ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ's banner
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ's profile picture

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

@EliasMeseret233,151 subscribers

Editor-in-Chief @AmjamboAfrica, Founder @MeseretMedia and @EthiopiaCheck, Former @AP reporter in Ethiopia

Shorts

2 ቢልየን ብር የሚሸጥ የሆስፒታል መሬት አፈፍ ያረገ ሰው አሸዋ መድፊያ አይቸግረውም እኮ! አፍንጫ ዳበስ፣ ዳበስ አይሰራም። አሁን የጋንዲ ሆስፒታልን መሬት ትመልሳለህ ወይስ አትመልስም? ልጅቷ ግን... "ከንክኖሀል" 😂

2 ቢልየን ብር የሚሸጥ የሆስፒታል መሬት አፈፍ ያረገ ሰው አሸዋ መድፊያ አይቸግረውም እኮ! አፍንጫ ዳበስ፣ ዳበስ አይሰራም። አሁን የጋንዲ ሆስፒታልን መሬት ትመልሳለህ ወይስ አትመልስም? ልጅቷ ግን... "ከንክኖሀል" 😂

27,614 görüntüleme

አንዱ ይህን ብልዜማ ሰውዬ አይቶ "Hybrid" ሲለው ሌላኛው ደግሞ "ኮሚሽን ከሁለት ቦታ ስትቀበል" ብሎታል። ግን ኑሮ ህዝቡን እንዲህ ናላውን አዙሮታል፣ አትሳቁ 😊

አንዱ ይህን ብልዜማ ሰውዬ አይቶ "Hybrid" ሲለው ሌላኛው ደግሞ "ኮሚሽን ከሁለት ቦታ ስትቀበል" ብሎታል። ግን ኑሮ ህዝቡን እንዲህ ናላውን አዙሮታል፣ አትሳቁ 😊

17,391 görüntüleme

Videos

EliasMeseret's profile picture

በቅርቡ በቦሌ አየር ማረፊያ ባሉ አካላት "የያዝሽውን ጌጣጌጥ እና ዶላር አካፍዪን" ስለተባሉ አንድ መንገደኛ መረጃ አቅርቤ ነበር። በዚህ ቦታ የሚደረገው ግፍ እና እንግልት እንደቀጠለ ማሳያ የሆነ ይህን በአቶ ነብዩ ሲራክ የቀረበ ሌላ ተመሳሳይ መረጃ ላጋራችሁ (ቪድዮው ተያይዟል)። በነገራችን ላይ በቅርቡ ያጋራሁትን መረጃ ተከትሎ: - ውጭ ሀገር ለመሄድ አዲስ የሆኑ እና የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እስከ 150,000 ብር ኤርፖርት እየተጠየቁ እንደሆኑ (በተለይ ወደ አረብ ሀገራት ለስራ የሚሄዱ እህቶች)፣ - አንዳንዶች ድብደባ እና የፆታ ትንኮሳ እንደደረሰባቸው፣ - በፍተሻ ወቅት "አውሮፕላኑ ሄዷል፣ አትገቡም" እና "የምናጣራው ነገር ስላለ መሳፈርያ ግዜ ይረፍድባችኋል፣ ስለዚህ ገንዘብ አምጡ እና እናሳልፋችሁ" የተባሉ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተደጋጋሚ፣ ተመሳሳይ መልዕክቶች ደርሰውኛል። አሁን የእኔ ጥያቄ እና ስጋት... "በጥቅም የሚሰሩ እነዚህ ሰዎች ደጎስ ያለ ገንዘብ ቢሰጣቸው ሀገር እና ህዝብ ላይ አደጋ የሚያስከትል ነገር ከማድረግ ይመለሳሉ ወይ?" የሚለው ነው። አሁንም በፍጥነት ይታሰብበት። ህዝብ ተበደልን፣ መረረን፣ ስለቸን እያለ ነው።

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

76,212 görüntüleme • 2 yıl önce

EliasMeseret's profile picture

ጋዜጠኝነት! ይህ ከሰሞኑ የክብር ሜዳልያ የተሸለመ የኢቢሲ ጋዜጠኛ (ዜና አንባቢ) የሚለውን እንስማው እስቲ። "ጋዜጠኝነት እውነትን መናገር አይደለም... በየትኛውም አለም እውነትን የሚናገር ጋዜጠኝነት ኖሮ አያውቅም።" እኔ ግን እላለሁ... ያላጎበደደ እና ለሙያው የታመነ ጋዜጠኛ እና ጋዜጠኝነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም ዙርያ ሞልቷል፣ ወደፊትም ይኖራል። ይህ ንግግር የተደረገው ደግሞ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ፊት መሆኑ ያሳዝናል። ሌላ መረጃ፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የትግራይ ህፃናትን ፎቶ ጭምር እየለጠፈ "ጁንታ" በማለት፣ የውጭ ሚድያዎች እና የበጎ አድራጊ ድርጅት ሰራተኞች ላይ በፌስቡክ ገፁ አመፅ ሲያነሳሳ እና ለእስር እና ለስደት እንዲዳረጉ ሲያረግ የነበረው ሌላኛው የኢቢሲ ጋዜጠኛ አስማማው አየነው ፍርድ ማግኘት ሲገባው VOA ገብቷል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የውጭ ሚድያ ላይ ስራ ሲያገኙ ደስ ይላል፣ እኔም የስራ እድል በሰማሁ ግዜ እያበረታታሁ የተቀጠሩ ሞልተዋል። ይህን ድርጊት ሲፈፅም የነበረ ይህ ግለሰብ ጉዳይ ግን ቢያንስ ህዝብ ሊያውቅ ይገባል። ይህ ጋዜጠኛ አብዛኛው እነዚህን ጉዳዮች ሲፅፍበት የነበረውን የፌስቡክ ገፁን ቆልፎ ሌላ አዲስ ከፍቷል። ይሁንና ምድራዊ ፍትህ ባይገኝ የሰማዩ ይኖራል። አይቼ እንዳላልፍ የምወደውና ብዙ ያየሁበት ሙያዬ ነው፣ እንዲህ አይነት ንግግሮችን እና ድርጊቶችን ሳይ ዝም ማለት ይከብዳል።

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

71,621 görüntüleme • 2 yıl önce

Daha fazla içerik yok.