Video wird geladen...

Video konnte nicht geladen werden

Zur Startseite

ከመንግስት አይን ይጠብቃችሁ🤍

43,058 Aufrufe • vor 3 Jahren •via X (Twitter)

9 Kommentare

Profilbild von Yewubdar
Yewubdarvor 3 Jahren

@EA_DevCouncil Amen

Profilbild von ナサニエル
ナサニエルvor 3 Jahren

The caption is perfect

Profilbild von Hiwot Bamlak
Hiwot Bamlakvor 3 Jahren

❤️

Profilbild von afiya seid
afiya seidvor 3 Jahren

@Gfasil አሚን

Profilbild von FanoHero
FanoHerovor 3 Jahren

@EA_DevCouncil Amen 🙏

Profilbild von HAGERE TESFA ALAT
HAGERE TESFA ALATvor 3 Jahren

@ethiopiansone ሥራ ፈት!!!!!!!

Profilbild von Ring of Fire , PhD
Ring of Fire , PhDvor 3 Jahren

@Leah_ORG @AbiyAhmedAli will shot them dead

Profilbild von smileygirl
smileygirlvor 3 Jahren

🤩

Profilbild von BarkotEthiopia
BarkotEthiopiavor 3 Jahren

ከመንግስት ዐይን ያውጣችሁ!

Ähnliche Videos

የብልፅግና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በለንደን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ሊያደርግ የነበረው ስብስባ በለንደን ፋኖ ተፅእኖ ተበትኗል :: በዲያስፖራ ውስጥ ተሸሽገው የአማራን ተወላጆች ለአራጁ ለአብይ አህመድ መንግስት አሳልፈው በመስጠት ከሚታወቁት የለንደን ቦዘኔወች አንዱ ወሰን ኢርኮ እጅ ከፍንጅ በለንደን ፋኖወች ዛሬ ተጋልጧል :: ግለሰቡ በድፕሬሽን ታብሌት የሚኖርና ከመንግስት የዲዜብል መኪና ተስጥቶት የሚያሽከረክር ሲሆን ለንደን ውስጥ ምንም ስራ የለለው በመንግስት እርዳታ የሚኖር ቦዘኔ ነው :: ለንደን ውስጥ በዳያስፖራው ውስጥ ተደብቀው ለብልፅግናው የአብይ መንግስት የአማራ ተወላጆችን ና የመንግስት ተቃዋሚወችን እያስጠቆሩ ከብልፅግና መንግስት መሬት ተስጥቷቸው ቤት የሚሰሩ እንዳሉ የለንደን ፋኖ በልዩ ክትትል ደርሶባቸዋል :: በቅርቡ ስም ዝርዝራቸውንና ተግባራቸውን እናጋልጣለን ከእንግዲህ በሗላ በአማራ ደም መቀለድ አይፈቀድም :: በለንደን የምትገኙ ኢትዮጵያዊን ሁሉ እነዚህን አድር ባዮች በማጋለጥ እንድት ተባበሩ የለንደን ፋኖ ጥሪ ያደርጋል ሞት ለባንዳዎች ፋኖ በድል አድራጊነት ያሸንፋል!

Elizabeth Altaye

17,691 Aufrufe • vor 1 Jahr

በዘመነ ካሴ የሚመራው “የአማራ ፋኖ በጎጃም” 34ቱን የወረዳ ሰዎች የረሸነበት ጭካኔ። እራሱን የደጋ ዳሞት ብርጌድ በሚል የሚጠራ “የአማራ ፋኖ በጎጃም” ታጣቂ ክንፍ ከመንግስት ጋር ተባባሪ ናችሁ በሚል ከፈረስ ቤት ወረዳ ብዛት ያላቸው ሲቪሎች አስሮ የነበረ ሲሆን 34ቱን በፈረስ ቤት ሚካኤል ት/ቤት ውስጥ መረሸኑ ተረጋግጧል። ከተገደሉት ውስጥ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዋሌ እንደሚገኙ ሌሎች ሳይገደሉ የቀሩት ከፍተኛ ገንዘብ የተጠየቁባቸው በሆናቸው ነው። ጅምላ ግድያው የተፈፀመው “የአማራ ፋኖ በጎጃም” ወታደራዊ አዛዥ በሆነው ዝናቡ ልንገረው የበላይ ትዕዛዝ እና የደጋ ዳሞት ብርጌድ አዛዥ ዘለቀ ሞላ ምረቴ ፈፃሚነት ነው። የህዝብን ቅቡልነት ማግኘት ሲያቅት ይህንን አይነት የሽብር ድርጊት እየፈጸሙ አርበኛ፣ ሻለቃ፣ ብርጌድ እየተባባሉ በስሙ ለመነገድ እንዲህ አማራውን የሚያሰቃዩት እነማን ናቸው? ከየትኛው ዘር የበቀሉ ናቸው? አማራው አርሶ መብላት፣ ተምሮ ማፍራት፣ ጀግኖ ሀገርን በጽናት መጠበቅ እንጂ ይህንን አይነት የጭካኔ መጠን በቤተሰቡ ላይ እንዲህ ሲያደርግ፤ የሰከነው፣ ተው ባዩ፣ ሽማግሌው ከወዴት አለ?

Natnael Mekonnen

22,816 Aufrufe • vor 1 Jahr

''ውሸቱ የሚቆመው የአብይ አህመድ መንግስት ሲወድቅ ነው። መንግስታት ይዋሻሉ። የአብይ አህመድ ግን በሽታ ነው'' ዶ/ር ዮናስ ብሩ Yonas Biru ሚዲያ Mesay Mekonnen የሰጠው ቃለ ምልልስ። ሰሞንኑን ህዝብ በሙሉ እንደታዘበው "በቁስል ላይ እንጨት ስደድበት" እንዲሉ #ብርቱካን ተመስገን ላይ እያደረሱ ያሉት የበደል በደል የብልጽግና መለያ ምግባሩና ማንነቱ ነው። ከቀደሙት አገዛዞች ሁሉ በተለየ የኦሮሚያ ብልጽግና የሚዘውረው አገዛዝ በተለይም ከመሪው አረመኔ የበሻሻ ደላላ #አብይአህመድ ጀመሮ እስከታችኛው እርከን የነጭ ውሸት ፣ የማጭበርበር፣ የውንብድና ክምር ነው ። አረመኔያዊ ተግባራት ፣ ሸፍጥ፣ ሴራ፣ ነውር፡ ክህደት ፣ ድንቁርና የሚሉ ቃላት ምንነቱን ምግባሩን ሙሉ በሙሉ አይገልጹቱም፣ ከዝቅጠቶቹ ፣ ከስራአትጁ ሞራል አልባነት ፣ ከወራዳነቱ ለ1000 ሺ መገለጫዎች እንዱ ብቻ ነው። ዶ/ር ዮናስ ብሩ የአገዛዙ ቁንጮና የውሸትና የአረመኔነት ክምር የሆነው አብይ አህመድ አይን ያወጣ ተደጋጋሚና አሳፋሪ ውሸቶች ዙሪያ ለአንከር ሚዲያ የሰጠውን ቃል ምልልስ ተከታተሉት፣ የፓርላማ ውሎው ላይ አይኑን ሳያሽ የተናገረቸውን ውሸቶች በዝርዝር ይሄድበታል። ሙሉውን እዚህ ታገኙታላችሁ።

Neamin Zeleke

161,863 Aufrufe • vor 1 Jahr

ማርሻሉ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ያሉ አማፂያንን 90% ደምስሰናል እያሉን ነው። ምነው እንዲህ የተጋነነ ፉከራን መደጋገም ቢያቆሙ? ገና 'ለውጡ' አንድ አመት ሳይሞላው "ሸኔን በ 2 ሳምንታት እናጠፋታለን" ብለው ጦርነት ያወጁ እለት በአካል አግኝቻቸው የርስበርስን ጦርነት አይደለም በ2 ሳምንታት በዓመታትም ማሸነፍ አዳጋች እንደሆነና ጉዳዩን በሰላም መፍታት እንደሚሻል ተመጽኛቸው እንደነበር ትዝ ይለኛል። ከዚያ ወዲህ ስንት በሁለት ሳምንታት አማፂያንን የማጥፋት ዘመቻ ተካሄደ? ተሳካ? አሁን ደግሞ ይህን በ90% ደመሰስን ፉከራ እየደጋገሙት ነው። እውነታው ግን የሀገሪቷ 2/3ኛ በላይ ከመንግስት ቁጥጥር ስር የወጣ ነው። ሌላው ይቅርና የአማፂያኑን ጥቃት በመፍራት ገበሬው በቆሎ እንዳይዘራ እስከመከልከል ተደርሶ የለ እንዴ? እባካችሁ ይህን ዋጋ ቢስ ቀረርቶ ተዉና ጦርነትን በድርድር አስቁሙ። ይህ ማለቂያ ያጣ የርስበርስ ጦርነት የሰራዊቱን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያመነመነ የመበተን አደጋን በየቀኑ እያቀረበ ባለበት በዚህ ጊዜ ኢታማጆር ሹሙ እንዲህ አይነት ከሀቅ የራቀና የሰላምን በር የበለጠ የሚያጠብ ዲስኩር መደጋገም ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ስልሆነ ቢታቀቡ ይሻላል።

Jawar Mohammed

24,001 Aufrufe • vor 1 Jahr

እውነትም ጋሻ - ው! የአብኑ ጋሻው መርሻ ከ BBC ጋዜጠኛ ጋር ያደረገውን የድምፅ ቅጂ ሰማሁት። ጋዜጠኛዋ ሌሎቹ ላይ እንደለመደችው ለአንድ አለም አቀፍ ሚዲያ እንደምትሰራ ረስታ የሞንጆሪኖን አፍ ተውሳ ልታሸሙር ስትሞክር ሰውዬው ጋሻው ነውና ቀንድ ቀንዷን ብሎ አስደንብሯታል። ጋሻው አይደለም ቢቢሲ ዶናልድ ትራምፕ ቢደውልለትም እውነትን ከነ ቡጉሯ አስቀምጦልህ ነው ሚሄደው። ጋዜጠኛዋ የአብን አመራር እንደሆነ እያወቀች ከመንግስት አጀንዳ እንደሚቀበል አድርጋ ልታሳየው ስትጋጋጥ “ምነው ድምፅሽ ወያኔን ወያኔን አለኝ” ብሎና እውነቱን በሃይለቃል ተናግሮ ደህና ዋይ ሳይላት mic drop አረገ 😂 ታዲያ ምናባቷ ያለፋድዳታል :D ቢቢሲዎች ግን ለአርባ ደቂቃ የቆየውን ኢንተርቪው ቆርጠው ጋሻው ከትንሽ ክርክሮች በኋላ ጥሎ የጠፋ አስመስለው አቀረቡ። እድሜ ለስልክ ቅጂው ሰማነው እንጂ። ቢቢሲን የሚያህል ትልቅ ጣቢያ ጥቂት የፖለቲካ ወገንተኝነት ባላቸው የወያኔ አጀንዳ አስፈፃሚዎች እንዲህ መቀለጃ መሆኑ ያሳዝናል። አብን እንደድርጅት በዚህ ጉዳይ ላይ ለዋና ጣቢያው ቅሬታውን መፃፍ ያለበት ይመስለኛል። ለማንኛውም ጋሻው መርሻ ቀልድ አያቅም ወዳጄ። ንግግሩ ቁጥብና ቆራጥ ነው። ውቃቢው ካልወደደህ ማንም ሁን ማን ካንተ ጋር ሲለፋደድ አይገኝም ጆሮህ ላይ ጠርቅሞት ስራውን ይቀጥላል። የመይሳው ልጅም አይደል! 🫡ይመችህ ጋሺቲ ቢቢሲ ላይ አጭርና መብረቃዊ ጥቃት አድርሰህ ነው ያባረርካት!

Natnael Mekonnen

12,670 Aufrufe • vor 4 Monaten

#ዘመቻ ማእበል በሚል አዲስ ስያሜ አረመኔው ነፍሰ በላ ፋሽስት #አብይአህመድ በአማራ ህዝብ ላይ ያዘመተው ሰራዊት በአራቱም ቀጠናዎች በአማራ ፋኖ አርበኞች ድባቅ እየተመታ ተመክቶአል። ዘመቻ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል (አፋብሃ) የጎንደር ቃል አቀባይ እንዳስቀመጠው የአብይ አህመድ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ማእበል ወደ “ምርኮኛ ማእብል” ተቀይሮአል። አይን ቀቅሎ የበላው ወሮበላው አብይ አህመድና በራሳቸው ቆመው ማሰብና አርቆ ማየት የተሳናቸው ምርኮኛና የኮታ ጀነራሎቹ ባለፉት 2 አመታት በአማራ ክልል ከደረሰባቸው ከተደጋጋሚ ውድቀቶቻቸውና ሽንፈቶቻቸው ፈጽሞ እይማሩም። የመከላከያ ስራዊቱ እና ጥምር ሃይል የሚሉትን ውድቀት፣ ውርደትን፣ ለ10ቱ ሺዎች ሞት፣ መቁሰልና ፣ ምርኮ የዳረጉ ዘመቻዎች በድጋሚ በማደርግ የተለየ ውጤት መጠበቅ፣ ድድብና ፣ እብደት ነው። “ውድቀት ያመጣን አንድ ዘይቤና ስትራቴጂ፣ ያንኑ ያኑኑ መልሶ መላሶ በመፈጸም የተለየ ውጤት መጠበቅ እብደት ነው” እንዳለው አንድ የዘመናችን ብልህ አሳቢ ሰው። ዛሬም እንደ ትላንቱ ለ 10ኛ ግዜ ሞክረውን ፣ በሸዋ፣ በወሎ ፣ በጎንደር፣ በጎጃም በበርካታ አካባብዊች ከባድ ሽንፈት፣ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን ተከናንበዋል። ለዝርዝሩ የሚከተሉትን የአንከር ሚዲያ ዘግባዎች ተከታተሉ። በህዝብ ላይ አየደረሰ የሚከኘው መከራና ውድመት ፣ የመከላከያ ስራዊቱ ላይ የሚደረሰው ሞትና ከባድ ኪሳራ ምንም ገድ የማይሰጠው በድን አረመኔው ፋሽስት አብይ አህመድ እና አስር አለቃ ብርሃኑ ጁላ ይህንኑ የሽንፈትና የውርደት ካባና ውድቀት የዳረጉ ድርጊቶቻቸውን ለመሸፋፈን "ከአፍሪካ ትልቁን መከላከያ ገንብተናል፣ ማንም የማይበገር ሰራዊት ግንብተናል ፣ ወዘተ " በሚል የኢትዮጵያን ህዝብ ማጭበርበራቸውን እና እና ማደናገሩን ይቀጥሉበታል። ዘመቻ ማዕበል በሰሜን ሸዋ የአብይ አህመድ 'ዘመቻ ማዕበል' Anchor Media ዘመቻ ማዕበል በምርኮኛ ማዕበል ተቀይሯል - አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ

Neamin Zeleke

12,719 Aufrufe • vor 1 Jahr

#አብይ አህመድ የበሻሻው አረመኔ ደላላና የኦሮሚያ ብልጽግና ፋሽስታዊ ጭንጋፎች በአዲስ አበባ ነዋሪዎችና በሸገር በሚሉት ዙሪያ ነዋሪ መቶ ሺዎች ኢትዮጵያውያን የፈጸሙት የግፍ ግፍና የወንጀል ጉድ በአመንስቲ ኢንተርናሽናል ሲጋለጥ፡ የበሻሻው ወሮበላ #አብይአህመድ "ካሳ ሳንከፍል ማንንም አላፈናቀልንም" በማለት አይን ቀቅሎ የበላ ቅጥፈትና ህዝብን ማጭበርበር በአመንስቲ ኢንተርናሽናል የምርመራ ዘገባ ዝርዝር ከሳተላይት ምስሎች ጋር ወጥቶአል። በሁሉም ኢትዮጵያዊ/ት መነበብ አለበት። እነዚህ መረጃዎች በማንበብ ከዚህ ቀደም ኢሰመጉ፣ ኢሰመኮ፣ በርክታ ሚዲያዎች ያወጧቸውን ተመሳሳይ አሰቃቂና ዘግናኝ ዘገባዎችን ትክክለኝነት የሚያሳይ ሌላ ማረጋገጫ መሆኑን ይረዳሉ። አጭበርባሪውና አረመኔው አብይ አህመድ ፣ አዳነች አበቤና የኦሮሞያ ብልጽግና ጉግማንጉጎች ፣ በመቶ ሺ ድሃ ኢትዮጵያውያን ላይ አረመኔነት፣ ባርባሪዝም ፣የግፍ ግፍ ጥግ መጠን በሚገባ መሰነድ ይገባዋል። ወደፊት የመንግስት ለውጥ ሲደረግ በዚህ አረመኔያዊ ተግባር ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ካሳ እንዲያገኙ፣ ፍትህ አንዲያገኙ ከወዲሁ መታሰብ አለበት። ህሊናቸው የተጋረደባቸው የአገዛዙ ካድሬዎችና መቶ ሺዎችን ዜጎች በማፈናቀልም ሆነ የዘር ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎች ሰለባ ከመደረግ በኋላ አሻፈረኝ ብሎ ለህልውናው የሚፋለመውን የአማራ ፋኖ የሚከሱ የአገዛዙ ደጋፊዎች ቀለም ሲቀቡት ይወላሉ። ተጋልጦ እርቃኑን የቀረውን የዚህን አረመኔ አገዛዝ ገመና ለመሸፈን ይጋጋጣሉ። አነዚህ ደናቁርት አይናችሁን ጨፍናችሁ፣ ይህን የአፓርታይድ ፋሽታዊ ስርአት ደግፉት፣ በማለት ነውሩን፣ የግፍ ግፉን፣ ኢፍትሃዊነቱን ለመሸፈን ነጋ ጠባ ይውተረተራሉ። ነገር ግን አውነትና ነጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ፣ ቀደም ሲል የሀገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች- ኢሰመኮ፣ ኢሰመጉ፣ ሌሎችም በየግዜው ያወጡትን ልዩ ልዩ ዘገባዎችና መረጃዎች ለማስተባበል ሲጋጋጡ፡ ይህን በተለይ በድሃው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ይተፈጸመ ወንጀል “ልማት ነው” በሚል ለማሳመን፣ ወንጀሉን ግፉን፣ የሰብአዊ መብቶች ረገጣውን ኖርማልይዝ ፣ለማድረግ ሲጋጋጡም ታዝበናል። አሁን ደግሞ አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ከሳተላይት ምስሎች ጋር በምርመራ ዘገባው አጋልጦታል። #JusticeforEthiopia #EthiopiaResist ethno fascism The Federal Government of #Ethiopia must pause the Corridor Development Project and end forced evictions that violate human rights law. #StopForcedEvictions #EndImpunity

Neamin Zeleke

15,425 Aufrufe • vor 1 Jahr

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እርሶ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሰጡት ምስክርነት ተነስቼ እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቆት ፈለኩ .. እሄውም ምንድነው ..አቶ ገዱ ሰለ አብይ አህመድ ምንነት ቀድሞ ተረድቶ በጣም በተጣራ ሁኔታ ፁሁፍ ፅፎ አዘጋጅቶ ባህርዳር በሄድኩበት ወቅት አሳየኝ ብለዋል .. ኦኬ እሺ ጥሩ ነው ሊሆን ይችላል ብለን እንውሰደውና .. አቶ ገዱ ቀድምው አውቀው ውስጥ ውስጡን ሲታገሉ የከረሙ ታጋይም እንደነበሩ መስክረዋል ባልሳሳት .. እንግዲህ እኝህ ሰው ይሄን ያክል በዚህ ደረጃ የውስጥ ተቃዋሚ ሆነው በሚንቀሳቀሱበት ሰአት እርሶ ደግሞ ከእስር ተፈተው እርሶና አብዛኛው የሀገሪቷ ህዝብ እንዲሁም የግንቦት አባል የነበራችሁ በጠቅላላ በሚባል ደረጃ የአብይ እህመድ ደጋፊ እና ተንከባካቢአፍላ ፍቅርኛ የነበራችሁበት ወቅት ነበር .. ለውጡ እንዳይደናቀፍ እያላችሁ ከላይ ታች ስትሉ ከነበሩት ህዝቦች መካከል ዋነኞቹም ነበራችሁ .. ለውጡን ልክ እንደ አራስ ልጅ እየተንከባከባችሁ ኮሽታ እንኳን እንዳይረብሸው በስስት ዘብ ከቆሙት ህዝቦች ዋንኞቹ ናችሁ ብል ምንም ማጋነን የሌለበት ነው .. ታዲያ ይሄ ሆኖ ሳለ የኔ ጥያቄ የሚሆነው እናተ አፍላ ደጋፊ በነበራችሁበት ወቅት አቶገዱ የውስጥ ተቃዋሚ ሆነው እየተንቀሳቀሱ እርሶ እና ጓደኞቾት ደግሞ በዚህ መጠን ድጋፍ እንደምትሰጡ እየታወቀ ወይም አቶ ገዱ ይሄንን እያወቁ እንዴት እርሶን አምኖዎት ነው አብይ አህመድ ጥሩ እንዳልሆነ ሊነግሮዎት የቻሉት ወይም የመቃወሚያቸውን ፁሁፍ ለእርሶ ሊያሳዮት የችሉት ..? ሃሃ..? 🤔 እስኪ እርሶ በዛን ሰአት almost የአብይ አህመድ ቀኝጅ ነበሩ እኮ እንዴት በዚህ ደረጃ ለስርአቱ ቅርብ ለሆነ ሰው አምነው አቶ ገዱ እርሶ የነገሩንን አይነት ፁሁፍ ለእርሶ ሊያሳዮዎት ቻሉ ..???????? አቶ ገዱ እንደሚነግሩን አይነት ሰው ከነበሩ እርሶ እኮ ታዲያ ለሳቸው ጠላት ነበሩ ማለት ነው ..! ታዲያ አቶ ገዱ ምን ያክል ጅል ቢሆኑ ነው ለጠላት ሚስጥር ሊያሳዩ የቻሉት ..? አረ ውሸትም እኮ አይነት አለው .. ! ተው ትውልዱ እሳት ነው አይሸወድም .. ተዉዉ እረፉ ..?! በዚህ መልኩ በማይዋጥ ትርክት ገፅታ ለመገንባት እና ትግልን ለመሻማት አይን ያወጣ ውሸት ምንም አይጠቅምም ይቅር ተዉ .. እውነት እንደው ልጠይቆት እርሶ ሆኑ አቶ ገዱ ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ከሆኑ እስከዛሬ ድረስ ላደረሳችሁት ዳሜጅ ህዝብ ይቅር እንዲላችሁ እና እውን ቅን ልቦና ካላችሁ በቅንንነት ይሄን የተገፋ ህዝብ ለማገልገል ከፈለጋችሁ እስኪ ከኋላ ሆናችሁ ምስክርነት በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ ብቻ እየተገኛችሁ የስርአቱን አስከፊነት እና የአብይ አህመድን ወንጀሎችን በማጋለጥ ረገድ ብቻ ለምን ትግሉን አታግዙም.. እውን ለዚህ ህዝብ ካሰባችሁ ..?? እንጂ ይቺ አሁን እርሶ ባመጧት ቁጭ በሉ አይነት ትርክት ማንንም ሊሸውዱ አይችሉም .. እሳተ ነበልባል ትውልድ ነው .. በጥያቄ ያጣድፋችኋል .. በዛላይ ብዙ የተገፋ ብዙ ሴራ የተጎነጎነበት ብዙ ግዜ በየዋህነቱ መጠቀሚያ ሆነና የነበረ አሁን ላይ በቃኝ ብሎ የተነሳ ትውልድ ብሶት የወለደው ህዝብ ነው .. ከእንግዲህ እይሸወድም ልሎት ፈልጌ ነው .. አበቃሁ ..✍️ ይድረስ ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ

liyu fkir

13,273 Aufrufe • vor 1 Jahr

የመሪ ስነ-ልቦነናና ዶክተር አብይ! Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚህ 8 አመት የተፈተኑትን ያህል ባለፉት መቶ አመታት የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች እንዳልተፈተኑ እርግጠኛ ነኝ። ሶማሌ ክልል ከነበረው አመፅ ጀምሮ በየቦታው ሁን ተብልው የተለኮሱ የብሔር ግጭትና ጥቃቶች፣ በየቅያሱ የፈላው አማፂ ብዛት፣ ሰፋ ላለ ግዜ የተደረገው የትግራዩ ጦርነት፣ ጂኦፖለቲካው፣ የሶማሊያና የሱዳን አለመረጋጋት፣ የውጪ ሃይል ጣልቃ ገብነት፣ ወዘተ ተቆጥሮ አያልቅም። እውነተኛ መሪ የሚለካው በፈተናው ልክ ነው። ኖርዌይን የሚመራም ኢትዮጵያን የሚመራም በእኩል አይን መታየት የለበትም። ኢትዮጵያን መምራት አምስት የተረጋጉ ሐገራትን ከመመምራት ይበልጣል። አንድ መሪ በተቻለ መጠን ወታደራዊ ባክግራወንድ ቢኖረው ጥሩ ነው ይባላል። ሐገር በፈተና ስትናጥ ተረጋግቶ ውሳኔ መስጠት እንዲችል ወታደራዊ ስነልቦና የግድ ይላል። ኢትዮጵያን ከዩኒቨርስቲ እስክሪብቶ ብቻ ይዘህ ወጥተህ በቀላሉ የምትመራት ሐገር አይደለችም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባይሆኑ ኖሮ ሐገራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በገባች ግዜ ተረጋግቶ ሐገርን ማስቀጠል ለብዙ ሰው የሚቻል ነገር አይመስለኝም። የማርቆሱ የአውሮፕላን ማረፊያ የሚነግረን ይሄንን ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቡር አይቆምም። ጠላት እፏልልበታለሁ የሚልበት ምድር ሄደው ትልቅ ፕሮጀክት ተክለው መርቀው ይመለሳሉ። ሰላም በራቀበት ቦታ ሰላሙን ማስጠበቅ አንድ ነገር ሆኖ እዚያው ቦታ ላይ ፕሮጀክት ጨርሶ ሄዶ መመረቅ ሌላ አቅም ይጠይቃል። በሌሎች አካባቢዎችም፥ በተለይ የፀጥታ ችግር አለባቸው በሚባሉባቸው አካባቢዎች ልማቱ አልተቋረጠም፣ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው መሬት ላይ ይወርዳሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሚሰጡት በስራ ይመስላል። loud minority ዎች ድምፃቸው ጎልቶ ስለተሰማ በጫጫታ ሐገሩን የተቆጣጠሩ ይመስላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሃላቸው ሄደው አይናቸው እያየ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ፈፅመው በስራ ምላሽ ይሰጣሉ። ይሄን ለማድረግ “መሪ” መሆን ይጠይቃል። አሜሪካ በታሪኳ የከፋውና አገርን ለሁለት የከፈለ የእርስ በርስ ጦርነት (American Civil War) ውስጥ በነበረችበት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሚያልቁበት አስቸጋሪ ወቅት። በግዜው መሪ የነበረው አብርሃም ሊንከን ጦሩን እየመራ የአሜሪካን ምሥራቅና ምዕራብ ጫፎችን የሚያገናኝ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ማይሎችንና አስቸጋሪ ተራሮችን የሚያቋርጥ ግዙፍ አህጉር አቋራጭ የባቡር መስመር (Transcontinental Railroad) እንዲጀመር አዘዘ። በግዜው ብዙዎች “አበደ” ብለውት ነበር። ሰላሙ ይቅደም ያሉም ነበሩ። እንዴት አሜሪካ ትሰንብት አትሰንብት ሳያውቅ እንዲህ አይነት እቅድ ያወጣል ያሉትም እልፍ ናቸው። ሊንከን ግን ጦርነቱን እየመራ በነበረበት በዚያ አስጨናቂ ወቅት፣ የባቡር መስመሩ የወደፊትዋን የተባበረች አሜሪካ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ተገንዝቦ ነበርና ከአቋሙ ዝንፍ አላለም። በ1862 (ጦርነቱ በሃይል በተፋፋመበት ወቅት) ህጉን አጽድቆ፣ በገንዘብ እጥረትና በጦርነት ግርግር ሳይበገር ፕሮጀክቱ እንዲቀጥል ማድረግና አሜሪካን ማስተሳሰር ችሏል። ትክክለኛ መሪ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ነገውን ይሰራል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም እንዲሁ ዛሬን ሳይሆን ነገን ማየት የሚችሉ መሪ ናቸው። እንደውም አንድ ግዜ ውሃዋን በብርጭቆ ይዞ አካባቢው ባለው ነገር Diatracted ሳይሆንና ውሃዋን ሳያጎድል ከግቡ ያደረሰውን ሰው ታሪክ ተናግረው ነበር። ያ ሰው እራሳቸው ዶክተር አብይ ይመስሉኛል። ለማንኛውም እኔና ቤቴ ነውጥ በሚመስል ግርግር ውስጥ ለማይናወጡት መሪ እጅ እንነሳለን!

Natnael Mekonnen

12,169 Aufrufe • vor 13 Tagen

ይህ ስሙን መጥራት የማልፈገው ለአንደበቱም ለሆዱም ለከት ያልፈጠረበት የሰው አሳማ ፣ እጅግ አሳፋሪ፣ ወራዳና፣ ቆሻሻ የሆነው ባህሪውና ስብእናው ለአረመኔው ዋና ወሮበላ ከ #አብይእህመድ እምብዛም ልዩነት የሌለው መሆኑ የሚታወቅ ነው። ከአንድ ውሃ እንደሚቀዱ እንዘንጋ። እስስት፣ እባብ፣ እንዲሁም እይጠ መጎጥ ቅልቅል ነገሮች ፡ ከትቢያ አንስቶ ማን እንዳሳደጋቸው፣ ለሁለት፡ ለሶስትም እስርት አመታት የማን ተላላኪ እንደነበሩ ለህዝብ መናገር እንደ ስድብ ይሆናል። ለማንኛውም ይህን የሰው ዝቃጭ ዘሪሁን ተሾመ የሚባል የሬድዋን ሁሴን ተላላኪ ሌላ ተላላኪ ወሮበላ በሚሰጠው መመሪያ በጃዋር መሃመድ Jawar Mohammed ላይ ያቀረበውን የውሽት ክምር ሞገስ ተሾመ በዚህ በምታዩት ምስል ላይ ደርምሶታል/Debunked. በተጨማሪም "አብጤ" የሚል ስያሜ የስጠው የሰላው ብእረኛ #ካሳአንበሳው በፌስ ቡክ ድህረ ገጹ የጻፈውም ይነበብ። ስውየው አይኑን በትልቅ ጨው የታጠበ እንደ ዋና አለቃቸው አይን ቀቅሎ የበላ በመሆኑ የሚገባው አይደለም እንጂ እኔ እሱን ቢሆን በሬን ዘግቼ ንሰሃ እገባ ነበር። ================ ኤርሚያስ (አብጤ) ዋቅጀራ የገጠሩ አማራ ፖለቲካ ውስጥ የነበረውን አክስዮን ከሸጠ (ከተቀማ?) በኋላ ግራ ገብት ብሎታል፣ አቅጣጫው ጠፍቶበታል፣ ግራ መጋባቱ እንዳይነቃበት ይመስላል "ኮምፓስ" የሚል ሚዲያ ከፍቶ እዛና እዚህ አየተላተመ ነው፣ የኬንያና የአሜሪካ የመረጃ ድርጅቶች (በስም ተዘርዝረዋል) በተመሳሳይ ሰአት ስለ ጃዋር መረጃ መቀያየራቸውን፣ መረጃው አንዱ የአሜሪካ የደንነት ሰው ጠረጴዛ ላይ መድረሱ፣ btw የደንነቱ (agent) ስም ተጠቅሷል 😄፣ ደንነቱ ጃዋርን እንደመረመረው፣ ጃዋር የባጥ የቆጡን እንደቀባጠረ፣ ጃዋር ለደንነቱ ሰውዬ የተናገራቸው (interrogation transcript) አብጤ እንዳሉ፣ የጃዋር ስልክና ላፕቶፕ እንደተበረበሩ፣ ከዛም አንድ ኩንታል ማስረጃ እንደተገኝ፣ የተገኙትን ማሰረጃዋች በዝርዝር ያቀርባል፣ ብቻ ብዙ ነገር ሲል ሰማሁት፣ It contains very detailed information እኮ. 😄 አብጤ ደ*ደብ እንደሆነ አውቃለሁ፣ በዚህ ደረጃ ባዶ መሆኑን ለማወቅ ግን የዛሬዋን ቀን መጠበቅ ነበረብኝ፣ የአብጤ ቀደዳ ተራ ውሸት መሆኑን ለመረዳት የአሜሪካ ህግ እንዴት እንደሚሰራ በደምሳሳው ማወቅ በቂ ነው፣ አንድ ሰው በምንም ምክንያት ተጠርጥሮ በደንነት ሰው ምርመራ ሊደረግበት ይችላል፣ ይህ በሆነ መንገድ ሊታወቅ ይችላል፣ ቢበዛ አንድ ሰው በቁጥጥር ስር ውሎ ለምርመራ ተወሰደ የሚል ነገር በሆነ ሊሰማ ትችል የሆናል፣ ከዛ ያለፈ የማወቅ እድል ግን ዜሮ ነው፣ ምክንያቱም ከፍተኛ የደንነት ሰው የሳተፍበት ምረመራ ቀርቶ የአንድ ተራ ፖሊስ የምርመራ ዝርዝር ጉዳይ ሚስጥር (classified) ይሆናል፣ አብጤ የዘረዘራቸውን መረጃዎች ማግኝት የሚችሉት የአሜሪካ ፍትህ ዲፓርትመነት (DOJ)፣ ፍርድቤት ወይም ሴኔት ነው፣ አብጤ ደግሞ ከነዚህ ውስጥ አንዱም አይደለም፣ የአብጤ ቀደዳ ትተን ነገሩን ትንሽ ሰፋ አድርገን እንመልከተው፣ አብጤ አገኝሁት ያለው መረጃ ትክክል ቢሆንስ? መረጃው leaked አድርጎ አግኝቶት ቢሆንሰ? የዛኔ ነገሩ ከባድ ወንጀል (felony) ይሆናል፣ የማይገባውንና ያልተፈቀደለትን መረጃ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በመያዙ አብጤ ላይ ክስ ይቀርብበታል፣ አሁንም ቢሆን ጃዋር ለልጆቹ አዝኖ ካለተወው መቀመቅ ሊወርድ ይቻላል፣ በዚህወሬ የአንድ ጃዋር ስም ብቻ አልተነሳም፣ የአሜሪካ ህግና ስርዓት ጭቃ ተለቅልቀዋል፣ *** አብጤ የጻፈው ድራማ አይመስለኝም፣ ድፍን አንጎል መሆኑን የሚያውቅ አንድ ሰው የተጫወተበት ይመስለኛል፣

Neamin Zeleke

15,095 Aufrufe • vor 6 Monaten