Mesay Mekonnen's banner
Mesay Mekonnen's profile picture

Mesay Mekonnen

@mamamesay248,659 subscribers

News anchor

Videos

mamamesay's profile picture

ሄኖክ ስዩም የሚባለው ሰው በይፋ ለብልጽግና ከተሸጠ ቆይቷል። ''ጎንደርን እንሞሽራት'' የተሰኘው የአብይ አህመድ መርዛማው ፕሮጀክት አካል ሆኖ የኪነጥበብ ሰዎችን በብልጽግና ዜማ ሊያስደንሳቸው ጎንደር ይዟቸው ከሄደበት ጊዜ አንስቶ የአብይ አህመድ ሻማ ያዥ ሆኖ ቀርቷል። ነቢዩ ባዬ ካበለጸጋቸው ባለሙያዎች አንዱ ይኸው የዛሬው የአብይ አህመድ ካዳሚ ይገኝበታል። ለማንኛውም አብይ አህመድ እንደመትረየስ ተኳሽ ቦታ እየቀያየረ፥ ከአንዱ ሚዲያ ወደ አንዱ እየተስፈነጠረ አንድ አይነት አሰልቺ፥ ቋቅ የሚል ዲስኩሩን ማንደቅደቁን ተያይዞታል። መሪን የሚያህል ሰው ቃለመጠይቅ ሰጥቶ 10ሺህ ሰው እንኳን በብሄራዊ ቴሌቪዥን የማያዳምጠው ከሆነ ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ክሊፕ ላይ የሚደመጠው አብይ አህመድ የታክሲ ሹፌሮችን ''ዋሹ'' እያለ ነው። ዋሽታችሁ የቱሪዝም ገቢ አምጡልኝ እያለ በአደባባይ ያለሀፍረት ይናገራል። የታክሲ ሹፌሮቹን የገጠማቸው የህይወት ፈተና በቃላት አቅም የሚገለጽ አይደለም። እንደቋጥኝ ላያቸው ላይ የተከመረው የኑሮ ሸክም የመኖር ህልውናቸውን አደጋ ውስጥ አስገብቶት ከፍተኛ ምሬትና ጭንቀት ላይ ናቸው። ይህ ደግሞ የሆነው በዚህ ሰው እብደት ነው። ለኢትዮጵያዊው ደንታ የሌለው፥ ንቀቱ በአፍጢሙ ሊደፋው የደረሰው አብይ አህመድ ለቱሪስት ደስታ ስትሉ ቅጠፉ፥ ዋሹ፥ ፍልቅልቅ ብላችሁ ታዩ፥ እያለ ሲናገር በድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆኜ ነበር የምሰማው። በቃ! ለየለት ማለት ነው? ብሎ ብሎ ከፈጣሪ ጋር ሊያጋጭ፥ የሰማያዊውን አምላክ ምህረት ሊያሳጣ፡ ዋሽታችሁ ዶላር አስመጡልኝ አይነት ጥሪ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ሰውዬው አይናችን እያየ ጨለለ ማለት ነው። ይህ ቃለመጠይቁ በትርጉም አማካኝነት በዲፕሎማቶች የሚታይ መሆኑን ዘንግቶ ነው? የሆነስ ሆኖ የኢትዮጵያ ህመም የሚደበቅ ነውን? አንደበታችን ባይናገረው የገረጣው ገፅታችንን እንዴት እንደብቀው? ሰውዬ አንተስ በደህና ጊዜ አብደሃል፥ ይብላኝ በአንተ ወፈፌ እየተገዛ ላለ 130 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ?!

Mesay Mekonnen

38,635 Aufrufe • vor 15 Tagen

mamamesay's profile picture

አንድ ወፈፌ የሆነ ግለሰብ እኔን ጨምሮ 16 ግለሰቦችን በስም እየጠራ በቅርቡ የሚሞቱ ናቸው የሚል ነገር ሲያወራ የሚታይበትን አንድ ክሊፕ በርካታ ወዳጆች እየላኩልኝ ነው። ከዚህ በፊትም ለሌላ ሰው ተመሳሳይ የሆነ በስድስት ወር ውስጥ እንደምሞት የሚተነብይበትን ክሊፕ አይቼ ነበር። ከሰውዬው ይልቅ እሱን እየጠሩ የሚያስለፈልፉት ሰዎች ናቸው የሚገርሙኝ። ለዚህ ዓይነቱ ነሆለል እብድ እንዴት መድረክ ይፈቅዱለታል? አፉን መቆጣጠር የማይችል፥ አንደበቱ ያልተገራ፥ እንኳን ለሚዲያ፥ ቆሞ ለማውራትም እጅግ የሚዘገንን ሰው ለምን እንደሚያስለፈልፉት አይገባኝም። በአማኑዔል ሆስፒታል ልዩ ጥበቃና ክትትል መደረግ ያለበትን ሰው በተደጋጋሚ ሚዲያ ላይ ማምጣቱ ምን ያህል በሞራልና እሴት እየተሸረሸርን፥ ህብረተሰባችን የእብዶች መጫወቻና ማላገጫ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። ለዚህ ሰው ፈውስን እመኛለሁ። ለአቅራቢዎቹ ደግሞ ማስተዋልን እንዲሰጣቸው ፈጣሪ ይርዳቸው። ብልጽግና የወፈፌዎች ስብስብ ነው የምንለው ያለምክንያት አይደለም። በእብድ የሚመራ የእብዶችና ወፈፌዎች ማህበር ነው - ብልጽግና። ከላይ ነው የተበላሸው - ከአናቱ። በዚህ ሰውና በአብይ አህመድ መሀል ያለው ልዩነት ቤተመንግስት የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ብቻ ነው።

Mesay Mekonnen

36,060 Aufrufe • vor 19 Tagen

mamamesay's profile picture

ብርሃኑ ነጋን ወዳጆች ካሉት ከቆሞ ቀርነት ትንሽ ፈቀቅ ቢያደርጉት ትልቅ ውለታ ነው። ሰው እንዴት ትላንት ላይ ተቸንክሮ ዛሬን ማስተዋል ይሳነዋል? ለወያኔ ያለውን ጥላቻ ሁላችንም እናውቃለን። ከልክ በላይ እንደሚጠየፋቸው እሱም መድረክ ባገኘ ቁጥር የሚናገረው አቋሙ ነው። ነፍጥ እንዲያነሳና የኤርትራ በረሃ እንዲገባ ያደረገው ለወያኔ ያለው ጠንካራ ጥላቻ ነው። በእርግጥ ምክንያት አለው። ወያኔ የሀገር ጠንቅ፥ ዛሬ ለገጠመን ብርቱ የህልውና አደጋ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ እኩይ ሃይል ነው። ግን አሁን ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ወያኔን በአስር ክንድ የሚያስንቅ፥ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ እጅግ ደካማና ጨካኝ እንደሆነ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ወያኔን የታገለውና የሚጠየፈው ብርሃኑ ነጋ ከዚህኛው ቡድን ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ዘንድሮም ስለወያኔ 'ወሮበላነት' ሊነግረን ይፈልጋል። እንዴት ያለ ጉድ ነው የገጠመን ጎበዝ?! እረ ፕሮፌሰር ትንሽ ራመድ በል?! ከተቸነከርክበት አንድ ስንዝር ተንቀሳቀስ እንጂ?! ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት እጅግ ጥልቅ የህልውና አደጋ አንጻር የወያኔ 'ወሮበላነት' በስንት ጣዕሙ?! ዘንድሮም በወያኔ ዜማና ግጥም መደነስ እንዴት ይቻላል? ቤተመንግስት ትልቁን አውሬ አስቀምጦ፥ ከአውሬው ጋር ውስኪ እየተራጩ እንደምን በድሮ በሬ ለማረስ አደባባይ ይወጣል? አረ ትንሽ ሀፍረት ይኑርህ?! 'ወሮበላነት' ነፍጥ የሚያስነሳና በረሃ የሚያስገባ ከሆነ ፕ/ር ብርሃኑ ያንተ መገኛ አዲስ አበባ ባልሆነ ነበር። ያንተስ ቁልቁለት በዛ። ፍሬን ያዝ ማድረግ የሚጠቅመው ከማንም በላይ ለራስህ ነው። እውነቱን ለመናገር ባትችል ዝም በማለት ተባበረን።

Mesay Mekonnen

14,629 Aufrufe • vor 2 Monaten