Video yükleniyor...

Video Yüklenemedi

Ana Sayfaya Dön

እየተስፋፋ የመጣው የገጠር ኮሪደር

31,344 görüntüleme • 6 ay önce •via X (Twitter)

0 Yorum

Yorum bulunmuyor

Orijinal gönderinin yorumları burada görünecek

Benzer Videolar

"የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በርካታ ገንዘብ፣ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ኢንጀክት እያደረጉ ነው፣ ፓምፕ እያደረጉ ነው። ይህ መግባቱን ተከትሎ ደግሞ የመጣው ጊዜያዊ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋገጥ ታይቷል። እሱ ጥሩ ነው። የፎሬን ከረንሲ ሪዘርቭ ማደጉ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾችም በተወሰነ ደረጃ መረጋገጥ ማሳየታቸው መልካም ጅምር ቢሆንም፣ የተገኘው ለውጥ የኢትዮጵያዊያንን ህይወት በተግባር ካልቀየረ ዘላቂ ትርጉም አይኖረውም። የችግሮቻችን ስር መሰረት ችላ በማለት በጊዜያዊ ማስታገሻዎች እና በፎሬክስ ክምችት እድገት ትረካ ብቻ ሀገርን ረጅም መንገድ መውሰድ የምንችል አይመስለኝም።" ይህ የንግግሩ ትርጉም በድምጹ ውስጥ ያለውን ሀሳብ በተሻለ ቃላት ለማቅረብ የተሞከረ ነው። የንግግሩ አላማ የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ ጊዜያዊ ማስታገሻ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ እንዳልሆነ፣ እናም የህዝቡ ህይወት በተግባር ካልተቀየረ የኢኮኖሚው እድገት ትርጉም አልባ መሆኑን ማስገንዘብ ነው።" ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ - በመጨረሻው የፓርላማ ንግግራቸው ዛሬ ከተናገሩት

Zehabesha

13,706 görüntüleme • 29 gün önce

NOORA RESORT SUNDAY BRUNCH : የኖራ ሪዞርት እሁድ ብራንች – የቤተሰብ ጊዜን በውብ መንገድ ለማሳለፍ ምርጥ ስፍራ! አዲስ አበባ ነዋሪዎች ከከተማዋ ግርግር ራቅ ብለው እሁድን ከቤተሰቦቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በሰላም፣ በመዝናናትና በጥራት የተሞላ መልኩ ለማሳለፍ ከፈለጉ፣ በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) የሚገኘው ኖራ ሪዞርት የሚያዘጋጀው የእሁድ ብራንች ኖራ ምርጥ ምርጫ ነው። የተፈጥሮ ውበቱ፣ የተረጋጋው አካባቢ፣ ጣፋጭና የተለያዩ ምግቦች፣ እንዲሁም ለልጆችና ለቤተሰብ የሚስማማ መዝናኛ ሁኔታዎች ቀኑን የማይረሳ ያደርጉታል። በተጨማሪም ኖራ ሪዞርት በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። በቅርቡ ትልቅ ዘመናዊ የመሰብሰቢያና የዝግጅት አዳራሽ እንዲሁም ወደ 200 የሚደርሱ አዳዲስ የመኝታ ክፍሎች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚውሉ ለላወቅ ችያለሁ። አዳዲስ 100 ክፍሎች አልቀው ስራ ጀምረዋል ይህም ሪዞርቱ ትላልቅ ኮንፈረንሶችን፣ ሰርጎችን፣ የተለያዩ ዝግጅቶችን እና የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን በተሻለ አቅም ለማስተናገድ ያስችለዋል። በዚህ አጋጣሚ የኖራ ሪዞርት ባለቤት አቶ ሸዋ እና መላውን የማኔጅመንት ቡድን በእንግዳ ተቀባይነታቸው፣ በጥራት ባለው አገልግሎታቸው እና በኢትዮጵያ የቱሪዝምና የመስተንግዶ ዘርፍ ላይ እያደረጉት ላለው ትልቅ ኢንቨስትመንት ከልብ አመሰግናለሁ። አቶ ሸዋ የእርስዎ ራዕይ፣ ትጋትና ቁርጠኝነት ለሌሎችም አርአያ ነው። ይህን መልካም ሥራ በመቀጠል ለሀገራችን ቱሪዝም፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚያችን እድገት የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የበለጠ እንዲጎለብት እመኛለሁ። አዲስ አበባ ነዋሪዎች እሁድን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በቢሾፍቱ በሚገኘው ኖራ ሪዞርት በማሳለፍ የማይረሳ ቆንጆ ትዝታ እንዲፈጥሩ ከልብ እጋብዛለሁ።

Natnael Mekonnen

13,389 görüntüleme • 10 gün önce

የድሬ መንገድ ትናንት የድሬዳዋ ከተማን ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ተመልክቻለሁ። ድሬዳዋ ይበልጥ ለመዘመን የምታደርገው እመርታ አስደናቂ ነው። ከድሬ እነዚህን ስድስት ነገሮች እንማር። 1. የድሬዳዋ እና የአካባቢዋ ኢንዱስትሪዎች ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት እንደሚያሣልጡ አይቻለሁ። የራስን ጥሬ ዕቃ አውጥቶ ኢንዱስትሪን ማልማት መለመድ አለበት። 2. ድሬዳዋን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚሠራው ሥራ ሞዴል የሚሆን ነው። ነባር ሆቴሎችን የማሻሻልና አዳዲስ የመገንባት ሥራዎች እየተከናወነ ነው። የድሬዳዋ የኮንፈረንስ ማዕከል ሲጠናቀቅ ለታላላቅ ስብሰባዎች ያለብንን የስብሰባ ማዕከል እጥረት የሚያቃልል ነው። 3. ድሬ እንኳን ተጨማሪ ውበት አግኝታ እንዲያውም ፈጣሪ ያደላት ናት። የከተማ መንገድ ግንባታ ከተማዋን እያዳረሰ ነው። በዚህ ላይ የኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ዐቅም ሆኗታል። የእግረኛ መንገዶች እና የመዝናኛ ቦታዎች እየተገነቡላት ነው። በተለይም የባቡር ታሪክ ያላት ድሬ ፣ የባቡር መሥመርን ከኮሪደር ልማት ያስተሣሠረችበት ስልት ለሌሎች አርአያ የሚሆን ነው። 4. ባቡሩን በቀድሞው መንገድ እስከ ደወሌ እንዲሠራ አድርገውታል። ሀብትን ዐውቆና አልምቶ ለሕዝብ ጥቅም ማዋል እንደዚህ ነው። 5. የድሬ ስታዲዮም ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን አይቻለሁ። የማታ ጨዋታ ቀረጻ ሊደረግበት የቻለ የሀገራችን ስታዲየም ነው። ስታዲየሙን በቶሎ በማጠናቀቅ በቀጣይ ላሰብነው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ዐቅም ሊሆነን ይገባል። 6. በዚህ ሁሉ ላይ የመደመር ትውልድ ቤተ መጻሕፍት ሲጠናቀቅ ድሬ የቱሪዝምና የንግድ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የዕውቀት መናኸሪያ ትሆናለች። ድሬ ብዙ ዐቅም አላት። አመራሩና ሕዝቡ ተባብረው ዐቅሞቿን ማውጣት እና ጸጋዎቿን መግለጥ አለባቸው። የተጀመሩትን በፍጥነት አሟልቶ ማጠናቀቅ ይገባል። ነገሮች አንድ ብቻ መሆን የለባቸውም። እስከ ድሬ የገጠር ቀበሌዎች ድረስ መስፋፋትና መዳረስ አለባቸው። ጀምረናል፤ ግን ገና ብዙ ይቀረናል። ወገባችንን ጠበቅ፣ ሀብታችንን ሰብሰብ አድርገን ተግተን እንሥራ። ያን ጊዜ ድሬዳዋ የዓለም ሕዝቦች የዓይን ማረፊያ ትሆናለች።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

56,210 görüntüleme • 1 yıl önce