
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@KiyaEthiopia • 30,370 subscribers
It is not our differences that divide us. It is our inability to recognize, accept, and celebrate those differences!
Shorts
Videos

ትናንት ኢትዮጵያን ረሀብተኛ ከዛም ጄኖሳይደር እየተባለ እዚህ ደረስን: ዛሬ ደግሞ እንደ አዶናይ ያሉ ዋልጌዎች ደግሞ በተራቸው ተነስተው ኢትዮጵያ በጥናት የተረጋገጠ በ porn addiction ከአለም 2ኛ ነች የሚል የ ሀገርን ስም የሚያጠፋ: የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር የሚነካ: የ ሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩ ልክ አይደለም የሚላቸው እንደ ነውረኛ ተቆጠረ: ትውልዱን ደደብ ካልሆንክ አያልፍልህም: የነገዋን ኢትዮጵያ ሀገር ተረካቢው ትውልድ በእውቀት እና በብስለት የሚመራ ሳይሆን በሶሻል ሚዲያ ላይ የደደበ ይረከብ: ብቻ አንተን ታዋቂ እስካደረገህ ድረስ የሰው ነብስ ብታጠፋም: ሀገር ብትሸጥም ችግር የለውም: ዋናው ነገር ታዋቂ መሆንህ እና ገንዘብ መሰብሰብህ ብቻ ነውን በአደባባይ ሰበኩት: ነውራቸው ጌጣቸው ሆነላቸው እና ልጆቻችንን አትማሩ ስላልክልን: ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ስላዋረድክልን ብለው ለብልግናው ሸለሙት: ሁለት ፀጉር ያበቀሉ አዋቂ የመሰሉን እና ያጨበጨብንላቸው ሰዎች ሁሉ ሲያሞግሱት ሲያወድሱት ታዝበን የልጆቻችችን ጭንቅላት የሚያቀነጭር: የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት የሚሸረሽር: ይሄ ሰው ከጀርባው ያለው ማነው ዝምታውስ ለምን ብለን ነበር: ዛሬ ፖሊስ ዝምታውን ሰብሯል: ጥብቅ የሆነ ምርመራ ያስፈልገዋል! አዶናይ ማነው? ትናንት ግድ የለም ያልናቸው ነገሮች ናቸው ዛሬ ዋጋ እያስከፈሉን ያሉት! ትንንሽ ነገሮች የመሰሉን ገዝፈው ያገኘናቸው! Demelash Gebremichael
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹21,402 Aufrufe • vor 8 Monaten

የዴሞክራሲ ልምምዱን እያደነቅን እንደዚህ ያሉ የሶሻል ሚድያ ጭብጨባ ለስካር የሚዳርጋቸው ደማቸው ያልረጋ: አንጎላቸው ያልሰከነ: ለወንበር የሚጋጋጡባትን ኢትዮጵያ በበላይነት የሚመሩት የኢፌድሪ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስተር ይሁኑ ፕሬዚደንት ሳይለዩ ማይክ የሚጨብጡ: የመፅሀፍ ሽፋን አንባቢ ደርሶ ግንፍል አለሌዎች ከወዲሁ ተገርተው ሀሳባቸውን በሰለጠነ መንገድ እንዲያብራሩ ቢመከሩ ባይ ነኝ! ነገሩስ ፖርቲው ኢህሀፓ አይደል 😂 ለማያውቅሽ ታጠኝ 🤣
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹14,439 Aufrufe • vor 6 Monaten

ኢሬቻን ባህልም ይሁን ሃይማኖት አልያም ባእድ አምልኮ: ለአክባሪው ተዉለት‼️ አክባሪው ማህበረሰብ (በነገራችን ላይ ኢሬቻን ኦሮሞ ብቻ አይደለም የሚያከብረው) ኢሬቻ በደረሰ ቁጥር "ባህል ነው ሀይማኖትነው አይይይይይ ባእድ አምልኮ ነው" እያለ እንዳይገባው አድርጎ ጭንቅላቱን በጥላቻ ለሞላ ጥራዝ ነጠቅ የማስረዳት ግዴታ የለበትም: “The Society doesn’t owe you an explanation. Period.”‼️ፍቼ ጨምባላላ: አሸንዳ: ግንቦት ልደታ: መስቀል: ጥምቀት: መውሊድ ወዘተ ለምን እንደሚከበሩ ማብራሪያ የጠየቀ የለም: በኢሬቻ የሚፀደቅም ከሆነ ፀዳቂው አክባሪው ነው: ኩነኔም ከሆነ የሚኮነነው እራሱ አክባሪው ሆኖ ሳለ የምን እንደ እርጎ ዝንብ ሁሉ ነገር ላይ ጥልቅ ማለት ነው: ብዙ ሀይማኖት ጥቂት አማኞች ባሉባት አለም ላይ እንደምንኖር እያወቅነው እራስን የመንግስተ ሠማይ የመግቢያ በር ቁልፍ ያዥ አድርጎ መመፃደቅም ግብዝነት ነው እና ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አትናገር እንዲሉ ኳስ በመሬት! ለ Valentine’s Day ቀይ ልብስ ላስቀድድ: ለ Thanksgiving Turkey ልሸልት: ለ Halloween የ monster አልያም የ witches costume ካልሸመትኩ baby shower ካልተደረገልን አንወልድም በ wedding shower ካልተንበዛበዝን: በ bachelor party ካልተመዣረጥን: እያሉ የሰው ባህል እና ወግ ማዳመቅን እንደ ሥልጣኔ እየቆጠሩ: በሀገሩ ባለሙያዎች ተፈትሎ በጥበበኞች ተሸምኖ በተሠራለት ልብሱ አምሮ እና ተውቦ ዓለም እኩሌታ ሆነች! ቀን እና ማታ እኩል የሚሆንበት ሕይወት ትክክሏን ባላንሷን የምታገኝበት ምድር ታድሳ አዲስ ፍሬ አዲስ ልምላሜ አዲስ ተስፋ ይዛ የምትመጣበት ወቅት ሆነ!የእኩሌታ (equinox) ጊዜ እንደመሆኑ በኑሮአችን ውስጥ የተዛነፉ ነገሮች ሚዛናቸውን መጠበቅ ያለባቸው ወቅት እነሆ መጣ! የተጣላ ይቅር የሚባባልበት በክረምት የተነፋፈቀው የሚገናኝበት ወቅት እነሆ መጣ! የአጨዳና ምርት ጊዜ እንደመቅረቡ የተነቃቃ እና አዎንታዊ ስሜት የሚፈጠርበት በየብሔሩም ጥሩ ነገርና መልካም የበጋ መንፈስ የሚናኝበት ወቅት እነሆ መጣ ብሎ ይህንን ያደረገለትን የሠማዩን አምላክ (ዋቃን) የሚያመሰግንበትን የምስጋና ቀኑን: ባህሉን ወጉን ትውፊቱን ካርኒቫሉን ለአለም አስተዋዉቆ ቱሪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ በቱሪዝሙ መስክ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለውን እና ብዙ ሚሊዮኖች የሚያከብሩትን ትልቅ በአል ለማሳነስ እና ጥላሸት ለመቀባት መጋጋጥ ነውርም ትንሽነትም ነው! አንድ ማህበረሰብ ይገልፀኛል ይወክለኛል የሚለውን ባህል እና ትውፊት ማንቋሸሽ ለማን ይበጃል...? ሰበብ እየፈለጉ በተለይም ደግሞ የኢሬቻ በአል በመጣ ቁጥር በየአመቱ የሚንፀባረቀው ጥላቻ እና ንቀት ለማንስ ይጠቅማል: ኢትዮዽያ ለሁላችንም ትበቃለች። የኔ ባህል የኢትዮዽያ መገለጫ ነው ያንተ ቆሻሻ ነው: የሚል አመለካከት ትላንት ሆኖ አልፎ ይሆናል። ዛሬን ግን በትላንቱ መንገድ ለመመላለስ መሞከር እንቅፋቱ እንደ ሀገር ሊጥለን ይችል ይሆናል እንጅ መንገዱ ብዙ ምቹ ሆኖ አያስኬድም እና መከባበሩ ይበጀናል! በኢሬቻ ቂም በቀል በይቅርታ ይሻራል፣ ፅልመት ተሸንፎ ለብርሃን እጁን ይሰጥ እና ጨለማው ተገፍፎ ብራ ይሆናል የተለያየ ይገናኛል፣ የተጣላ ይታረቃል፣ ፍቅር ነግሶ ጥላቻ ቦታውን ያጣል: ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እና አብሮነት ይነግሳል ኢሬቻ ሠላም ነው ኢሬቻ በህብረት መቆም ነው! ሠሙም ወርቁም ይሄው ነው‼️ከኑማ‼️ ሰላም ለኢትዮዽያና ለህዝቦችዋ! መልካም በአል /Ayaana Gaari! Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 Office of the Prime Minister - Ethiopia Adanech Abiebie Mayor Office Of Addis Ababa Shimelis Abdisa Visit Oromia እናመሰግናለን🙏 #Ethiopia🇪🇹🇪🇹🇪🇹#Irreechaa2024
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹31,626 Aufrufe • vor 1 Jahr

የነፃነት እና የሕልውና ትግል እየተባለ በዚህ መንደር የቀውስ አትራፊ የሶሻል ሚድያ ተጧሪዎችና በሻዕብያና ግብፅ አበል ልባቸው ያበጠ አዕምሮአቸው የተደፈነ የነዓምን ዘለቀ Neamin Zeleke ዐይነት ሆድአደሮች ሲለፈፍ የሚውልለት: ስደተኛው ከሰው በታች ሆኖ የሚያገኛትን ዶላር የሚበዘበዝበት ፋኖ የሚባል ስልጣኔ እንደሰማይ የራቀው barbaric ቡድን በስሙ የሚነግድበትን ደሃ የአማራ ገበሬ እንዲህ ነው ቤት ለቤት እየረሸነ😭 ቤተሰብ እየበተነ: ሚስት እና ልጆቻቸውን እየደፈረ: ያጠራቀሙትን የቃረሙትን አሟጦ እየዘረፈ መከራ የሚያበላ ያለው። በጭካኔ ጥግ ለሊሻን ተገዳዳሪ የለውም የተባለለት ወያኔም በገዛ ወገኑ ላይ ይህን ሲፈፅም አላየንም አልሰማንም አላነበብንም። የነዚህ ለብቻው ነው!!! "መኃሉ አይነገርም "ነው ያለው በጋሻው ደሳለኝ🤔 ካሜራ ያላየው አደባባይ ያልወጣውን አቅፈው መክረው ገስፀው ባሳደጓቸው የአካባቢያቸው አዛውንቶች ላይ ሳይቀር የሚፈፅሙትን ግፍማ ቤት ይቁጠረው! ራስን መልሶ ለሚያትረከርክ የሲኒ ማዕበል የሆነ "ትግል" እናቶቻችን እና አባቶቻችን: ሴት ልጆቻችን እና እህቶቻችን ወንድሞቻችን እስከመቼ ዋጋ እንደሚከፍሉ አይገባኝም! ለማንኛውም the so called የአማራ "ትግል" እንደዚህ መንደር የምላስ አርበኞች አይደለም መሬት ላይ ያለው ሀቅ ከውንብድና የዘለለ ምንም መሠረታዊ አይዲዮሎጂ: በአግባቡ የተዋቀረ ትርክት: አመራር እና መሬት ላይ ጠብ የሚል አጀንዳ የሌለው። በፕሮፖጋንዳ ብቻ አየር ላይ ተንሳፎ ያለ የሻዕብያ እና የግብፅ ሥራ አሥፈፃሚ ሥብሥብ ኢሊት የሚመራው ሳያላምጥ የሚውጠው መንጋው ከበሮ የሚደልቅለት የባንዳ እና የሽፍታ ዘባተሎ እታገልለታለሁ የሚለውን ህዝብ ጨምሮ እንደ ድመት የሚበላ: ለመንደር ሹመት: ለሶሻል ሚዲያ ጭብጨባ እና እዛው እንደየአቅማቸው ላለችው "ሥልጣን" በነፍስ ሳይቀር የሚጨረጋገዱበት የእውር ድንብር ጉዞ ጉራ ብቻ ነው! ይሄው ነው‼️ ከኑማ‼️ Ethiopia 🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹31,651 Aufrufe • vor 2 Jahren

የኤርትራ "ነፃነት"? 1/2 በእኔ እይታ ኤርትራ የሻዕቢያ ህልም: የሻዕቢያ ቅዠት: የሻዕቢያ ድርሰት እና የሻዕቢያ ትግል ውጤት ናት። ሻዕቢያ ኤርትራን እንደሀገር አቆማለሁ ብሎ ሲነሳ ህልሙ የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር ሆኖ ኢትዮጵያን ቁልቁል እያየ የቀጠናው ፈላጭ ቆራጭ መሆን ነበረ። ይህንንም ለማሳካት እንደ ሀገር ተገንጥለናል ይበሉ እንጁ በንጉሱ ዘመን የኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ መልሶ መዋሃድ ተከትሎ የተከፈተላቸውን በር ተጠቅመው ያገኙትን ኢኮኖሚክ ፕሪቪሌጅ ትተው ለመሄድ ፈቃደኞች አልነበሩም። ይልቁኑ የኢትዮጵያን ቡና በብር እየገዙ በዶላር ኤክስፖርት በማድረግ በአንድ ወቅት በዓለም 1ኛ ቡና አቅራቢ ለመባል ሁሉ በቅተው ነበረ። ከዚህም ባሻገር እንደ ሀገር ኢትዮጵያን የሚያዳክም ኢኮኖሚክ ሳቦታጆችን ሲተበትብ ሰንብቶ ነበረ ሻዕቢያ። ወያኔም ወያኔ ሆኖ ካብ ለካብ ተያይተው አመከናቸው እንጂ! በተለይ የማልረሳው ሻዕቢያ ሀገር መስርቻለሁ ብሎ የራሱን ገንዘብ አትሞ ሲያበቃ የሚገበያየው ግን በኢትዮጵያ ገንዘብ ነበረ። ኋላ ህወሐት አገር ከሆናችሁ ራሳችሁን ችላችሁ የምትቆሙበትን መንገድ ቀይሱ ብሎ ከመሃል ሀገር ኢኮኖሚ ስራቸውን ሲነቅለው ከኢትዮጵያ ገበያ የሰበሰቡትን ከፍተኛ የሆነ የኢትዮጵያ ብር ወደ ገበያው በአንድ ጊዜ ለቆ ኢኮኖሚውን ለማላሸቅ ሲያሴር ውሎ አላደረም። በወቅቱ የመለስ ዜናዊ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ዶ/ር ነዋይ ገ/አብ ባስቀመጡት አቅጣጫ መለስ ዜናዊ ሌሊቱን የሃገሪቱን ገንዘብ ቀይሮ አድሮ ሻዕብያ ጠዋቱን መርዶ ተቀምጦ አረፈው። ይህና ሌሎች በሻዕብያ እና ወያኔ መካከል የነበሩ የጎንዮሽ ሽኩቻዎች ናቸው የ1991ዱን የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት የወለዱት። በነገራችን ላይ የሻዕቢያ ተንኮል ሳይገለጥልን በፊት ብዙ ኢትዮጵያውያን ከልባችን አዝነልናቸውም ነበር: አሁንም ነፃነት እና ለውጥ ፈላጊው የኤርትራ ህዝብ እንደሠውኛ በጣም ያሳዝናል:: ከጦርነቱ ማብቂያ አንስቶ ጠ/ሚ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ዐብይ አህመድ ወደስልጣን እስኪመጡ ድረስ ሻዕቢይ ግሎባላይዝድ ከሆነ ፕሮግሬሲቭ የዓለም ፖለቲካ ጋር አብራ መራመድ ያልቻለች: አፈና ያጎበጣት: ድህነት ያንበረከካት: ልጆቿ በየባህሩ የአሳ እራት የሆኑባት: የጡረተኞች ማማሻ ሆናለች። መሪዎቿ ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲና ብልፅግና ከማራመድ ይልቅ እንደግል ንብረታቸው እንደአባታቸው ርስት ሕዝቡን ጠርንፈው ይዘው ዲያስፖራውን ሳይቀር ግብር አንቀው እያስከፈሉ በየአውሮፓ እና አሜሪካ ከተሞች በግለሰብ ስም ሻዕብያ ከፍቷቸው ከሚሰሩ ሻይ እና ምግብ ቤቶች እንዲሁም መሸታ ቤቶች በሚቃረም ዶላር ምስር እና ዘይት ከአረብ ሀገር ጀሌዎቹ እየገዙ በንጉሱ የተከፈተውና በዘመኑ ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ያልተናነሰ reputation የነበረውን የአስመራ ዩኒቨርሲቲን እንኳን ዘግተው ከስደት የተረፈውን ወጣት ወደሳዋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እያጋዙ ኤርትራን 500 ዓመት ወደኋላ መልሰዋታል። ምፅዋን የሚያህል port city ዛሬ ፍርስራሹ ወጥቶ የዝንብ መጫወቻ ሆኗል። አሰብም ከዚያ ብዙ ይሻላል ለማለት አያስደፍርም። ጎረቤቴ በልቶ ከሚያድር እኔ ፆሜን ልደር ተብሎ! የኢኮኖሚ ነፃነት: የፖለቲካ ነፃነት: ምንም ዓይነት democratic progress የማይታይባት - ባለፉት 30 ዓመታት እንደሀገር የራሷን intellectual class እና ምንም ዐይነት ተተኪ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ elite ያልፈጠረች ይልቁንም መሪዎቿን በየሳምንቱ የምትቀብር ሀገር: ሀገር ከሆነች አንስቶ ከብሄራዊ ጦሯ እስከሚሊሻዋ በትግራይ ጦርነት ከኢትዮጵያ ተዘርፎ መሣርያ እስኪጋዝላቸው ዘመናዊ መሣርያ ያልታጠቀ ሰራዊት እና ከዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂዎች ጋር በጎሪጥ የሚተያዩ የጋርዮሽ ዘመን ተዋጊ የጦር ጄነራሎች የሚዘውሯት ሀገር: ዜጎቿ በስርዓቱ ተንገሽግሸው ኢትዮጵያ በሯን ገርበብ ስታደርግ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ወጣት እና አዛውንት አይንሽን ለአፈር ብሎ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሮጠባት ሀገር: የምን ነፃነት ቀን ይሆን የምታከብረው። እንደሀገር ቆምን ካሉበት ከ1984 እስከዛሬዋ ቀን ድረስ እራሳቸውን ከማስተዳደር ይልቅ.... ቀጣይ ገፅ ይመልከቱ
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹28,744 Aufrufe • vor 2 Jahren

እኔ በግሌ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 መሠረተ ልማት ባይገነባ ሀገር ባያለማ ከጠዋት እስከማታ ቢያሻው እግሩን ሰቅሎ ቢፈልግ ጋደም ብሎ የሚውል መሪ ቢሆን እንኳን እንደነዚህ ያሉ ገሚሱ በኦሮሞ በትግራይ እና በአማራ ሕዝብ ጫንቃ ታዝሎ ገሚሱ በኢትዮጵያዊነት ለምድ ተጀቡኖ የነበረ እና አሁንም እያላዘነ ያለውን አለሌ የስልጣን ጥመኛ ሁላ ለምዳቸው ተገፎ የጎጠኝነት ዛራቸው ተንገፍግፎ ተራግፎ አደባባይ እርቃናቸውን አጥቦ ጨምቆ ስላሰጣልን እና ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን እንደራስ ቅማል ተጣብቀው ደም የሚጠቡበትን በር ስለነፈጋቸው ብቻ እስከቀራንዮ እደግፈዋለሁ ። ነገሩ ግን ሰውየው (አቢቹ) Office of the Prime Minister - Ethiopia ልማቱንም እንክርዳድ ከስንዴ እየለዩ ሀገር ማጥራቱንም ከቴክኖሎጂው እስከ ዲፕሎማሲው እያሳለጠ እና በዐይነት በዐይነቱ እያቀላጠፈው እንኳን እዬዬን የትግል ስልት ላደረገው ጥራዝ ነጠቅ መርህ አልባ ተቀዋሚ ለደጋፊዎቹም የቱን ተናግረን የቱን እንደምንተው ግራ እስኪገባን ድረስ ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል ትንግርቱ! ወንበር ያፅና ብለናል‼️ ግን ግን ጀዌ ቀዌ Jawar Mohammed ምነው Tsegaye Ararssa Hᴇɴᴏᴋ G. Gᴀʙɪsᴀ ህዝቅኤል ጋቢሳ ምናምን የከሸፈው የናይሮቢው the so called የመፅሀፍ ምርቃት ፕሮግራምህ ላይ ጋብዘህ አዳዲሶቹን cheerleaderችህን Neamin Zeleke Mesay Mekonnen Andargachew Tsege ደረጄ ሀብተወልድ Dereje Habtewold እና መሰል የ ደረት ደቂዎቹን ማህበራት (ወ.ሸ.ፋ) ዎችን ዘነጋሀቸው? ሰብሰብ ብሎ ለመላዘኑ ጥሩ አጋጣሚ ነበር እኮ 🤔 ከኑማ‼️ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹23,041 Aufrufe • vor 1 Jahr

This chairperson of the African Union African Union says Djibouti is an Arab country, not an African one. Its one thing to acknowledge both African & Arab roots but the CP Mahmoud Ali youssouf says DJI is Arab for they are muslims, offering their country in a silver platter for Egypt to exploit. Hence his position on Somaliland as well. Most shocking was the fact that he justified the Houthi's attacks against trade shipments on the Red Sea, & mind you, the Houthi's have a transnational alliance with Al-Shabaab.
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹11,212 Aufrufe • vor 8 Monaten

እነኚህ የሀገር ሽማግሌዎች ሕዝባቸው በሰላም ማጣት ሳቢያ የሚከፍለውን አላስፈላጊ መከራን ለማቆም በመንግስት እና በሕዝብ መካከል ያለውን መግባባት በማጠናከር ሰላም እንዲመጣ ክልሉ ላይ ሠላም እንዲሰፍን የክልሉ ተወላጆች በራሳቸው ተነሳሽነት ተሰባስበው ከመድከም ውጪ ለዚህ ውርደት የሚያደርስ አንዳች ነውር የለባቸውም። የአማራን ሕዝብ ነፃ አወጣለሁ በሚል እንቶፈንቶ ሽፋን ኪሱን የሚያደልበው እና በአመፃ የሕዝብን መከራ ማራዘም የእንጀራ ገመዱ የሆነለት ፅንፈኛው የፋኖ ሽፍታ ነው ለምን ስለ ሠላም ሰራችሁ ብሎ ወልደው የሚያደርሷቸውን አባቶች እና እናቶች እንዲህ ኢሰብዓዊ እና ክብረነክ በሆነ መንገድ የሚያዋርዳቸው እና የሚያጎሳቁላቸው። እነኚህ ከዘመን ጋር የማይራመዱ ደም ያሰከራቸው ዕውቀት እና ምክንያታዊነት እንደሰማይ የራቃቸው ወሮበሎች ናቸው እንግዲህ የአማራ "ነፃ አውጭዎች" ሠላምን በዚህ መልኩ እየገፉ እና እየተፀየፉ ስለ ሠላም የሚሰብከውን በለው ግንባሩን እያሉ ይህን ቪድዮ አይተው እስክሪብቶ እና ወረቀት ይዞ ሠላምን ለማስፈን እየሰሩ ያሉ ወገኖችን ሳይሆን ብርጌድ የውጭ ወራሪ ጦርን የያዙ አስመስለው እየለፈፉ ያሉት ጉዶች ናቸው መንግስት ላይ ያላችሁ ቅሬታ ስትላቸው ያለማፈር የፕሪቶርያው የሠላም ስምምነት ላይ አልተወከልንም ብለው ሙሾ የሚያወርዱት! እንኳን ቀሩ እንጂ በዚህ አያያዛቸው የ86 ዓመቱን አዛውንት ፕሬዚደንት ኦባሳንጆንም ዳዴ ይበልልን የሚለውን ቀዳሚ መነጋገርያ አጀንዳቸው አርገው ይመጡ ነበር :) ሲጀመር እንደነዚህ ያሉ ሽፍቶችንስ ሆነ ኢሊቶችን በየቱኛው የህግ አግባብ ነው መንግስት ለድርድር የሚያስቀምጣቸው እራሳቸውንስ ምን አድርገው አስበው ነው ? ይህቺ እውነትን ሽሽት ለራስ ኢጎ ማስተንፈሻ እና መፅናኛ ትሆን ዘንድ እንደ ታብሌት እየቃሙ በብላሽ የሚቆለሏት ነገር ከመሳቅ አልፋ ታሳቅቃለች! ለማንኛውም የፌደራል መንግስቱ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 Office of the Prime Minister - Ethiopia በቁርጠኝነት ክልሉ ላይ የኃይል የበላይነቱን ለማስጠበቅ የሚሰራው እና የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንም ጥሻ ለጥሻ የሚሯሯጠውን ሽፍታ እግር በእግር እያደነ አደብ የሚያስገዛው የአማራ ክልል ነዋሪ እንደዚህ ያሉ retarded እና የማህበረሰቡን የሃይማኖት እና የሞራል እሴት ከመሰረቱ ያናጉ ደም ያሰከራቸው ጦረኞች እና በደሃ ደም እና እምባ የሚገኝ ስልጣን እና ሃብት በቁም የሚያቃዣቸው ጥራዝ ነጠቅ ጎጠኛ ኢሊቶች እጅ እንዳይወድቅ ነው!!! ቢመርህም ቢጎረብጥህም ሀቁ ይሄው ነው 🤷♀️ ከኑማ ‼️ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ENDF
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹23,061 Aufrufe • vor 2 Jahren

ዮናስ ብሩ Yonas Biru አንዳርጋቸው ፅጌ Andargachew Tsege ነአምን ዘለቀ Neamin Zeleke መሳይ መኮንን Mesay Mekonnen ደረጄ ሀብተወልድ Dereje Habtewold እዚህ ውስጥ ስማቸውን ያልጠቅስኳቸውን አግድም አደግ #ArmChairWarlords የዩቲዩብ ጭራ ቀረሾች ጓዶቻችሁንም ሠብሰብ አድርጋችሁ ይህቺን እራት ተቋደሱልኝማ! “እሱ አይናገር እንጂ ከተናገረ" አልያም "እሱ አይፃፍ እንጂ ከፃፈ" ብለን በአክብሮት ስማቸውን ከምንዘረዝራቸው social criticዎች መካከል አንዱ የሆነውን የሀገር ምልክት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን Daniel Kibret እንዲሁም እዩኝ እዩኝ የማይለውን: ዘር ከልጓም የማይስበውን በጭብጨባ የማይኮፈስ በነቀፌታም የማይበረግግ ልበ ሙሉው የጋዜጠኞች ፈርጥ ሲሳይ አጌናን Sisay Agena እናመሰግናለን ኢትዮጵያ ታመሰግናችኃለች‼️ ዱቢን ከኑማ እውነቱ ይሄው ነው‼️ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹15,578 Aufrufe • vor 1 Jahr

እውነቱ ይሄው ነው‼️ Kanuma dubbin ‼️ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ENDF
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹13,577 Aufrufe • vor 1 Jahr

አንዳንዱ ወጣት በደም ፍላት ወይም በዕድሜው አፍላነት: ባለመብሰል: ነገሮችን ባለማገናዘብ: ወይም ተግቶ ያደገው ዘረኝነት እያገረሸበት የሚያሳየውን ጋጠወጥ የፖለቲካ ባህል በተወሰነ ደረጃ መረዳት ይቻላል። ለሰውም ለእግዜርም የቸገረው ነገር ዕድሜ የማያስተምረው እና መማር እና በሰለጠነ ሀገር መኖር የማይለውጣቸው ቆሞቀሮች እና ዓለምን ክዳችሁ ተከተሉኝ ያላቸውን አምላክ "ጎጤን ብቻ አንጠልጥዬ" ብለው ከአቅማቸው በላይ የተሸከሙት የጵጵስና/ቅስና/ድቁና ማዕረግ እና ከትከሻቸው ክብር እጅግ የከበደ ልብሰ ተክህኖ የደረቡ ፋኖነት እና ኦርቶዶክሳዊነት የተምታታባቸው (አንዳንዶቹም በግዜው የሀይማኖት መሪዎች ውትድርና የመዝመት ግዴታ ስላልነበረባቸው: የደርግን ብሄራዊ የውትድርና ግዳጅ ለመሸሽ የቆቡ ክብር ሳይገባቸው የመነኑ) "አባቶች" ናቸው። በእንደነዚህ አይነቶቹ ሀይማኖትን ተገን አድርገው ፓለቲካ በሚሸቅጡ የሀይማኖት መሪዎች ምክንያት ቢቀርብኝስ ብሎ ከ ደጀ ስላም የቀረውን ምእመን ቤት ይቁጥረው: እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊት የመስቀሉ ስር የፖለቲካ ቁማርተኞችን ስመለከት ስለ እነርሱ እኔ እሸማቀቃለሁ:: በደርግ ዘመን ነው አሉ - አንድ ወዳጄ ሲያወጋኝ - የኢህአፓ ዋና ማዕከል የሚገኝበት እና ቆንጆ ሴት ለመወዳጀት ወጣቱ የሚያዘወትርበት ቀበሌ 28 አደሬ ሰፈር ነበረ። ታድያ በወቅቱ ዋና መሰባሰቢያውን እዛው ሠፈር ያደረገው ኢህአፓ የኡኡታ ኮሚቴ የሚባል ጩኸት የሚያስተባብር ቡድን ያዋቀራል። እናማ: ኮሚቴው በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ሌሊት ላይ ሠው ሁሉ በሩን ዘግቶ እዚህ ቪድዮ ላይ እንዳየናቸው ዕድሜ ሽበት እና ቁጥር ብቻ የሆነላቸው ሴት "ኡኡኡኡኡኡኡኡ አለቅን ሠው አለቀ" እየተባለ ይጮህ ነበረ:: ለማን እና ለምን እንደሚጮሁ ባይገባውም አብዛኛው ሰው በሩን ዘግቶ ኡኡኡኡኡ አለቅን እያለ አብሮ እሪታውን ያቀልጠው ነበር:: ደርግ በጩኸት ይፈርስ ይመስል! አሁንም ታዲያ የኛ ሰው ከትላንት አይማርም። ከቅርብ ግዜ ትዝታችን ካየነው ከኖርነው እና ከሰማነው የትግራይ ጦርነት እና የወያኔ ደጋፊዎች ልምድ አይቀስምም ። በዚህ አጋጣሚ የወያኔ ደጋፊዎች በስንት ጣዕማቸው: ፕሮፓጋንዳንማ እነሱ ይስሯት ፐፐፐፐ 🙄 ለማንኛውም እንዲህ ያለው እርባና ቢስ ኡኡታ እና ያዙኝ ልቀቁኝ ራስን ከማስገመት: ከመቅለል እና መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆን ውጪ ምንም አይፈይድም: ያውም ከዓባይ በረሃ ማለፍ ላልቻለ በየስራስሩ እየተንደፋደፈ ደሀ ወገኑን ለሚዘርፍ: ሴቶችን ለሚደፍር እና የገዛ ወገኑን ለሚያጎሳቁል የሽፍታ ስብስብ!!! ባይሆን እንደደርግ እና እንደወያኔ ወጣቱን የአፈሙዝ እራት አታድርጉት! የኢትዮጵያ እናት ስንት ሆና እንደምታሳድግ ዛሬ ላይ ሺህ ግዜ በሰው ሀገር ቢፏለል አይረሳም። ግፍን ፍሩ! አመፃን ፍሩ! አልያም የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ብላችሁ የልጅ ልጆቻችሁን ጭምር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን እጯጯህ እያሰለጠናችሁ ስለሆነ ኡኡኡታም በቅርስ ባላደራ አማካኝነት የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ይመዘገብላችሁ ዘንድ አቤቱታችሁን ታቀረቡ ይሆን 🤔 ከኑማ ‼️ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹16,726 Aufrufe • vor 2 Jahren

በወረኃ ጥቅምት የኢትዮጵያ "ነጩ ቤተመንግስትን በጎበኘን ግዜ‼️ 1/2 ቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ ለ25ኛ የንግስና የብር ኢዮቤልዩ በዓላቸው ሲባል ያስገነቡት የህንጻ ጥበብ ያረፈበት በ1941 ዓ.ም ተጀምሮ በ1948 ዓ.ም ግንባታው የተጠናቀቀው ይህ ቤተመንግስት ለ ቀ.ኃ.ስ መኖሪያቸው ብቻ ሳይሆን ዘውዳዊ አስተዳደራቸውን ከረዳቶቻቸው ጋር ሆነው የመሩበት ታላላቅ እንግዶችን እየተቀበሉ ያስተናገዱበት ነው: በ ቀ.ኃ.ስ ዘውዳዊ ስርዓት ፍጻሜ ወቅትም የደርጉ አባላት በ ቮልስ ዋገን ተሸከርካሪ ጭነው ያወጧቸውም ከዚሁ ከኢትዮጵያ ነጩ ቤተመንግስት ውስጥ ነበር: የህወኃት/ኢህአዴጉ ዘመን የቀድሞው ፕሬዚደንት ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ከ1987 እስከ 1994 ዓም ድረስ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የኖሩበትን ይህን ቤተመንግስት በሚመለከት በ’’ዳንዲ የነጋሶ መንገድ’’መጸሐፋቸው ሲገልፁት በዚህ ቤተመንግስት ውስጥ ምቾት እንደማይሰማቸውና ሌላው ቀርቶ ‘’ አይጦች‘’ እና ‘’ፍሳሽ ‘’ያስቸግሯቸው እንደነበር መግለጻቸውን ልብ ይሏል፡ የዕደሳት ስራው ተጠናቆ የተመረቀው ይህ ታላቁ ቤተመንግስት/ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት በገዘፉ ነባር ዛፎች: በአረንጓዴ ተክል ተውቦ በውስጡ ታቅፎት የኖረው ለማመን የሚከብድ የሀገር ሀብትና የታሪክ አሻራን ውድና ምስጢራዊ የቤተመንግስቱን ሀብቶችን ማየት ብቻ ኢትዮጵያ ምን ያህል በዓለም ታላላቅ መሪዎች ዘንድ የተከበረች ሀገር መሆኗን የሚያረጋግጡ ናቸው:: ይህ ቤተመንግስት በውስጡ ከብዙ ሀገራት በስጦታ መልክ የተበረከቱ እፁብ ድንቅ የሆኑ ገፀ በረከቶችን ከአሜሪካው የወቅቱ ዝነኛ ፕሬዚደንት ሮዝቬልት እስከ እንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርችል፣ ከዩጎዝላቪያው ጀግና መሪ ፊልድ ማርሻል ቲቶ እስከ ግብጹ ፕሬዚደንት ገማል አብደል ናስር ድረስ በስጦታ የቀረቡላቸው ውድ ስጦታዎች÷የቅንጦት የባቡር ፉርጎዎች፣በልዩ ሞዴል የተሰሩ ተሸከርካሪዎችና ሌሎች ድንቅ ስጦታዎች የእንግሊዟ ንግስት የሸለመቻቸው ውድ ሰረገላዎችም እጅግ የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ታዲያ ይሄንን የሀገር ሀበት በውስጡ የያዘውን እና ለመፍረስ የተቃረበውን ይህን ቤተመንግስት ለማደስ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግስትOffice of the Prime Minister - Ethiopia የወሰደውን ፈጣን እርምጃና የደረሰበትን ውሳኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው በሚመሩት የልዩ ልዩ ባለሙያዎች በየደረጃው የተዋቀረ ኮሚቴ እንቅስቃሴ በአስጎብኝዎቻችን ሲገለጽ መስማትና አስደማሚውን የግንባታ ሂደት ተዘዋውሮ መመልከት በእርግጥም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 ኢትዮጵያ በፈተና ወቅት ያገኘቻቸው ድንቅ መሪ መሆናቸውን ለማመን እና ለመመስከር ንጹህ ህሊና ብቻ በቂ ነው፡፡የቀድሞው የኢዮቤልዩ ቤተመንግስትና በደርግ አዲስ ስያሜ ብሄራዊ ቤተመንግስት የተባለው ይህ ቤተመንግስት የተሸከመው በዋጋ የማይተመን ብርቅና ድንቅ ቁሳዊና ታሪካዊ ሀብት በወጉ ተደራጅቶ ለህዝብ እይታ ይበቃ ዘንድ የተደረሰበት ውሳኔ የሚያስደምም ነው፡፡በተለይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተመንግስት ተሸከርካሪዎችና የባቡር ፉርጎዎች፣ ሰረገላዎችና ሌሎች በቅርስነት የተመዘገቡ ንብረቶች በጥንቃቄ የሚቀመጡበትና ለዕይታ ክፍት የሚሆኑበት የተሸከርካሪ ማቆሚያ ህንጻ በአፍሪካ ውስጥ የሚወዳደረው እንደሌለ ሲነገር እንደመስማት እና እንደማየት ከቶ የሚያስደስት ነገር ምን አለ? በአስጎብኝዎቻችን ከተገለጹልን ሌሎች አስገራሚ ነገሮች ጥቂት ፡፡ጽ/ቤቱን በዚሁ ‘’የኢትዮጵያ ነጩ ቤተመንገስት ‘’ውስጥ ያደረገው የኢፌዲሪ ቤተ መንግስት አስተዳደር በስሩ ዘጠኝ ታሪካዊ ቤተመንግስቶችን እንደሚያስተዳድር ምን ያህሎቻችን እናውቃለን? አብዛኛዎቹ የሚገኙት ደግሞ በየክልሎች ውስጥ መሆኑ ደግሞ ልብ ያሞቃል፡ ስለ ቤተ መንግስት ሲነሳ ሁላችንም በዓዕምሯችን የሚመጣው የጎንደሩ ፋሲለደስና የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስቶች ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን የጎንደሩ ፋሲል ቤ/መ ሆነ ጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት፣ወይም የወሎው የንጉስ ሚካኤልና የልኡል አልጋወራሽ አስፋወሰን ኃይለስላሴ ቤተመንግስቶችም ከዘጠኙ ውስጥ የሉበትም! ይቀጥላል…Al Mariam Abe Tokichaw Jony #Saynomore
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹12,595 Aufrufe • vor 1 Jahr

ዩቲዩበር መዓዛ መሃመድ Meaza Mohammed የምሁር መጥፋት ያገነናት የጠበበው የብሄር ፖለቲካ እንደዋርካ የሰፋ ዕውቀት ያላቸውን ተፍቶ እንደሷ ያለውን 3rd rate አውርቶ አዳሪ ከሰው ተርታ የመደባት ጥራዝ ነጠቅ ናት! ሴትዮዋ አፏ በተላቀቀ ቁጥር ዕውቀት እና ዕውነት ዓይንሽ ለአፈር ያሏት መሃይም የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛ መሆኗን ግራ ቀኝ ማየት የሚችል የሚሰራ ጭንቅላት ያለው ሁሉ የማይክደው ሀቅ ነው። በትግራይ ጦርነት ወቅት አማራን 27 ዓመት አንገቱን አስደፍቶ ዘሩን ሲያፀዳው ታሪኩን ሲቀብረው ማንነቱን ሲያዋርደው የኖረውን ወያኔን በአንቀልባ አዝሎ ዐባይን እንዲያሻግረው ያለ ሀፍረት የሲ.አይ.ኤ civilian foreign agents የነፍስ አባት የሆነው @NEDemocrarcy በአደባባይ በሚደጉመው የዩቲዩብ የሚዲያ ገጿ ስትለፍፍ ከርማለች! አሁን ደርሳ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆና ለምን ብሎ የማይጠይቅ መንጋ አግኝታ የአማራ ትግል ምልክት ሆና ለመውጣት ትጋጋጥ ይዛለች! ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ ማለት ይሄኔ አይደለ! የሆነው ሆነና እቺው "ጨዋ" ሴት (ጨዋ በጎጃም አፍ መሃይም ማለት መሆኑን ልብ በሉልኝ): ተርቦ እህል እንዳየ ሰው የጎፈንድሚ ዶላር ለመቀራመት እና የግል ኢጎው እያንገራገጨው ሲገፋፋ እና ሲዘነጣጠል የሚውለው ስፍር ቁጥር የሌለው ለአማራ ነው የምንታገለው ባዩ የርቀት "አታጋይ" ዲያስፖራ መሃል ተቀባይነት ለማግኘት የኦሮሞ ተወላጅ ከሆኑ ፖለቲከኞች አልፋ ሕዝብን እንደማህበረሰብ ባልተገራ አንደበቷ ለመዝለፍ እየዳከረች ራሷን ማዋረዷን ቀጥላለች! ዳሩ ቅሉ: እሷ ከወሎ - ያውም ከሙስሊም ቤተሰብ ሆና አሁን ያለው የአማራን ሙስሊም ያገለለው አልፎም የሚያጠቃው ጎጃም መሩ የምስለኔው የ አማራ ትግል የሚባለው ደግሞ ነውሩን በቤተክርስትያን ክብር ለመሸፈን የሚጋጋጥ አክራሪ ኦርቶ-ማራ! ወትሮም ለራሱ ጥቅም ሲፈልገው ብቻ ካልሆነ ለወሎዬ ክብር የለውም : የእሷ የእምነት controversy ሲጨመርበት በእነርሱ ዐይን she is not even qualified to join let alone to lead it😂 ለዚያ ነው ይሄ ሁሉ መዘላበድ! እንደኔ እንደኔ ግን ዝም ብላ ስለLiposuction, ስለ weightloss surgery, ስለFacial ምናምን video እየሰራች እና ልምዷን እያካፈለች: influencer ሆና ብትቀጥል ባይ ነኝ! ያው ለደሃ ከተሰበሰበው ገንዘብ እነሱ ያለማፈር እየተሽሞነሞኑበት ( ፈርሰው እየተሰሩበት) እኛም እየታዘብን እስከመቼ?! የሰጪውስ ድንቁርና እናንተዬ! አበስኩ!!! በሉ እስቲ ይህቺን ለወይዘሪት/ሮ መዓዛ አድርሱልኝማ ከኑማ‼️ ነጋቲ ቡላ!!! #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹13,876 Aufrufe • vor 2 Jahren

The Ethiopian Grand Renaissance Dam #GERD recently welcomed visits from religious leaders and renowned athletes, highlighting its significance not just as a source of power but as a symbol of national pride, unity, and self reliance. Their visit underscores the monumental achievement of the Ethiopian people, who came together to make this dream a reality. Built entirely with the contributions of Ethiopians children, the elderly, the poor, and the rich alike the dam stands as a testament to the country’s determination and resilience. Despite immense pressure from Western powers favoring Egypt, Ethiopia made great sacrifices to complete this historic project. Ethiopia’s right to use its own resources and its fair share of the Abay (the Nile River) has long been undermined and misunderstood, as if Egypt owns the water a complete lie. Ethiopia contributes more than 85% of the Nile’s water through its rivers, yet it has historically been denied equitable access. GERD is a declaration of Ethiopia’s sovereignty and its rightful claim to utilize its resources for the benefit of its people. I am so glad to see that it’s finalized. GERD is a shining example of what Ethiopians can achieve when united for a common purpose. #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ItsMyDam
Kiya Negash /ታይሲ/ የ ኢትዮጵያ ካድሬ🇪🇹🇪🇹🇪🇹10,968 Aufrufe • vor 1 Jahr