
Sahle-Work Zewde
@SahleWorkZewde • 612,497 subscribers
Former First Woman and Fifth President of Ethiopia 25 Oct 2018 - 07 Oct 2024
Shorts
Videos

የናሚብያ የመጀመርያ የሴት ፕ/ት ቃለ መሃላ ፈጽሙ! ለዚህ ታሪካዊ ቀን ከተጋበዙት የቀድሞ ሴት ፕ/ቶች መካከል ነበርኩ! በአፍሪካ 2 ሴት ፕ/ቶች አሉ:: ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል ሴት ም/ፕ/ት ሾመዋል:ከ24 ወደ 14 የተቀነሰው ካቢኔ ውስጥ 8ቱ ሴቶች ናቸው! ሴቶች አብላጫ የሆኑበት ብቸኛ ካቢኔ ነው። አገራቸውን ከቅኝ አገዛዝ ለማላቀቅ ታግለዋ: ታስረዋል:ተሰደዋል። አገራችንና ላይቤርያ የናሚብያን ቅኝ ገዢ ዘረኛው የደቡብ አፍሪካን መንግሥት ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የወሰደች፣ የትግሉ መሪ ፕ/ት ሳም ንዮማ በኢት/አየር መንገድ አገራቸው የመለሰች፣ ነጻ አውጪ ግንባሩ ስዋፖ በአአ ጽ/ቤት እንዲኖረው፣ አባላቱ እንዲሠለጥኑ …ያደረገች፣ አጋርነትን በተግባር ያሳየች፣ ትልቅ ከበሬታን ያተረፈች ታላቅ አገር ነች።
Sahle-Work Zewde14,606 görüntüleme • 1 yıl önce
Daha fazla içerik yok.