
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
@EliasMeseret • 233,151 subscribers
Editor-in-Chief @AmjamboAfrica, Founder @MeseretMedia and @EthiopiaCheck, Former @AP reporter in Ethiopia
Shorts
Videos

ከሀገራችን አልፎ ከሶማልያ እስከ ምፅዋ ድረስ ሰላም የማስፈን አቅም ያለው ብቁ ሀይል (elite force) ተዘጋጅቷል ሲባል በቅርቡ ሰማን፣ እዚሁ ጉያችን ስር አርሲ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈፀመውን የንፁሀን ግድያ ማስቆም እንዴት አቃተ? ከትናንት በስቲያ ብቻ እዛው አርሲ ውስጥ 30 ገደማ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ሞትን ተላምደን ነፍስ ይማር ማለት እንኳን እየከበደን ነው። እየሆነ ያለው ነገር እጅግ ያሳዝናል!
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ19,874 Aufrufe • vor 4 Monaten

በቅርቡ በቦሌ አየር ማረፊያ ባሉ አካላት "የያዝሽውን ጌጣጌጥ እና ዶላር አካፍዪን" ስለተባሉ አንድ መንገደኛ መረጃ አቅርቤ ነበር። በዚህ ቦታ የሚደረገው ግፍ እና እንግልት እንደቀጠለ ማሳያ የሆነ ይህን በአቶ ነብዩ ሲራክ የቀረበ ሌላ ተመሳሳይ መረጃ ላጋራችሁ (ቪድዮው ተያይዟል)። በነገራችን ላይ በቅርቡ ያጋራሁትን መረጃ ተከትሎ: - ውጭ ሀገር ለመሄድ አዲስ የሆኑ እና የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እስከ 150,000 ብር ኤርፖርት እየተጠየቁ እንደሆኑ (በተለይ ወደ አረብ ሀገራት ለስራ የሚሄዱ እህቶች)፣ - አንዳንዶች ድብደባ እና የፆታ ትንኮሳ እንደደረሰባቸው፣ - በፍተሻ ወቅት "አውሮፕላኑ ሄዷል፣ አትገቡም" እና "የምናጣራው ነገር ስላለ መሳፈርያ ግዜ ይረፍድባችኋል፣ ስለዚህ ገንዘብ አምጡ እና እናሳልፋችሁ" የተባሉ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተደጋጋሚ፣ ተመሳሳይ መልዕክቶች ደርሰውኛል። አሁን የእኔ ጥያቄ እና ስጋት... "በጥቅም የሚሰሩ እነዚህ ሰዎች ደጎስ ያለ ገንዘብ ቢሰጣቸው ሀገር እና ህዝብ ላይ አደጋ የሚያስከትል ነገር ከማድረግ ይመለሳሉ ወይ?" የሚለው ነው። አሁንም በፍጥነት ይታሰብበት። ህዝብ ተበደልን፣ መረረን፣ ስለቸን እያለ ነው።
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ76,212 Aufrufe • vor 2 Jahren

ጋዜጠኝነት! ይህ ከሰሞኑ የክብር ሜዳልያ የተሸለመ የኢቢሲ ጋዜጠኛ (ዜና አንባቢ) የሚለውን እንስማው እስቲ። "ጋዜጠኝነት እውነትን መናገር አይደለም... በየትኛውም አለም እውነትን የሚናገር ጋዜጠኝነት ኖሮ አያውቅም።" እኔ ግን እላለሁ... ያላጎበደደ እና ለሙያው የታመነ ጋዜጠኛ እና ጋዜጠኝነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም ዙርያ ሞልቷል፣ ወደፊትም ይኖራል። ይህ ንግግር የተደረገው ደግሞ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ፊት መሆኑ ያሳዝናል። ሌላ መረጃ፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የትግራይ ህፃናትን ፎቶ ጭምር እየለጠፈ "ጁንታ" በማለት፣ የውጭ ሚድያዎች እና የበጎ አድራጊ ድርጅት ሰራተኞች ላይ በፌስቡክ ገፁ አመፅ ሲያነሳሳ እና ለእስር እና ለስደት እንዲዳረጉ ሲያረግ የነበረው ሌላኛው የኢቢሲ ጋዜጠኛ አስማማው አየነው ፍርድ ማግኘት ሲገባው VOA ገብቷል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የውጭ ሚድያ ላይ ስራ ሲያገኙ ደስ ይላል፣ እኔም የስራ እድል በሰማሁ ግዜ እያበረታታሁ የተቀጠሩ ሞልተዋል። ይህን ድርጊት ሲፈፅም የነበረ ይህ ግለሰብ ጉዳይ ግን ቢያንስ ህዝብ ሊያውቅ ይገባል። ይህ ጋዜጠኛ አብዛኛው እነዚህን ጉዳዮች ሲፅፍበት የነበረውን የፌስቡክ ገፁን ቆልፎ ሌላ አዲስ ከፍቷል። ይሁንና ምድራዊ ፍትህ ባይገኝ የሰማዩ ይኖራል። አይቼ እንዳላልፍ የምወደውና ብዙ ያየሁበት ሙያዬ ነው፣ እንዲህ አይነት ንግግሮችን እና ድርጊቶችን ሳይ ዝም ማለት ይከብዳል።
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ71,621 Aufrufe • vor 2 Jahren

Several residents in Southern Ethiopia reported witnessing a massive phenomenon in the sky earlier tonight, around 7:30 PM local time. One resident from the Dimtu area in West Guji told me: "It appeared to be huge, and the sound was terrifying. It seemed like it was falling from the sky, and we were all watching in amazement." I’m sharing this in the hope that those with expertise in such matters can provide more information. Ethiopian Space Science Society NASA European Space Agency РОСКОСМОС P.S.: In recent days, space debris fell in a rural village in Kenya. I'm unsure if this is a similar phenomenon.
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ43,237 Aufrufe • vor 1 Jahr

#ሀቅ ይህንን ቪድዮ ከአመታት በፊት እንዳየሁት ባስታውስም ከሰሞኑ ቲክቶክ ላይ በስፋት ሲዘዋወር ተመለከትኩት እና ላጋራው ፈለግኩ። ኢህአዴግ ዴሞክራሲያዊ ያልነበረ እና አሁን ላሉ አንዳንድ ችግሮች ጭምር ምንጭ እንደነበር ይታወቃል፣ መሪዎቹም ለዚህ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ የማይካደው ሀቅ ግን የፓርቲው እና የሀገሪቱ መሪ የነበሩት የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ መለስ ዜናዊ world class አእምሮ እና እውቀት ያላቸው መሪ ነበሩ። ዴሞክራሲን በማስፋት ዘርፍ "የጋን ውስጥ መብራት" የነበሩ ናቸው ማለት ቢቻልም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቻ ሳትሆን በአለም እጅግ ፈጣን እድገት ካላቸው ሀገራት ተርታ ነበረች፣ እንደዛሬው ቢያንስ ሰው በቁሙ ሲቃጠል፣ ሲገደል እና ሲታገት በየቀኑ አንሰማም ነበር።
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ62,480 Aufrufe • vor 3 Jahren

በአንዳንድ ጋጠወጥ የፖሊስ አባላት ህዝብ ላይ የሚፈፀም ድብደባ፣ እስር፣ ማንገላታት እና እስራት እየተበራከተ መጥቷል። ማንም ወንጀል ሰርቷል ተብሎ የተጠረጠረ ሁሉ ተይዞ ወደ ህግ ቦታ ሊወሰድ ይገባል እንጂ አይቀጠቀጥም። ከህዝብ ጋር እልህ የተጋቡ የሚመስሉ እነዚህ ፍጡሮች ዛሬ ተይዘው ነገ ይለቀቃሉ፣ ይህ በችግር የሚማቅቅ ህዝብ ምን አርጓቸው ነው? ሌላ ሀገር ፖሊስ ሲመጣ፣ ሲታይ ህዝብ ደህንነት ይሰማዋል። እኛ ሀገር በተቃራኒው ህዝብ እንዲፈራ እየተደረገ ነው። ይህ ነገር ውሎ አድሮ ሌላ ችግር ሳያመጣ መንግስት ለፖሊስ አባላት በተሻለ መልኩ ስልጠና ይስጥ፣ ይምከር።
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ11,449 Aufrufe • vor 3 Monaten

የዚህች ህፃን ልጅን ለቅሶ ተመልከቱ...! ጎንደር አካባቢ ይቺን ልጇን ይዛ ወላጆቿን ለመጠየቅ የሄደች እናት ከቤተሰቦቿ ቤት ታግታ ተወስዳ 1 ሚልየን ብር ተጠይቆባታል። ህፃኗ እንዲህ ስታለቅስ ውላ ታድራለች፣ ቤተሰብ እንኳን 1 ሚልየን ብር ኖሮት ሊከፍል ብሩ ሲጠራ እንኳን ምን ያህል ገንዘብ እንደሆነም አያውቁም። ድሀው ህዝብ እንዲህ እየተሰቃየ እየኖረ ነው። በእውነት ይደክማል! Via መሠረት ሚድያ/ነብዩ ሲራክ
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ25,571 Aufrufe • vor 1 Jahr

#ውሸትመልክቢኖረው ከፃፈው ኖት እያነበበ..."አንገቱ በማርያም፣ ሌላው አካሉ በሚካኤል ነው የተቀበረው" እምብርቱስ? 😅😅
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ11,818 Aufrufe • vor 3 Jahren
Keine weiteren Inhalte verfügbar
