
Mesay Mekonnen
@mamamesay • 248,659 subscribers
News anchor
Videos

ሄኖክ ስዩም የሚባለው ሰው በይፋ ለብልጽግና ከተሸጠ ቆይቷል። ''ጎንደርን እንሞሽራት'' የተሰኘው የአብይ አህመድ መርዛማው ፕሮጀክት አካል ሆኖ የኪነጥበብ ሰዎችን በብልጽግና ዜማ ሊያስደንሳቸው ጎንደር ይዟቸው ከሄደበት ጊዜ አንስቶ የአብይ አህመድ ሻማ ያዥ ሆኖ ቀርቷል። ነቢዩ ባዬ ካበለጸጋቸው ባለሙያዎች አንዱ ይኸው የዛሬው የአብይ አህመድ ካዳሚ ይገኝበታል። ለማንኛውም አብይ አህመድ እንደመትረየስ ተኳሽ ቦታ እየቀያየረ፥ ከአንዱ ሚዲያ ወደ አንዱ እየተስፈነጠረ አንድ አይነት አሰልቺ፥ ቋቅ የሚል ዲስኩሩን ማንደቅደቁን ተያይዞታል። መሪን የሚያህል ሰው ቃለመጠይቅ ሰጥቶ 10ሺህ ሰው እንኳን በብሄራዊ ቴሌቪዥን የማያዳምጠው ከሆነ ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በዚህ ክሊፕ ላይ የሚደመጠው አብይ አህመድ የታክሲ ሹፌሮችን ''ዋሹ'' እያለ ነው። ዋሽታችሁ የቱሪዝም ገቢ አምጡልኝ እያለ በአደባባይ ያለሀፍረት ይናገራል። የታክሲ ሹፌሮቹን የገጠማቸው የህይወት ፈተና በቃላት አቅም የሚገለጽ አይደለም። እንደቋጥኝ ላያቸው ላይ የተከመረው የኑሮ ሸክም የመኖር ህልውናቸውን አደጋ ውስጥ አስገብቶት ከፍተኛ ምሬትና ጭንቀት ላይ ናቸው። ይህ ደግሞ የሆነው በዚህ ሰው እብደት ነው። ለኢትዮጵያዊው ደንታ የሌለው፥ ንቀቱ በአፍጢሙ ሊደፋው የደረሰው አብይ አህመድ ለቱሪስት ደስታ ስትሉ ቅጠፉ፥ ዋሹ፥ ፍልቅልቅ ብላችሁ ታዩ፥ እያለ ሲናገር በድንጋጤ ስሜት ውስጥ ሆኜ ነበር የምሰማው። በቃ! ለየለት ማለት ነው? ብሎ ብሎ ከፈጣሪ ጋር ሊያጋጭ፥ የሰማያዊውን አምላክ ምህረት ሊያሳጣ፡ ዋሽታችሁ ዶላር አስመጡልኝ አይነት ጥሪ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ሰውዬው አይናችን እያየ ጨለለ ማለት ነው። ይህ ቃለመጠይቁ በትርጉም አማካኝነት በዲፕሎማቶች የሚታይ መሆኑን ዘንግቶ ነው? የሆነስ ሆኖ የኢትዮጵያ ህመም የሚደበቅ ነውን? አንደበታችን ባይናገረው የገረጣው ገፅታችንን እንዴት እንደብቀው? ሰውዬ አንተስ በደህና ጊዜ አብደሃል፥ ይብላኝ በአንተ ወፈፌ እየተገዛ ላለ 130 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ?!
Mesay Mekonnen38,635 Aufrufe • vor 15 Tagen

አንድ ወፈፌ የሆነ ግለሰብ እኔን ጨምሮ 16 ግለሰቦችን በስም እየጠራ በቅርቡ የሚሞቱ ናቸው የሚል ነገር ሲያወራ የሚታይበትን አንድ ክሊፕ በርካታ ወዳጆች እየላኩልኝ ነው። ከዚህ በፊትም ለሌላ ሰው ተመሳሳይ የሆነ በስድስት ወር ውስጥ እንደምሞት የሚተነብይበትን ክሊፕ አይቼ ነበር። ከሰውዬው ይልቅ እሱን እየጠሩ የሚያስለፈልፉት ሰዎች ናቸው የሚገርሙኝ። ለዚህ ዓይነቱ ነሆለል እብድ እንዴት መድረክ ይፈቅዱለታል? አፉን መቆጣጠር የማይችል፥ አንደበቱ ያልተገራ፥ እንኳን ለሚዲያ፥ ቆሞ ለማውራትም እጅግ የሚዘገንን ሰው ለምን እንደሚያስለፈልፉት አይገባኝም። በአማኑዔል ሆስፒታል ልዩ ጥበቃና ክትትል መደረግ ያለበትን ሰው በተደጋጋሚ ሚዲያ ላይ ማምጣቱ ምን ያህል በሞራልና እሴት እየተሸረሸርን፥ ህብረተሰባችን የእብዶች መጫወቻና ማላገጫ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። ለዚህ ሰው ፈውስን እመኛለሁ። ለአቅራቢዎቹ ደግሞ ማስተዋልን እንዲሰጣቸው ፈጣሪ ይርዳቸው። ብልጽግና የወፈፌዎች ስብስብ ነው የምንለው ያለምክንያት አይደለም። በእብድ የሚመራ የእብዶችና ወፈፌዎች ማህበር ነው - ብልጽግና። ከላይ ነው የተበላሸው - ከአናቱ። በዚህ ሰውና በአብይ አህመድ መሀል ያለው ልዩነት ቤተመንግስት የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ብቻ ነው።
Mesay Mekonnen36,060 Aufrufe • vor 19 Tagen

አብይ አህመድን የምስጋና ጠኔ ሊገለው ነው። ነፍሱ በእጅጉን ምስጋናን ተርባለች። የግብዝ ሰው አንዱ መገለጫ የጭብጨባና የውዳሴ ጥማቱ የትየለሌ መሆኑ ነው። አምፖል ሰቅዬ አላመሰገናቹኝም፥ ዘንባባ በየቦታው ተክዬ አላጨበጨባችሁልኝም፥ መንደራችሁን ፏፏቴ በፏፏቴ አድርጌላችሁ አንደበታችሁ ለምስጋና ንፉግ ሆነብኝ፥ ፓርክና ሎጅ በየቦታው ገንብቼ አፋችሁ ለውዳሴ አልከፈት አለ፥ ማይክ በጨበጠ ቁጥር የምስጋና ረሃቡን ለመግለጽ ጭንቅ ጥብብ ሲል ለሰማው፥ የሰውዬውን ጤንነት ይበልጥ እንዲጠራጠር ያደርገዋል። የውጭ ሰዎች እያነደቁ፥ የባዕድ ቲክቶከሮች 'ምርጫ አያስፈልጋችሁም፥ መሪ ከእግዚያብሄር ተሰጥቷችኋል' እያሉ፥ እነአሜሪካና አውሮፓ በሰራሁት እየቀኑ እናንተ ግን አንዲት የምስጋና ቃል መተንፈስ አቃታችሁ' እያለ ጭቅጭቅ ያደርገናል። እባካችሁ አንድ በሉት!
Mesay Mekonnen16,460 Aufrufe • vor 2 Monaten

ብርሃኑ ነጋን ወዳጆች ካሉት ከቆሞ ቀርነት ትንሽ ፈቀቅ ቢያደርጉት ትልቅ ውለታ ነው። ሰው እንዴት ትላንት ላይ ተቸንክሮ ዛሬን ማስተዋል ይሳነዋል? ለወያኔ ያለውን ጥላቻ ሁላችንም እናውቃለን። ከልክ በላይ እንደሚጠየፋቸው እሱም መድረክ ባገኘ ቁጥር የሚናገረው አቋሙ ነው። ነፍጥ እንዲያነሳና የኤርትራ በረሃ እንዲገባ ያደረገው ለወያኔ ያለው ጠንካራ ጥላቻ ነው። በእርግጥ ምክንያት አለው። ወያኔ የሀገር ጠንቅ፥ ዛሬ ለገጠመን ብርቱ የህልውና አደጋ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ እኩይ ሃይል ነው። ግን አሁን ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ወያኔን በአስር ክንድ የሚያስንቅ፥ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ እጅግ ደካማና ጨካኝ እንደሆነ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ወያኔን የታገለውና የሚጠየፈው ብርሃኑ ነጋ ከዚህኛው ቡድን ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ዘንድሮም ስለወያኔ 'ወሮበላነት' ሊነግረን ይፈልጋል። እንዴት ያለ ጉድ ነው የገጠመን ጎበዝ?! እረ ፕሮፌሰር ትንሽ ራመድ በል?! ከተቸነከርክበት አንድ ስንዝር ተንቀሳቀስ እንጂ?! ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት እጅግ ጥልቅ የህልውና አደጋ አንጻር የወያኔ 'ወሮበላነት' በስንት ጣዕሙ?! ዘንድሮም በወያኔ ዜማና ግጥም መደነስ እንዴት ይቻላል? ቤተመንግስት ትልቁን አውሬ አስቀምጦ፥ ከአውሬው ጋር ውስኪ እየተራጩ እንደምን በድሮ በሬ ለማረስ አደባባይ ይወጣል? አረ ትንሽ ሀፍረት ይኑርህ?! 'ወሮበላነት' ነፍጥ የሚያስነሳና በረሃ የሚያስገባ ከሆነ ፕ/ር ብርሃኑ ያንተ መገኛ አዲስ አበባ ባልሆነ ነበር። ያንተስ ቁልቁለት በዛ። ፍሬን ያዝ ማድረግ የሚጠቅመው ከማንም በላይ ለራስህ ነው። እውነቱን ለመናገር ባትችል ዝም በማለት ተባበረን።
Mesay Mekonnen14,629 Aufrufe • vor 2 Monaten

እንደዚህ ጅላጅል ፓርቲ ግን ምድር ላይ ያለም አይመስልም። ህወሀት ሀጢያቱ የሚገዝፈው እነዚህን ደካማና በጎሳ ኮታ የተሰባሰቡ ሰዎችን ወደላይ አውጥቶ ሀገሪቱን እጃቸው ላይ ጥሎ መሰናበቱ ነው። በ21ኛው ክ/ዘመን እንዲህ ዓይነት ስብስብ መኖሩ በራሱ ትዕንግርት ነው። የአንድ እብድ ግለሰብ - የጭንቅላት ጭማቂ የሆነውና ስሙ የከበደው ፓርቲ በአደባባይ ሲጃጃል ማየት ያሸማቅቃል። በእውነት ለኢትዮጵያ በዚህ ስብስብ መመራት እርግማን ነው።
Mesay Mekonnen22,477 Aufrufe • vor 5 Monaten

ይህ ከታች የምታዳምጡት ብርሃኑ ነጋ በአሁኑ ብርሃኑ ነጋ ተቀርጥፎ ተበልቷል። ሰው ራሱን በራሱ ሲያጠፋ እንዲህ ነው። እነዚያ የዲሲ መድረኮች ላይ፥ በቨርጂኒያ አዳራሾች ውስጥ፥ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች ሲስተጋቡ የነበሩ የብርሃኑ የፍትህና የነጻነት ድምጾች አየር ላይ ተነዋል። ይህን የመሰለ ስሜት ገዢና ሰው ሰው የሚሸት መልዕክት ያሰማን አንደበት፡ የአብይ አህመድን አረመኔያዊ አገዛዝ ሲያገለግልና ጥብቅና ሲቆም መስማት ያስደነግጣል። ለአሁኑ ብርሃኑ ነጋ የምናቀርብለት አንድ ጥያቄ የትላንቱን ብርሃኑ ነጋ የት አደረከው? ውጠኸውም ከሆነ ትፋውና ለኢትዮጵያ ይድረስላት የሚል ነው።
Mesay Mekonnen15,101 Aufrufe • vor 4 Monaten

አንድ የተቀነጫጨበ የድምጽ ቅጂ በተለያዩ ማህበራዊ መድረኮች ላይ መሰራጨቱን አንዳንድ ወዳጆች አሳውቀውኝ ተመልክቼዋለሁ። ይህ በእኔና በጄነራል ተስፋዬ አያሌው መሀል የተደረገው ምልልስ ከአንከር ሚዲያ ወጥቶ ሌሎች ዘንድ የደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ እያጣራነው እንገኛለን። 15 ደቂቃ ከሚሆነው የእኔና የጀነራል ተስፋዬ አያሌው ምልልስ የተቀነጫጨበና ፈጽሞ ከዋናው ምልልስ አውድ የተለየ መልዕክት እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራጨው የድምጽ ቅጂ ብዙዎችን እንዳደናገረና በእኔም ሆነ በአንከር ሚዲያ ላይ የተለየ የቅሬታ አስተያየት እንዲሰጥ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ይህን ሆን ተብሎ የተደረገውን አደናጋሪ የድምጽ ቅጂ የሚገኝበትን ዋናውን ሙሉ ምልልስ እንደወረደ ለማቅረብ ተገደናል። ምንም ዓይነት ኤዲቲንግ ሳይደረግ እንዳለ የሁለታችንን ምልልስ የሚደመጥበትን የድምጽ ቅጂ ዛሬ ምሽት የምናቀርብ እንደሚሆን ለመግለጽ እንወዳለን።
Mesay Mekonnen26,013 Aufrufe • vor 1 Jahr

''ከታህሳስ አንድ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የአንድነት ሳምንት እናድርገው'' አርበኛ ጌታ አስራደ
Mesay Mekonnen22,907 Aufrufe • vor 1 Jahr