Adebabay Media's banner
Adebabay Media's profile picture

Adebabay Media

@AdebabayMedia • 26,496 subscribers

https://t.co/BmtzJm0S7q https://t.co/14wbgadyHp Retweets are NOT endorsements. አደባባይ ሚዲያ:- የሁላችን ስለሆነች ኢትዮጵያ ።

Shorts

ሰበር ያልሆነ ሰበር ዜና (UPDATED News) ++++ (አደባባይ ሚዲያ፣ ሐምሌ 6/2015 ዓ.ም፤ July 13/2015) ትላንት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደኅንነት ተይዘው የነበሩት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተለቀው ወደ ቦሌ የአገር ውስጥ በረራ ተርሚናል እያመሩ እንደኾነ እማኞች ገልጸዋል። ትላንት ማለዳ 11:00 ላይ ከኖሩበት አውስትራልያ ተነሥተው ዐዲስ አበባ ደርሰው የመቐለን የትራንዚት በረራ እየተጠባበቁ እያሉ በኤርፖርቱ ደኅንነት ለጥያቄ በሚል ከተያዙ በኋላ፣ ለኹለት ጊዜያት ያህል ወደ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት እየተወሰዱ ተመልሰዋል። በአገር ውስጥ ለመቆየት እንዳልተፈቀደላቸውና ወደ መጡበት አልያም ወደ ሌላ ወደፈለጉት ሀገር እንዲመለሱ ቢጠየቁም፣ "በጦርነቱ የተጎደቱን ልጎበኝ ነው የመጣኹት" በሚል እምቢታ ማደራቸው ታውቋል። አባ ሠረቀ ብርሃን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ይፈጸማል፤ ተብሎ የሚጠበቀው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ላይ ለመገኘት ከአውስትራሊያ እንደመጡ ይታወቃል። አነጋጋሪ ጉዳዮችን በመናገር የሚታወቁትና "የመንበረ ሰላማ" ዕቅድ አባት የሚባሉት አባ ሠረቀ፥ ኢትዮጵያን ጋለሞታ፣ ኤልዛቤል፣ ጣዖት፣ የተረገመች ሀገር... በማለት የሚጠሩ ሲሆን፣ ዐማራውን በጅምላ "ትውልደ ነገድ የሌለው ጥርቅም ሕዝብ" በሚለው ጸያፍ ንግግራቸው ይታወቃሉ።

27,362 views

Videos

No more content to load