Loading video...

Video Failed to Load

Go Home

ከኮንሰርት ጡረታ ይውጡ

12,289 views • 6 months ago •via X (Twitter)

0 Comments

No comments available

Comments from the original post will appear here

Related Videos

ጌታቸው ለሰላም ዋጋ ከፈለ Getachew K Reda ጌታቸው ረዳ ባይፈልገውም አስከፊው ጦርነት ውስጥ ራሱን እሳት መሀል አገኘው። የጦርነት ሰው አይመስለኝም። ነገር ግን ጦርነትን ባይወድም በደምብ perform አደረገ። በተአምርም በተደጋጋሚ ከሞት ተረፈ። በመጨረሻም ህውሀት ከገደሉ ላይ ለመውደቅ አንዲት ሳር ላይ ተንጠልጥላ በምታጣጥርባት ሰአት ከአራት ኪሎ የሰላም እጅ ተዘረጋ። ጌች ያ የተዘረጋውን የሰላም እጅ ጨብጦ ለሚወደው ህዝብ ሰላምን ለህውሀት ደግሞ ሁለተኛ የመኖር እድልን አጎናፀፈ። በጦርነቱ ግዜ ሁላችንም እንደተሰለፍንበት ወገን ብዙ ብለናል። ጌታቸውም ብዙ ብሏል። የጦርነት ባህሪ ነው። ሰው ማለት የማይሳሳት አይደለም ሰው ማለት ስህተቱን የሚያርምና ስህተቱ ዳግም እንዳይፈፀም ዋጋ የሚከፍል ነው። ጌታቸው ይሄን ነው ያደረገው። "እትብታችን አራት ኪሎ ነው የተቀበረው" የሚሉ የስልሳዎቹን አዛውንቶች እብደት በመቃወም ለትግራይ ህዝብ መጪ ተስፋ ሲል ታገለ። የትግራይ ወጣት ዳግም ወደእሳት እንዳይማገድ ሲል በህይወቱ ሳይቀር ተወራርዶ ተሟገተ። ስሙን አጠፉት! በካድሬዎቻቸው ዘመቱበት። በአካባቢ ተደራጅተው አብጠለጠሉት። የሚዲያ ዘመቻ ከፈቱበት። ጌታቸው ግን አልሸነፍ አለ። የከተማ ልጅ ስለሆነ ጥሎ ይሸሻል ብለው አዋከቡት። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች፣ ጡረታ አንወጣም ያሉ ቁሞ ቀር አዛውንቶችና በእውር ድንብር የሚነዳ ስሜታዊ ካድሬ ትናንት ሳኒታይዘር እንዳላለው በአጭር ግዜ ያዋርደውና ይዘረጥጠው ገባ። ጌታቸው ግን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ የትግራይን ህዝብ አይኔ እያየ ወደጦርነት አልጨምርም። በኔ ፊርማ ዳግም ህፃናት ልጆች አካለ ስንኩል አይሆኑም። በኔ ትእቢት ዳግም ትግራይ የጦርነት ቀጠና አትሆንም ብሎ በአቋሙ ፀና። ለዚህ ክብር አለኝ። ጌታቸው ጦርነትን አይቷል። ከሱ በላይ ለጦርነት የቀረበ ሰው አልነበረም። ጦርነት በዘፈን እንደሚፎከርበት፣ በጦርነት ፊልሞች ላይ ተቀነባብሮ እንደሚታው attractive ነገር እንዳልሆነ አይቷል። ጌታቸው ከትምህርቱም በላይ ህሊና ስላለው ጦርነትን ሲያስብ የሚታየው በሱ ተረማምዶ የሚያገኘው ስልጣንና ገንዘብ ሳይሆን ለፍታ ያሳደገችውን ልጇን አጥታ ብቻዋን የቀረች እናት ነች። ለዚያች እናት ሲል ታገለ፣ ለመጭው የትግራይ ወጣት ሲል ከሞት አመለጠ፣ ለህዝቡ ሰላም ሲል ስልጣኑን አስረከበ። መልካም የስራና የእረፍት ዘመን እመኝልሀለሁ ጌች።

Natnael Mekonnen

18,363 views • 1 year ago