቋም ለላድረግ ምን መሰራት እንዳለበት የተናገሩት ንግግር ነው:: ፌደራል ፖሊስ አሁን ለደረሰበት ብቃትና ዘመናዊነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዛሬ 20 አመት ንግግርን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው:: ዝም ተብሎ ብሎ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አልተገባም:: በዕውቀት፣ በትጋት፣ በራዕይ እና በመሪነት ብቃት ነው አራት ኪሎ ቤተ መንግስት የሚገባው። በወቅቱ ከእሳቸው በዕድሜና በልምድ የሚበልጡ የመንግስት ኃላፊዎችን በማስተማር፣ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ አስተዳደር እውቀትን በማስረዳት እና ለሀገር ተቋማት ራዕይን በማስጨበጥ ሰርተዋል። በአጭሩ መልዕክቱ የሚለው፦ ስልጣን በወሬ፣ በሐሜት ወይም በጦርነት አይገኝም፤ እውነትን እና ተስፋን ይዞ በመስራት፣ በመማር እና በማስተማር ህዝብን በስራ በተግባር በማሳመን ነው ሀገር የሚመራው እና ትልቅ ኃላፊነት መድረስ የሚቻለው። እነ ጽንዶ ይሰማል? 👂የለም እውቃለሁ 👀 ታውሯል 🫡

Natnael Mekonnen

12,859 görüntüleme • 1 ay önce

አድማጭ ከሱማሌ ክልል አማራ ጥያቄ አለው ወይ? አዎ ብዙ ያልተመለሱና ያልተፈቱ ጥያቄዎች አሉት እዚህ ላይ ምንም ብዥታ ሊኖር አይገባም:: ግን የአማራው ጥያቄ በጦርነት በአመጽ ይፈታል ወይ? አይፈታም:: የእነ ሻለቃ ዳዊት አካሄድ ግን ከጦርነት አልፎ አማራውን በሌላው ብሔር ከንፈር እንዲመጠጥበ እያደረጉ ነው ያሉት:: አብዛኛው ሚሊዮን አማራ በስራ በንግድ በጋብቻ... ከክልሉ ውጪ የሚኖር ነው እንዴት ይሄን እያስቡም? የዛሬ አመት፣ ወያኔ በአማራ እና በአፋር ክልል እጨፈጨፈ፣ እየዘረፈ፣ እያወደመ ያን ሁሉ ግፍ ሲሰራ፤ ከአማራ ህዝብ አልፎ ሁሉም ህዝብ ላይ ይህን ግፍ ይሰራል ተብሎ ክተት ሲጠራ ነበር። ሁሉም በዚህ አምኖ ከየክልሉ በመትመም ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አማራንም ታድጓል። ታዲያ ዛሬ በግልፅ ሌላውን ብሄር እያጥላላና እየሰደበ፣ ኢትዮጵያ የእኔ ብቻ ናት በማለት ሻለቃ ዳዊት የተባለ የአማራ ግንባር መሪ ሽማግሌ ሲናገር ቁጭ ብሎ የሚታይ ያለ ይመስላቿል? የተከበረውን ሰፊውና ደጉ ሰው አክባሪው የአማራ ህዝብ ሆይ በማይወክሉ ተውሳኮች የክልሉን ማህበረሰብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለመለየት የሚያደርጉት ደባ አይሳካም:: ምክንያቱም ከህወሃት ትምህርት ወሰድን። ስለዚህ ሰላም ይሻላል። ከኢትዮጵያ ጋር ተላትሞ ያተረፈ የለም‼ ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላምለአማራ 🙏

Natnael Mekonnen

25,707 görüntüleme • 3 yıl önce

ጠቅላይ ሚኒስትሩ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ትናንት ማታ እንግዳ ተቀብለው ዛሬ ጠኋት ቄለም ወለጋ በመታየታቸው ብዙ ሰዎች ሲገረሙ ታዝቢያለሁ እስከማውቀው ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትንሹ በቀን ለ 16 እና 18 ሰአታት ይሰራሉ። ይህ በየቀኑ ነው አንዳንዴ እስከ 20 ሰአታት በስራ ላይ ናቸው:: ይሄንን አብረዋቸው የሰሩ ሁሉ የሚመሰክሩት ሃቅ ነው። (አቶ ገዱ ራሱ ቢጠየቁ ለማህተባቸው ይመሰክራሉ 😁) የኢትዮጵያ መከላከያ አመራሮችም በተለይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና ጀነራል አበባው ታደሠ ሌሎችም ጀነራሎች ክብርት ከንቲባዋን Adanech Abiebie ጨሮም ቀንና ለሊት እንደሚሰሩ አውቃለሁ። ገና አላሁ አክበር ሳይል ለሊት 10:30 ቢሮ ገብቶ ከለሊቱ ሰባት ሰአት ከቢሮ መውጣት በሰዎቹ ቤት ባህል እንደሆነ ባለችኝ አነስተኛ እድል ለመታዘብ ችያለው። በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመስራት በሳቸው የፍጥነት ልክ መሮጥ ብቻ ሳይሆን አንድ የመንግስት ሰራተኛ ከሚሰራው ሰአት ቢያንስ ሁለት እጥፍ ለመስራት ዝግጁ መሆን አለብህ። ይህንን ከሳቸው ጋር አብረው የሰሩ ቢያንስ አምስት ሰዎች ነግረውኛል። አንዳንዴ አብረዋቸው የሚሰሩ ሰዎች ቢሮ ለሰአታት ሲሰሩ አይተዋቸው እነሱ ቤታቸው ሄደው ቴሌቭዥን ሲከፍቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አንዱ ሐገር ሄደው የሆነ ፕሮጀክት ሲመርቁ አይተዋቸው ይገረማሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ ባህልና ጥብቅ Discipline አንዳንዴ ለሚሰማው ሰው ግነት ይመስላል። አብረዋቸው የሚሰሩት ግን ቀን በቀን የሚመለከቱት ጉዳይ ነው።

Natnael Mekonnen

17,868 görüntüleme • 6 ay önce

የመሪ ስነ-ልቦነናና ዶክተር አብይ! Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚህ 8 አመት የተፈተኑትን ያህል ባለፉት መቶ አመታት የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች እንዳልተፈተኑ እርግጠኛ ነኝ። ሶማሌ ክልል ከነበረው አመፅ ጀምሮ በየቦታው ሁን ተብልው የተለኮሱ የብሔር ግጭትና ጥቃቶች፣ በየቅያሱ የፈላው አማፂ ብዛት፣ ሰፋ ላለ ግዜ የተደረገው የትግራዩ ጦርነት፣ ጂኦፖለቲካው፣ የሶማሊያና የሱዳን አለመረጋጋት፣ የውጪ ሃይል ጣልቃ ገብነት፣ ወዘተ ተቆጥሮ አያልቅም። እውነተኛ መሪ የሚለካው በፈተናው ልክ ነው። ኖርዌይን የሚመራም ኢትዮጵያን የሚመራም በእኩል አይን መታየት የለበትም። ኢትዮጵያን መምራት አምስት የተረጋጉ ሐገራትን ከመመምራት ይበልጣል። አንድ መሪ በተቻለ መጠን ወታደራዊ ባክግራወንድ ቢኖረው ጥሩ ነው ይባላል። ሐገር በፈተና ስትናጥ ተረጋግቶ ውሳኔ መስጠት እንዲችል ወታደራዊ ስነልቦና የግድ ይላል። ኢትዮጵያን ከዩኒቨርስቲ እስክሪብቶ ብቻ ይዘህ ወጥተህ በቀላሉ የምትመራት ሐገር አይደለችም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባይሆኑ ኖሮ ሐገራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በገባች ግዜ ተረጋግቶ ሐገርን ማስቀጠል ለብዙ ሰው የሚቻል ነገር አይመስለኝም። የማርቆሱ የአውሮፕላን ማረፊያ የሚነግረን ይሄንን ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቡር አይቆምም። ጠላት እፏልልበታለሁ የሚልበት ምድር ሄደው ትልቅ ፕሮጀክት ተክለው መርቀው ይመለሳሉ። ሰላም በራቀበት ቦታ ሰላሙን ማስጠበቅ አንድ ነገር ሆኖ እዚያው ቦታ ላይ ፕሮጀክት ጨርሶ ሄዶ መመረቅ ሌላ አቅም ይጠይቃል። በሌሎች አካባቢዎችም፥ በተለይ የፀጥታ ችግር አለባቸው በሚባሉባቸው አካባቢዎች ልማቱ አልተቋረጠም፣ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው መሬት ላይ ይወርዳሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሚሰጡት በስራ ይመስላል። loud minority ዎች ድምፃቸው ጎልቶ ስለተሰማ በጫጫታ ሐገሩን የተቆጣጠሩ ይመስላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሃላቸው ሄደው አይናቸው እያየ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ፈፅመው በስራ ምላሽ ይሰጣሉ። ይሄን ለማድረግ “መሪ” መሆን ይጠይቃል። አሜሪካ በታሪኳ የከፋውና አገርን ለሁለት የከፈለ የእርስ በርስ ጦርነት (American Civil War) ውስጥ በነበረችበት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሚያልቁበት አስቸጋሪ ወቅት። በግዜው መሪ የነበረው አብርሃም ሊንከን ጦሩን እየመራ የአሜሪካን ምሥራቅና ምዕራብ ጫፎችን የሚያገናኝ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ማይሎችንና አስቸጋሪ ተራሮችን የሚያቋርጥ ግዙፍ አህጉር አቋራጭ የባቡር መስመር (Transcontinental Railroad) እንዲጀመር አዘዘ። በግዜው ብዙዎች “አበደ” ብለውት ነበር። ሰላሙ ይቅደም ያሉም ነበሩ። እንዴት አሜሪካ ትሰንብት አትሰንብት ሳያውቅ እንዲህ አይነት እቅድ ያወጣል ያሉትም እልፍ ናቸው። ሊንከን ግን ጦርነቱን እየመራ በነበረበት በዚያ አስጨናቂ ወቅት፣ የባቡር መስመሩ የወደፊትዋን የተባበረች አሜሪካ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ተገንዝቦ ነበርና ከአቋሙ ዝንፍ አላለም። በ1862 (ጦርነቱ በሃይል በተፋፋመበት ወቅት) ህጉን አጽድቆ፣ በገንዘብ እጥረትና በጦርነት ግርግር ሳይበገር ፕሮጀክቱ እንዲቀጥል ማድረግና አሜሪካን ማስተሳሰር ችሏል። ትክክለኛ መሪ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ነገውን ይሰራል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም እንዲሁ ዛሬን ሳይሆን ነገን ማየት የሚችሉ መሪ ናቸው። እንደውም አንድ ግዜ ውሃዋን በብርጭቆ ይዞ አካባቢው ባለው ነገር Diatracted ሳይሆንና ውሃዋን ሳያጎድል ከግቡ ያደረሰውን ሰው ታሪክ ተናግረው ነበር። ያ ሰው እራሳቸው ዶክተር አብይ ይመስሉኛል። ለማንኛውም እኔና ቤቴ ነውጥ በሚመስል ግርግር ውስጥ ለማይናወጡት መሪ እጅ እንነሳለን!

Natnael Mekonnen

12,401 görüntüleme • 1 ay önce

ነሃሴ 2016 አብይ አህመድ በገዛ ወሬው የስከረ መሪ። የሚገርም ዘመን፣ ከዋናው የሃገር መሪ እስከ ተራው ካድሬ ምንም አይነት የሞራል ኮምፓስ የሌላቸው፤ የሞራል ልጓማቸው የተበጠሰባቸው ሆነዋል። የኢትዮጵያ ጉዶች ። እንዳንዴ ለእነዚህ ሰዎች አጓጉል ንግግር መልስ መስጠት እንደነሱ መሆን ነው በሚል ስጋት ዝምታ መምረጣችን የራሳቸውን ቅጥፈት እንደእውነት በመውሰድ በእብደት ህዲድ እንዲነጉዱ ከማድረጉ በላይ የእነሱን መበጥረቅ (ከኮሜዲያን እሸቱ መለስ የተማርኩት ዘመኑን የዋጀ ቃል) ጥቂቶችንም ቢሆን ማወናበዱ ስለማይቀር፣ ሁሌም ባይሆን አልፎ አልፎ የተመዘነና በቅጡ የታሰበበት ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ለዚህ ነው እየታከተኝም ቢሆን አልፎ አልፎ ብእሬን የማነሳው። 1. ሀተታ ላለማብዛት አጠቃላይ ከሆነው የሃገር ሁኔታ ልጀመር፤ “ኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነቷን እና ጥቅሟን የሚያስጠብቅላት መንግስት የላትም። መንግስቷ በአንድ በራሱ ምስል በስከረና ባበደ አደገኛ ግለሰብ እጅ ወድቋል። ይህ በራስ ምስል አምልኮት የአእምሮ በሽታ የተጠቃ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ ካልተነሳ ኢትዮጵያና ህዝቧ ብሄራዊ ደህንነታቸው፣ ጥቅማቸው፣ ሰላማቸው ብልጽግናቸው አይረጋገጥም ስንል ዝም ብለን እንደ አብይ አህመድ፣ እየተበጠረቅን አይደለም። ኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ መሰረት አድርገን ነው። አብይ አህመድና ደንገጡሮቹ ግን ይህ ማየት ከማይችሉበት የተዘጋ የአእምሮ ውቅር ወይም ህሊና ገንብተው ተቀምጠዋል። መስማት ብቻ የሚፈልጉትን እየሰሙ፣ ማየት ብቻ የሚፈልጉትን እያዩ፣ ማመን ብቻ የሚፈልጉትን እያጠለሉ እያመኑ እንዲኖሩ ያደረገ፣ እውነታን በካደ የቅዥተ አዙሪት ውስጥ ወድቀዋል። እንደማይሰሙን ብናውቅም እስኪ ጥቂት እንበላቸው። ዝምታችን ለእብደታቸው የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ መፍቀዱ እኛንም ተባባሪ ያደርገናልና። የአንድ ሃገር ብሄራዊ ደህንነት ጥቅም የሚከበረው በመከላከያ ሰራዊቱ ነው። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ሰራው ዳር ድንበርና ሉአላዊነት ማስከበር መሆኑ ቀርቶ የአንድ ግለሰብ ስልጣን ለማስጠበቅ ሲል ከመላው የሃገሪቱ ህዝብ ጋር ተራ በተራ ወይም በአንድ ጊዜ ሲዋጋ መኖር፤ የገዛ የሃገሩን ልጆች መግደልና በነሱም መገደል እጣው ከሆነ ሰነበተ። ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ዳር ድንበሯ ተደፍሮ፣ መሬቷ በውጭ ሃሎች እጅ ተይዞ ይህን ማስቆም የሚገባው የመከላከያ ተቋም መሳሪያውን፣ የሰው ሃይሉንና መሉ ጉልበቱን በኢትዮጵያውያን ፍጅት የአንድን ግለሰብ የስልጣን ሱስ ለማርካት በስራ ላይ እንዲያውል ተደርጓል። የሰራዊቱ ጄነራሎች ለዚህ ታማኝነታቸው ቢሸጡት እስከ 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሬት ታደሏቸዋል፣ የሃገር ወርቅ ከየክልሉ መሪዎች ጋር በመሻረክ እያስቆፈሩ ከሃገር ውጭ ያወጣሉ፣ መሳሪያና መረጃ ለአልሸባብ ሳይቀር ይሸጣሉ፣ የግንባታ የንገድ ድርጅቶች፣ ከህንዶችና ከቻይኖች ጋር አቁመው ከሪል እስቴት አለፈው መለስተኛ ግድቦች ይገነባሉ። ለመከላከያ ከተመደበው ግዙፍ ባጀት የሚዘርፉትን እዚህ ላይ ማከል ነው። ሌላው የአንድ ሃገር የብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም አስከባሪ ተቋም፣ የመረጃ የደህንነት ተቋሙ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ተቋም እንደተቋም መስራት ካቆመ ሰንብቷል። በሃሰት የትወልድ፣ የትምህርትና የማነንት መታወቂያ ማስረጃ፣ በዘመድ አዝማድ፣ በምልጃና በጉቦ የሚቀጥራቸውን ሰዎች እውነተኛ ማንነት መስሪያ ቤቱ ከማያውቅበት ደረጃ ላያ ደርሷል። ግለሰቦች በጠላት ሃገራት መንግስታትና ድርጅቶች ተመልምለው፣ በተቋሙ ውስጥ መተከላቸውን ወይም ከሰራተኞቹ መሃል ለጠላት ተመልምለው የሚሰሩ ከሃዲዎች እንዳይኖሩ የሚከታተል፣ በደህንነቱ መስሪያ ቤት ላይ የስለላ ስራ የሚሰራ ጸረ መረጃ የተባለው ክፍል ከደህነነት ተቋሙ ከጠፋ ስንብቷል። በዚህም የተነሳ አልሸባብ ወኪሎቹን በኢትዮጵያ የመረጃ መስሪያ ቤት አስቀጥሮ መረጃ መዝረፍ የቻለበት ሁኔታ ተከስቷል። ከመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች መሃል ምን ያህሉ አሁንም ለኢትዮጵያ ጠላቶችና መረጃ ለሚፈለጉ ሌሎች ተቋማት እንደሚሰሩ፣ መረጃ እንደሚሸጡ አይታወቅም። የመረጃ መስሪያ ቤቱ ከሱማሌው አልሸባብ እስከ ናይጀሪያው ቦኮ ሃራም አባላት የኢትዮጵያን ፓስፖርት በማደል በሃሰተኛ ስምና መረጃ በኢትዮጵያ ፓስፖርት በአለም ላይ መንቀሳሰ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥሯል። ቀደም ብሎ ይደረግ የነበረው ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ የግማሽ መንፈቅ የመረጃ መስሪያ ቤቱ ግምገማዎች አይደረጉም። እቅዶችም የሉም። የሃገር አደጋ ትነተና አይቀርብም። የመረጃ ስራ የ24 ሰአታት ስራ መሆኑ ቀርቶ እንደማንኛውም መስሪያ ቤት ከሰአት በኋላ የስራ ሰአት 11 አንድና 12 ሰአት ላይ ሲያበቃ አብሮ ይቆማል። ከተማውና ሃገሪቱ በምሽት ያለደህንነት መስሪያ ቤቱ ክትትልና ቁጥጥር አድረው ይነጋላቸዋል። ሲመሸ የደህንነት መስሪያ ቤቱ የስራ ድርሻ በየጭፈራ ቤቱ እየዞሩ ባለቤቶቹን እያስፈራሩ መጠጣትና እንደማፍያ አለቆች የከለላ ክፍያ (protection fee) መሰብሰብ ሆኗል። የመስሪያ ቤቱ አለቆች በከፍተኛ ደረጃ የሚናናቁ፣ እርስ በርሳቸው የማይነጋገሩ፣ ሁሉም በግልና በቀጥታ ለእብዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ወሬ አቀባዮች ሆነዋል። የመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ሙሉ ጊዚያቸውን እንደ መከላከያ ጀነራሎች በግል ሃብት ማካበቺያነት፣ የሃገርና የህዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የሚያወሉ ሆነዋል። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ልክ እንደ ወታደራዊ ጀኔራሎች በአለቃቸው በአብይ አህመድ እየታወቀ ነው። ታማኝ እስከሆኑ በየትኛውም የዘረፋ ስራ እንዲሰማሩ ፈቃድ ሰጥቷቸዋል። በርካታ ማስረጃዎች አሉን። ሌላው የሃገር ደህንነት ጠባቂ ተቋም የፌደራል ፖሊስ ተቋም ነው። ይህ የፌደራል ፖሊስ ተቋም እየከረረ በሄደ የዘር ክፍፍል የተወጠረ፣ ተቋማዊ አንድነቱ የተናጋ ነው። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በተለይ የአማራ ተወላጅ አባላቱ (የትግራይ ሰዎች ከመስሪያ ቤቱ ውስጥ ከጠፉ ቆይቷል) መሳሪያቸውን እንደያዙ የሚከዱበት ሁኔታ የተስፋፋበት ተቋም ነው። መሪዎቹ ከአደገኛ እጽ አንስቶ እስከ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ ውስጥ የተደፈቁ መሆናቸው ተደጋግሞ የተገለጸ ጉዳይ ነው። ባለፈው ሳምንት አብይ አህመድ ኮማንደር ፍቅሩ አለማየሁ ለሚባል የአዳነች አበቤ አጃቢ ለነበረ ግለሰብ በቀጥታ በምክትል ኮሚሽነርነት ማእረግ የአዲስ አበባ የወንጀል መከላከል ሃላፊ እንዲሆን የስጠው ሹመት “የዘር ኮታ ምደባውን የተጻረረ፣ የአማራን ቦታ ለኦሮሞ የሰጠ ነው” በሚል በተቀሰቀሰ ቁጣ 16 ዝቅተኛ መኮንኖችና ፖሊሶች እኛን አማሮችን በእዚህ ተቋም ውስጥ የሚወከለን የለም በሚል ምሬት መሳሪያቸውን ይዘው መሰወራቸው ታውቋል። የፌደራል ፖሊሲ ሃላፊዎች ዋናው ስራቸው በአብይ አገዛዝ ላይ ህዝብ እንዳያማጽ ከመጠበቅ ውጭ በሃገር ብሄራዊ ጥቅምና ደህነት ዙሪያ ከታዬ ዋናዎቹ የሃገር ጠንቆች ከሆኑ ሰነባብቷል። ሌላው የሃገር ጥቅምና ደህነነት ማስጠበቂያ ተቋም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱና የዲፕሎማሲ ስራው ነው። ይህን መስሪያ ቤት በአብይ ተላላኪዎች ከመሞላት አልፎ የአብይ አህመድ የግል ፍላጎት ማስፈጸሚያ ከሆነ ቆይቷል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከታዬ አጽቀስላሴ በላይ ተሰሚነት ያላት ምክትሉ ብርቱካን አያና ናት። አምባሳደሮች የሚያደገድጉት፣ የተሻለ ምደባ እንዲያገኙ ጉቦና ስጦታ የሚሰጡት ለዚች የአብይ አህመድ የቅርብ ሴት ነው። የአብይ አህመድ እብደት በሚገባ የተገለጸበት፣ የሃገርና የህዝብ ደህንነትና ጥቅም ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት የመንግስት እንቅስቃሴ ቢኖር የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ ነው። በተሳሳተ የአብይ አህመድ የውጭ ጉዳይ እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ተጣልታለች። ማንም በበጎ አይን የሚያያት የለም። ምንም ደሃ ብትሆን በቀጠናውና በአለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎምሲ መስኩ ትታይበት የነበረው የላቀ ስፍራዋ ላይ ዛሬ የለችም። ኢትዮጵያ ለደረሰባት ጉዳት ብዙ ምሳሌ ማቅረብ ቢቻልም ከሱማሌላንድ ጋር አብይ ገባሁ ያለው በቅጥፈት የተሞላ፣ ገና ከመጀመሪያ የትም እንደማይደርስ የተነበይነው የመግባቢያ ሰንድ ፊርማ ትልቁ ምሳሌ ነው። ሰነዱ በተፈረመበት ወቅት “ለሃገር ደህንነት አደገኛ ውሳኔ ነው” ብለን የተቃወምነው ግለሰቦች፣ አብይና አሽቃባጮቹ እንዳሉት ሃገር ሲያልፍላት አይናችን የሚቀላ ባናዳዎች ስለሆን አልነበረም። ይህን የሚሉት የባንዳነት ታሪክ በዘር ማንዘራችን እንደሌለ አጥተውት አይደለም። የሱማሌን ሉአዋላዊ ሃገርነት የሚጻረር ድርጊት በኢትዮጵያ ላይ ብዙ መዘዞች ያስከትላል ከሚል ተጨባጭ ስጋት በመነሳት ነበር ስምምነቱን ያወገዝነው። ለአንድ ሰሞን ህዝብን የማወናበድና የማፋዘዝ ፕሮጀክት ሲባል የተፈጸመ ድርጊት ኢትዮጵያ ሰራዊቷን ከሱማሌያ የምታስወጣበትን፣ አልሸባብ ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ካምፕ የመሰረተበትን፣ ግብጽ በኢትዮጵያ ድንበር ሱማሌ ውስጥ ወታደሮቿን ማስፈር፣ የሱማሌን ሰራዊት ማሰልጠን የምትችልበትን፣ ቱርክ የሱማሌን የባህር ዳርቻዎች ደህንነት የምትጠብቅበትን ውሎች ከሶማሊያ ጋር መዋዋል የቻሉበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል። ህዝብ ለህዝብ መቀራረብ ጀመሮ በነበረው የኢትዮጵያና የሱማሌ ህዝብ ግንኙነት ላይ ያደረሰው ጉዳት ቀላል አይደለም። የመከላከያ የደህንነት ተቋማቷን አፍርሳ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ መስኩ የሃገሪቱን ጥቅም ተጻረው ለሚቆሙ ሃገራትና መንግስታት፣ እድሜ ለአብይ አህመድ፣ የተመቻቸ ሁኔታ ፈጥራ አርፋዋለች። ሌላው የአንድ ሃገር ሉአላዊነት፣ደህነነትና ጥቅም ማስከበር የሚችለው ሃይል ከህዝብ አንድነትና በህዝብና በመንግስት መቀራረብ የሚገኘው ጉልበት ነው። የአብይ አህመድ አገዛዝ ሆን ብሎ የሃገሪቱ ህዝቦች እርስ በርስ በጎሪጥ እንዲተያዩ፣ ከዛም አልፈው እንዲጨፋጨፉ የሚሰራ መንግስት ሆኗል። በአብዛኛው የሃገሪቱ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ ተጋጭቷል። አሁንም እየተጋጨ ነው። ከጦርነት በተረፈው ህዝብ ላይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚል ስም የኢኮኖሚ ጦርነት ከፍቶ፣ ከጥቂት ባላሃብቶችና የመንግስት ባላስልጣናት በቀር የእያንዳንዱን ዜጋ ህይወት የምድር ሲኦል አድርጎት አርፏል። አብይ በፈጸማቸው ዘርፈ ብዙ ጸረ ህዝብ ድርጊቶቹ ከህዝብ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኗል። ከሃገሪቱ የቆዳ ስፋት የሚቆጣጠረው እየጠበበ ሄዶ አገዛዙ እንደለቡ ያሻወን መፈጸም የሚችልበት ቦታ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሆኗል። አብይ አህመድ ህዝብንም ከሃገር ደህንነትና ጥቅም ማስጠበቅ ስራ አግሎታል። ኢትዮጵያ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ናት የምንለው ይህን ሁሉ ጉድ አይተን ነው። 2. ወደ ውቅታዊ ጉዳይ ስመለስ አብይ አህመድ የጫካ ቤተመንግስት፣ የኮሪደር ልማት፣ አዲስ ቱሞሮ (ጥራዝ ነጠቅ ስትሆን የሚመጣ የእንግሊዝኛ አጠቃቀም) እያለ የአልሞትኩም ብዬ አልዋሽም ፕሮፓጋንዳውን እራሱ እየሰራ፣ እራሱ እየተጋተ ሰከሮና ደንዝዞ መኖርን መርጧል። ይህን ድርጊቱን አያዋጣም የምንለውን በወሬ የምንኖር እራሱን በስራ የሚኖር አድርጎ መግለጽ ደግሞ የሰሞኑ የፐሮፕጋንዳ አቅጣጫው ሆኗል። ከዚህ ቀጥሎ የምላቸው ጥቂት ቃላቶች የአብይ አህመድ የሰሞኑ ጭኸቶች የቁራ ጭኸቶች እንደሆኑ የሚያሳዩ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልገባው እሱ የያዘው ስልጣን በአንዳንዶቻችን እጅ ቢገባ ለጫካ ቤተመንግስቱ አዲስ አበባ ላይ የሚያጠፋውን ከ10 እስከ 15 ቢሊዮን የሚደርስ ዶላር ከሱ በተሻለ ሃገርና ህዝብን ወደከፈተኛ ብልጽግና መውሰድ የሚያስችል ስራ ማዋል የሚችሉ ልጆች ኢትዮጵያ እንዳሏት ነው። አብይና አሽቃባጮቹን በምክን ያት ተከራክሮ ማሳመን እንደማይቻል በገባንም በህዝብ ፊት ማሳፈር ስለሚቻል 10 ቢሊዮን ዶላሩን እንዴት እንደምናጠፋው ቀጥሎ እናቀርባለን። 10 ቢልዮን ዶላሩን ምን እናደርገው እንደነበር ስንነግራችሁ የጫካው ቤተመንግስት፣ በግንባታ ወቅት የሚቀጥረውንና ከተገነባ በኋላ ስራ የሚፈጥርለትን የሰው ብዛት፣ ግንባታው ሲያልቅ የሚያስገኘውን የኢኮኖሚ ጥቅምና ሃገራዊ ፋይዳ በሚገባ ተመልክተን ነው።ዝርዝሩን ማቀረብ ያለበት አብይና ኩባንያው ነው። እኛ ማድረግ የምንችለው እንዲህ አይነቱ የጫካ ቤተመንግስት ኢንቨስትመንት ቱሩፋቶቹ ምን ይሆናሉ ብለን በመገመት ብቻ ነው። በተለይ ይህን ያህል ዶላር የፈሰሰበት ቤተመንግስት ሰላምና መረጋጋት በሌለበት ሃገር ቀርቶ ሰላም ቢኖርም ክወጭ የሚስበው ጎብኝ ይሁን በዚህ ቤተመንግስት ዙሪያ የሚገነቡ ህንጻዎች የሚስቡት የውጭ ኢንቨስትመንት እዚህ ግባ የሚባል የኢኮኖሚ ፋይዳ እንደማይኖር የታወቀ ነው። በግንባታ ስራውም ሆነ ካለቀ በኋላ የሚፈጥረው የስራ እድል ውሱን ነው። እንግዲህ ይህን አይነቱን በሃገራችን ከሚሰሩ ስራዎች ቅደም ተከተሉ እጅግ የተዛናፈን የዛሬ መቶ አመት እንኳን ሊሰራ የማይገባውን ስራውን እያመላከተ ነው አብይ አህመድ የስራ ሰው መሆኑን ሊነግረን የሚዳዳድው። እኛ ደግሞ ይህን በጫካ ቤተመንግስት ላይ አብይ አህመድ የሚያወጣውን ከ10 እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር፣ በ10 ቢሊዮን ዶላር ገድበን ይህን ገንዘብ በሀሃገራችን ውስጥ ቅድሚያ ማግኘት አለባቸው ከምንላቸው ስራዎች አንዱ በሆነው የማዳበሪያ ኢንደስትሪ ምስረታ ላይ እንዴት እንደሚውልና ምን ሃገራዊ የኢኮኖሚ እርባና እንደሚኖረው በማሳየት አብይ የወሬ እንጂ የስራ ሰው አለመሆኑን ማሳየት እንችላለን። የማዳበሪያ ኢንደስትሪ ራሳችንን በምግብ ለመቻል፣ ከዛም አልፎ ግብርናውን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ አብዮት ለማስጀመር፣ በግብርና ምርታቸን ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ችግራችንን መቅረፍ የምንችልበት እድል ለመፍጠር፣ በግንባታው ወቅትና ከተገነባ በኋላ የሚቀጥረውን የቋሚ ሰራተኛ ብዛት፣ ኢንዱስትሪው ራሱ የሚያመርተው ምርት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ተርፎ ወደ ውጭ ከሚላከው ምርት የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ ገቢ በአንድ ላይ ግምት ወስጥ አስገብተን የአብይን 10 ቢሊዮን ዶላር በማዳበሪያ እንዱስትሪ ምስረታ ላይ ብናውለው ምን ውጤት እናገኝ ነበር የሚለውን ጉዳይ ለአብይ አህመድና በዙሪያው ላሉ አሽቃባጮቹና በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን እናስውባለን በሚልፕሮፓጋንዳቸው ሊያደነዝዙት የፈለጉትን ህዝብ የሚከተሉትን ሃቆች እንንገራቸው። አብይ አህመድ ጫካ ቤተመንግስት የሚገነባባትን ገንዘብ ወደ ማዳበሪያ ኢንደስትሪ አዙሮት ቢሆን። 1. ለማዳበሪያ መስሪያ አስፈላጊ የሆነወን አሞኒያ የተባለ ኬሚካል በአመት በብዙ ሚሊዮኖች ሜትሪክ ቶን ማምረት ይቻል ነበር። 2. ለማዳበሪያ መስሪያ አስፈላጊ የሆኑትን ፎስፌትና ፖታሸ 1 እስከ 2 ሚሊየን ሚትሪክ ቶን በአመት ማምረት ይቻል ነበር። 3. ይህ የማዳብሪያ ኢንደስትሪ ኢትዮጵያ በአመት ለማዳበሪያ የምታወጣውን ከ800 ሚሊዮን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያሰቀር ነበር። 4. በውጭ የማዳበሪያ ኩባንያዎችና መጓጓዣዎች እንዲሁም በየጊዜው ከሚዋዥቅ የማዳባሪያ ዋጋ ራሷን ነጻ ማድረግ ትችል ነበር። 5. ዘመኑ የሚፈቅደውን የተራቀቀ ቴክኖሎጂ በማደበሪያ ማምርቻ ስራ ላይ ማዋል ትችል ነበር። 6. ይህ ዶላር በጥናትና ምርምር ላይ የተመስረተ ከማዳበሪያ ጋር የተያያዘ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የጥናትና የምርምር ተቋም እንዲኖረን ያስችል ነበር። 7. ለተፈጥሮ እና ለአካባቢ ጥበቃ እንብካቤ የሚያደርግ ኢንደስትሪ መገንባት የሚያስችል አቅም ይሰጠን ነበር። 8. በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች፣ ኤንጂኔሮች፣ ኬሚስቶችም የፋብሪካ ማሽነሪ አንቀሳቃሾች፣ የማእድን ሰራተኞች፣ የድጋፍ ስራ የሚሰሩ ሌሎችንም በመቶ ሸዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስራ ያስገኝ ነበር። 9. የማዳበሪያው ኢንደስትሪ ትልቅነት የአለምን የማዳበሪያ ገበያ ከ5 እስከ 15 በመቶ የመቆጣጠር ትልቅ አቅም ሰለሚኖረው ኢንቨስትመንቱ ከኢትዮጵያ ውጭ በሌሎች ሃገሮች ሳይቀር መስሪያ ቤቶች የሚኖሩትና ሰራተኞችም የሚቀጥር ይሆን ነበር። 10. ኢትዮጵያ ለማደባሪያ መስሪያ የሚሆን ትልቅ የፖታሽ ክምችት ቢኖራትም፣ ለፖታሽና ለሌሎችም ለማዳበሪያ መስሪያ የሚሆኑ ወሳኝ ግብአቶችን ሩቅ ሳትሄድ ከጎረቤቶቿ ማግኘት የምትችልበትን የኢኮኖሚ ትብብር እድል የሚከፈት ይሆን ነበር። ከኤርትራና ከጅቡቲ ጋር ፎስፌትና ፖታሽ በማውጣት፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከሱዳን ናይትሮጂን ለሚያስፈለገው የአሞኒያ ማዳበሪያ ለመስሪያ የሚሆነው የተፈጠሮ ጋዝ በመግዛት የሚፈጠረው የኢኮኖሚ መደጋገፍ ለቀጠናው ትልቅ ትርጉም ይኖረው ነበር። 11. ጥናቶች የሚያሳዩት በ10 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት የሚጀመር የማዳበሪያ ኢንደስትሪ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምርት ሲጀመር ከ 5 ቢሊዮን እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ አመታዊ ገቢ ሊኖረው የሚችል ይሆናል፣ ከዚህ ውስጥ ትርፉ በየትኛውም ኢንደስትሪ ከሚገኝ ትርፍ የላቀ እንደሚሆን ይገመታል። 12. ይህ ስራ ለማስጀመር • የአሰሳና የአዋጭነት ጥናት ለማጥናት ከ50 እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር፤ • የመስረተ ልማት ስራ ትልቁ ነው። የማእድን ማውጫ መሳሪያዎች፣ የማጓጓዣ ስራ፣ የኤነርጂ አቅርቦት፣ የውሃ አቅርቦት ስራ ከ500 ሚሊዮን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚኖረው ይገመታል። • ማእድን ማውጣትና ማጣራት ማምረት ፋብሪካዎችን ማቆም ከ 1 ቢሊዮን እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ ይገመታል። • ለሎጂስትክ ለሃገር ውስጥና ወደ ውጭ ማጓጓዣ ከ300 ሚሊዮን እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር፤ • አመታዊ የሰራተኛ ደሞዝ፣ የጥገና የመለዋወጫና ሌሎችም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ መንቀስቃሰ እሰክሚችል ድረስ የሚያፈልገው ወጪ ከ 200 እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር ይሆናል። አጠቃላይ የአንድ ትልቅ የማዳበሪያ ፋብሪካ የኢንቭስትመንት ወጪ ከ2 ቢሊዮን ዶላር እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል። ስራው አድካሚ ነው። በትንሹ አምስት አመታት ጊዜ ይወስዳል። እንደ ኮሪደር ልማት፣ እንደ ጫካ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ቤተመንግስቱ አካባቢ ለአብይ አይን ማረፊያነት የሚሰራ አይሆንም። አብይ ጠዋትና ማታ የሚጎበኘው፣ ውጤቱም በሚብለጨጩ ህንጻዎች በቀላሉ የማይታይ ስራ ነው። እንግዲህ ይህ ቁልፍና መሰረታዊ የሆነ የሃገርና የህዝብ ትልቅ ችግር ለመቅረፍ የሚያስፈለግ፣ ከዛም አልፎ በየአመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘትና ከፍተኛ ቁጠር ያለውን ቋሚ ሰራተኛ ለመቅጠር የሚያስችል አንድ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ከ 2 እስከ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ ከሆነ፣ የጫካው ቤተመንግስት በሚሰራበት በ 10 ቢሊዮን ዶላር በአማካይ 3 ትልልቅ የማዳበሪያ ኢንዱስትሪዎች መገንባት ይቻል ነበር ማለት ነው። ይህን ኢንደስትሪ ለጫካው ከሚወጣው ወጪና የጫካው ፕሮጀክት ለሃገርና ለህዝብ ከሚሰጠው ፋይዳ ጋር ማነጻጸሩና የፋይዳወን ልዩነት የመገመቱ ስራ ለብልሁ የኢትዮጵያ ህዝብ እንተወዋለን። የአብይ አህመድ አገዛዝ የሀገር ጠንቅ ነው። ብልጭልጭ ፕሮጀክቶቹም የግለሰቡን ብኩን ስብእና የሚያሳዩ ናቸው የምንለው፣ በበልጽግና ዙሪያ አብይ እንደሰበሰባቸው የፓርቲው ደናቁርትና እነሱን እንዲያጅቡ አብይ ስልጣን ያጋራቸው እንደብርሃኑ ነጋ እንደ ግርማ ሰይፉ እንደነ በለጠ ሞላ ከአብይ እግር ስር እየወደቀን ጭራችንን የማንቆላው፣ በዘራችሁ አይድረስ ከሚል የመዋረድ እርግማንም ራሳችንን የምናድነው ጌታቸውና ፈጣሪያቸው አብይ እንደሚለው በወሬ ስለምኖር ሳይሆን፣ ለግል ስማችን፣ ክብራችንና ሆዳችን ሳይሆን ሃገርን የሚጠቅምና የሚጎዳ ተግባር ምን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው። ይች በድህነት የተጨማደደች ሃገራችን እና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ደሃ ህዝባችን ወደ ብልጽግና የሚያመራው ጥቂት ከተሜዎችና ዳያስፖራዎች፣ አብይ እንዳለው ፎቶ መነሳት የሚችሉባቸውን ቦታዎች አዲስ አበባ ላይ ለመፍጠር ሲባል ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን በከንቱ በማባከን እንዳልሆነ ስለምናውቅ ነው። የከተማወን ህዝብ ረሃብ ለማስታገስ ማዳበሪያ ያለውን ትርጉም ስለምናውቅ ነው። ልኡላዊነትን አሳልፎ የሸጠ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስራ ላይ እንዳናውል የሚያደርገንን፣ ከፍተኛ የሆነ የወጭ ምንዛሪ ፍላጎታችንን የሚቀንስ፣ ኢንደስትሪው ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝልን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው። ግብርናን መሰረት ያደረገ የኢንደስትሪ አብዮት በማካሄድ አስተማማኝ ልማት ለህዝባችን ማጎናጸፍ እንደሚችል ስለሚገባን ነው። የአብይ አገዛዝ ያለበት ችግር በእውነት፣ በሃቅ፣ በእውቀት ላይ ተመስርተው ስካርና እብደቱን ከሚያመላክቱት ሰዎች ይልቅ እሱ የሚለውን እንደገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ፣ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር እንደተዋወቀች አይና አፋር ለጃገረድ የሚሽኮረሞሙ ወራዶችን ማቅረቡ ነው። ከእነዚህ ሰዎች መሃል እኔ በግሌ የማውቃቸው በአንድ ወቅት ትልቅ ክብርና ግምት የሰጠኋቸው ሰዎች መገኘታቸው ነው፤ “እንዲህ አይነት ውርደት በዘራችሁ አይድረስ” እንድል ያሰኘኝ። አንዳርጋቸው ጽጌ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 FDRE Government Communication Service Mustafe M. Omer Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ Ethiopian Reporter Sahle-Work Zewde Reuters Ethiopian Citizens for Social Justice #Ezema FDRE Ministry of Justice ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር Al Jazeera English Billene ቢልለኔ Aster Seyoum Neamin Zeleke Office of the Prime Minister - Ethiopia BBC News (UK) DW Amharic Redwan Hussien Daniel Kibret Taye Atske Selassie Ethiopian National Dialogue Commission VOA Amharic Fana Media Corporation S.C. (FMC) @walta_info EBC WORLD እስከዳር እምሻው 🇪🇹አስካለ ማርያም Dawit

Andargachew Tsege

61,369 görüntüleme • 2 yıl önce

የ EBS ባለቤት ይቅርታ ጠይቀዋል:: እውነት ለመናገር #EBS በግሌ ከምወዳቸው ቴሌቭዥን ጣብያዎች አንዱ ነው:: ይህ ቴሌቭዥን ጣቢያ በተለይ ባለቤቶቹ በዚህ ደረጃ ህዝብን ሊያባላ የሚችል ፕሮግራም ሆን ብለው ያስተላልፋሉ ብዬ አልገምትም:: ለኢትዮጵያ ህዝብና ለቴሌቭዥኑ ተከታታዮች ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት ነው:: ይህን ስል ምናልባት በገንዘብ በብሔርተኝነት ተታለው ይህን ዝግጅት የሰሩ ያስተላለፉ የለም እያልኩኝ አይድለም:: ፓሊስ የያዘው ምርመራ ሲያልቅ አብረን የምናየው ይሆናል:: እንደ ሃገር ግን ሊደርስብን ከነበረው ትልቅ እልቂት ኢቢኤስም ቢሆን ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት ብዬ አምናለሁ:: አንዳንዶች ባለቤቶቹ ኤርትራዊ ናቸው ሻቢያ ናቸው የምትሉት ነገር ትክክል አይደለም:: ኢቢኤስ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በልማትም ተቋማትንን በመርዳትና በጎ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ለብዙ አመታት የቆየ ተቋም ነውና ይህን የማይሆን አስተያየታችሁን እንድታቆሙ እጠይቃለሁ:: በተረፈ ኢቢኤስ ከዚህ በኃላ አሁን ከተፈጠረው ስህተት ትምህርት ተምሮ ብዙ ነገሮችን ያስተካክላል ብዬ እምናለሁ:: ሰራተኞቹን ጨምሮ:: የኢቢኤስ ትልቅ ስህተት ለሌሎችም ትምህርት ሊሆንም ይገባል::

Natnael Mekonnen

19,873 görüntüleme • 1 yıl önce